ሶማሊያ፡ ታዳጊዋን ደፍረው ለህልፈት የዳረጉት በጥይት ተደብድበው ተገደሉ

አይሻ ኢልያስ አደን Image copyright Radio Banaadir

በሶማሊያ ሰሜን ምስራቅ ግዛት የአስራ ሁለት አመት ታዳጊዋን የደፈሩ ሁለት ወንዶች በተኳሽ ቡድን በጥይት እንዲገደሉ ፍርድ ቤቱ ባዘዘው መሰረት ቅጣቱ በትናንትናው እለት ተፈፃሚ ሆኖባቸዋል።

የፑንት ላንድ ነዋሪ የሆነችው አይሻ ኢልያስ አደን ጋልካዮ ከሚባለው አካባባቢ ቁጥራቸው የማይታወቅ ወንዶች ጠልፈው ከወሰዷት በኋላ በቡድን ደፍረው የጣሏት ቤቷ አካባቢ ነበር።

ሁኔታው ከፍተኛ ድንጋጤንና ቁጣን ያስከተለ ሲሆን ብዙዎች በሰልፍ ሃገሪቷን አጥለቅልቀውት ነበር።

‘በአስራ አራት ዓመቴ ስደፈር የሚያሳይ ቪዲዮ በወሲብ ፊልም ድረገፅ ላይ ነበር'

የአስገድዶ መደፈር ክሷን ለመከታተል የሄደችው ወጣት በእሳት ተቃጠለች

የተነጠቀ ልጅነት

አስር ተጠርጣሪዎች ታዳጊዋን በመድፈር ተይዘው የነበረ ሲሆን የአካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሶስቱን ጥፋተኛ ሆነው አግኝቷቸዋል።

ግለሰቦቹን ለመጀመሪያ ጊዜ የዲኤንኤ (ዘረ መል) ማስረጃን በመጠቀም ጥፋተኛነታቸው መረጋገጡን አቃቤ ህግጋትም አሳውቀዋል።

ጥፋተኛ ሆነው የተገኙት አብዲፈታህ አብዱራህማን ዋርሳሜና አብዲሻኩር ሞሃመድ ዲጌ፣ ቦሳሶ በሚገኝ አደባባይ ላይ በተኳሽ ቡድን በትናንትናው እለት በጥይት እንደተገደሉ ዘ ጋሮዌ የተባለው ድረገፅ አስነብቧል።

በህንድ በቡድን ተደፍራ የተገደለችው ዶክተር ጉዳይ ከፍተኛ ቁጣን ቀሰቀሰ

ሶስተኛ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው አብዲሰላም አብዲራህማን በሞት የተቀጣው የአብዲፈታህ ወንድም ሲሆን ምንም እንኳን የሞት ፍርድ ቢፈረድበትም ቅጣቱ ተግባራዊ ሳይደረግበት ቀርቷል።

የታዳጊዋ አይሻ አባት ኢልያስ አደን ለፑንት ላንድ መንግሥታዊ ጣቢያ እንደተናገሩት የአብዲሰላምን ቅጣት ሁኔታው እንደገና እስኪገመገም ፍርድ ቤቱ ለአስር ቀናት እንዲያዘገየው መጠየቃቸውን ነው።

"እንዲህ አይነት አይቀጡ ቅጣት በተለይ የሞት ፍርድ የማያዳግም ምክር ያስተላልፋል። የሶማሊያ ሴቶችም ደህንነታቸው የተጠበቀ ይሆናል" ብለዋል አቶ አደን።

መደፈርና ሌሎች ፆታዊ ጥቃቶች በሶማሊያ በቅርብ አመታት መበራከታቸውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ይናገራሉ።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ