ሌሎችን ለማገዝ የሞባይል መተግበሪያ የሰራው ኢትዮጵያዊ ወጣት

ወጣት ናታን ዳምጠው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን በ2007 ዓ.ም ሲቀላቀል ለትምህርቶቹ ልዩ ትኩረት ሰጥቷል። ነገር ግን ከዚያ በፊት ለኮምፒተር ሳይንስ የነበረው እውቀት አናሳ ስለነበር ችግር ሆኖበታል። ችግሩ ግን መልካም ነገርን አመጣ። እርሱ ባለፈበት ችግር ውስጥ ሌሎች ተማሪዎች እንዳይቸገሩ በማሰብ መፍትሔ ብሎ ያሰበውን ነገር ለመስራት ወሰነ። ተሳክቶለትም አሁን ከ7 እስከ 13 ዓመታት ያሉ ሕጻናት መሰረታዊ የኮምፒውተር ሳይንስ የሚማሩበትን የሞባይል መተግበሪያ ፈጥሯል።