የደቡብ ኮሪያው 'ፓራሳይት' ፊልም በኦስካር ሽልማት ታሪካዊ ሆነ

ቡን ጁን ሆ Image copyright Getty Images

የደቡብ ኮሪያው ፊልም 'ፓራሳይት' በዘንድሮው የኦስካር ሽልማት በምርጥ ፊልም (ቤስት ፒክቸር) ዘርፍ አሸንፏል።

በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያልተሰራ ፊልም በዚህ ዘርፍ ሲያሸንፍ የመጀመሪያው ሲሆን ታሪካዊም ነው ተብሏል።

ሬኔ ዜልዌገር 'ጁዲ' በሚለው ፊልም የጁዲ ጋርላንድን ገፀ ባሕርይ ወክላ በመጫወት በሴት ተዋንያን ዘንድ የምርጥ ተዋናይነትን ዘርፍ ያሸነፈች ሲሆን፤ ጆዋኩን ፊኒክስ 'ጆከር' በሚለው ፊልሙ በወንዶች ምርጥ ተዋናይ ዘርፍ ሽልማቱን ወስዷል።

የሆሊውዱ ሃኪም ገብረወልድን ያውቁታል?

ኢትዮጵያውያን 'የሌሉበት' ስለ ኢትዮጵያ የሚዘክረው ሬድ ሲ ዳይቪንግ ሪዞርት ፊልም

ብራድ ፒት 'ዋንስ አፕ ኦን ኤ ታይም ኢን ሆሊውድ' ላውራ ደርን ደግሞ 'ሜሪጅ ስቶሪ' በሚለው ፊልማቸው በረዳት ተዋናይነት ዘርፍ አሸንፈዋል።

ፓራሳይት በአጠቃላይ አራት ሽልማቶችን ያሸነፈ ሲሆን፤ የሰር ሳም ሜንዴዝ ፊልም '1917' ሶስት ሽልማቶችን ወስዷል።

ምንም እንኳን በአንደኛው የዓለም ጦርነት ላይ የሚያጠነጥነው '1917' በምርጥ ፊልም ዘርፍ ቢታጭም፤ ሽልማቶቹ በሙሉ በቴክኒክ ዘርፍ ናቸው።

Image copyright Getty Images

የፓራሳይት ዳይሬክተር ቦንግ ጁን ሆ ቢት በምርጥ ዳይሬክተርነትም ሰር ሳምን አሸንፎ ሽልማቱን ወስዷል። ከዚህም በተጨማሪ ፊልሙ በምርጥ ፅሁፍ ዘርፍም ሽልማቱ ሊያሸንፍ ችሏል።

የፊልሙ ታሪክ የሚያጠነጥነው ሁለት ከተለያየ መደብ የመጡ ቤተሰቦችን ህይወት ሲሆን፤ በምፀት መልኩም ያስቃኛል። አንደኛው ቤተሰብ ቁምጥምጥ ያለ ደሃ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የናጠጠ ሃብታም ነው።

እግራቸው አሜሪካ ልባቸው አፍሪካ ያለ የሆሊውድ ተዋንያን

ዶናልድ ትራምፕን ከዝነኛው ፊልም ማን ቆርጦ ጣላቸው?

ኦስካር ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ 92 አመታት ቢያስቆጥርም በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያልተሰራ ፊልም ሲያሸንፍ የመጀመሪያው ነው፤ ይህም ሁኔታ ብዙዎችን አስደምሟል።

የፊልሙ ፕሮዲውሰር ክዋክ ሲን አኤ ሽልማቶቹን ከተቀበለ በኋላ "ቃላት የለኝም። በጭራሽ ይህ ይፈጠራል ብለን አላሰብንም። ይህ ለኛ ታሪካዊ ቀን ነው" ብሏል።

በፊልም ታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የኦስካር ሽልማት የተቀበለው ብራድ ፒት በስነስርአቱ ወቅት ባደረገው ንግግር ዶናልድ ትራምፕን እንዲሁም ሪፐብሊካን ፓርቲን ወርፏቸዋል።