ሳዑዲ መራሹ ኃይል በየመን ለተፈጸሙት ጥሰቶች ፍርድ ሊቀርብ ነው

በሳዑዲ መራሹ ጥምር ኃይል የአየር ጥቃት ጉዳት ደርሶባት ህክምና እያገኘ ያለ አዳጊ። Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በሳዑዲ መራሹ ጥምር ኃይል የአየር ጥቃት ጉዳት ደርሶባት ህክምና እያገኘ ያለ አዳጊ።

በየመን የጦር እርምጃ እየወሰደ የሚገኘው ሳዑዲ መራሹ ኃይል፤ በዚያች አገር ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የፈጸሙ ወታደሮችን በህግ ሊጠይቅ መሆኑን አስታወቀ።

የተባበሩት መንግሥት ጥምር ኃይሉ በየመን የጦር ወንጀሎችን ሳይፈጽም አይቀርም ይላል።

ይሁን እንጂ ጥምር ኃይሉ የራሱን ወታደራዊ ኃይሎች በገለልተኛነት ይዳኛል ወይ የሚለው የበርካቶች ጥያቄ ነው።

የመን ደም አፋሳሽ በሆነው የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ የምትገኝ ሲሆን፣ የሁቲ አማጺያን ምዕራባዊ የየመን ክፍልን በቁጥጥራቸው ሥር ማድረጋቸውን ተከትሎ ፕሬዝደንት አብደራቡህ ማንሱር ሃዲ አገር ጥለው ከተሰደዱ በኋላ ጦርነቱ ተጋግሎ ቀጥሏል።

የተባበሩት መንግሥታት እስካሁን በየመን 7500 ነጹሃን ዜጎች መሞታቸውን ያረጋገጥ ሲሆን አብዛኛዎቹ ህይወታቸውን ያጡት በሳዑዲ በሚመራው ጥምር ኃይል የአየር ድበደባዎች ነው።

በጥምር ኃይሉ ተፈጽሟል ከተባሉት እና በችሎቱ ከሚታዩ ጉዳዮች መካከል የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው፡

  • እአአ 2016 ላይ አብስ በሚሰኘው ገጠራማ ሆስፒታል ላይ የተሰነዘረው እና 19 ሰዎች የተገደሉበት የአየር ጥቃት
  • እአአ 2018 ላይ በባኒ ቃይስ ሰርግ እየታደሙ በነበሩ ሰዎች ላይ የተሰነዘረው እና 20 ሰዎችን የተገደሉበት የአየር ጥቃት እንዲሁም
  • እአአ 2018 ላይ በአውቶብስ ላይ የተሰነዘረው እና 29 ህጻናት የተገደሉበት ጥቃት ይገኝበታል።