በማህበራዊ ሚዲያ ውሃ አጣጭን ለማግኘት የሚረዱ ሰባት ነጥቦች

በቡዳፔስት ከተማ ወጣት ሴት ስልክ ይዛ Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ አጣማሪዎን እናገናኛለን የሚሉ መተግበሪያዎች ላይ ውሃ አጣጭ መፈለግ ነውር አይደለም። ነገር ግን ፍለጋውን እርስዎ ሊወዱት ይገባል

ዛሬ፣ በፍቅረኞች ቀን፣ ሁሉም ጥንድ ጥንድ ሆኖ ሲሄድ እያዩ እርስዎ ግን ብቻዎን በመሆንዎ ቆዝመዋል? የፍቅር አጋርዎን ማግኘት ይፈልጋሉ?

እንደ ስታስቲስታ ግምት ከሆነ 240 ሚሊዮን የሰዎች ጎርፍ ወደ የፍቅር አጋር አገናኝ ድረ ገጾች ይተማሉ። ነገር ግን ሁሉም 'ያሰብኩት ተሳካ ያለምኩት ደረሰ፤ ሐሳቤም ተሟላ መንፈሴ ታደሰ' ብሎ አይመለስም።

ከራሱ ሠርግ በጠራቸው እንግዶች የተባረረው ሙሽራ

ለዚያም ነው የፍቅርና የትዳር ግንኙነቶች አማካሪና የበርካታ መጽሐፍት ደራሲ የሆነችው ሱዚ ሄይማንን ምክር ልናካፍላችሁ የወድነው።

1. የፍቅር አጋር ለማግኘት ብለው ብቻ ቀጠሮ አይቀበሉ

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ደንብ አንድ፡ ካልፈለጉ አያድርጉት

"መሞከር" አድካሚ ነው፤ ያሰለቸናል፣ ስሜታችንን ያደፈርሰዋል፤ ስለራሳችን ያለንንም ግምት ዝቅ ያደርግብናል። ስለዚህ ካልፈለጉ፤ ልብዎን ደስ ካላለው አያድርጉት። በማህበራዊ ሚዲያ የተዋወቁትን ሰው ልብዎን ካላሞቀው፣ ቀልብዎን ካልሳበው አያግኙ።

2. ደመ ነፍስዎን ይመኑ

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ደስ ካላለዎት ወይንም ሊያገኙ የቀጠሩትን ሰው ካላመኑት ወዲያውኑ ይወስኑ

በማንኛውም ሰዓት አደጋ የሚመስል ነገር ከሸተትዎት ወዲያውኑ እርምጃ ይውሰዱ። አንዳንዴ አእምሮ ውስጥ 'እንዲሁ ተጠራጣሪ ሆኜ' ነው የሚል ቀጭን ሐሳብ ሰበዝ መጥቶ ወይንም ሌላ ሰበብ ሰጥተው ወደ ቀጠሮዎ ሊሄዱ ይችላሉ።

በሠርግ ዕለት ማታ በጉጉት የሚጠበቀው 'የደም ሸማ'

ይህ ግን በማህበራዊ ሚዲያ ለተዋወቁት ሰው አይመከርም። ከተጠራጠሩ ደመ ነፍስዎን ይመኑ።

3. በማህበራዊ ሚዲያ መልዕክት ሲቀባበሉ ቁጥብ መሆን ብልህነት ነው

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ በማህበራዊ ሚዲያ የመልዕክት ናዳ ከማዝነብ ይልቅ ቁጥብና ወደ ነጥቡ የሚያተኩር መልዕክት መለዋወጥ ይመከራል

በማህበራዊ ሚዲያ ለተዋወቁት ሰው የመልዕክት ዶፍ ከማዝነብ ይልቅ፤ ልብዎን የሚያሞቅ ገንቢ የሆነ ጥቂት መልዕክት በቂ ነው (ከብዛት ይልቅ ጥራት)።

በፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ቲውተር፣ ቴሌግራም... ለተዋወቁት ሁሉ መልዕክት መጻፍ፣ ለተጻፈልዎት መመለስ የእርስዎንም ልብ ማፍሰሱ፣ ስሜትዎንም ማጎሹ አይቀርም። ስለዚህ ለተመረጠ ብቻ የተቀነበበ መልዕክት መላክ ብልህነት ነው።

በተለይ ሲያወሯቸው ደስ የሚልዎትን ሰው ብቻ ቢያዋሩ ጠቃሚ ነው። ያ ማለት የወደፊት አጋር የመሆን እድል ካላቸው ሰዎች ጋር መልዕክት መለዋወጥ ጥሩ ነው።

4. የፍቅር አጋርን በማበራዊ ሚዲያ ለማግኘት ከወሰኑ በርካታ ተጠቃሚ ያላቸውን መተግበሪያዎችን ይጠቀሙ

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ በርካታ ተጠቃሚ ያላቸው ማህበራዊ ሚዲያዎችን የሚጠቀሙ ከሆነ በርካታ ምርጫ ይኖርዎታል። ብዙም ሰው የማያውቃቸው ማህበራዊ ሚዲያዎችን ያርቁ

ልፋት ብቻ የሚያደርግዎ ተጣማሪ አገናኞችን አልያም ማህበራዊ ሚዲያዎችን ያስወግዱ። በርካታ ሰዎች ወደሚጠቀሟቸው ድረገፆች ወይም መተግበሪያዎች ጎራ ይበሉ።

በማህበራዊ ሚዲያ የፍቅር አጋር የማግኘት ጉዳይ የምርጫ ጉዳይ ነው። ምርጫ ደግሞ ካለ በርከት ያለ የሚመረጥ አጋር መኖር አለበት። ስለዚህ ከበርካታ ራሳቸውን ቀባብተው ብቅ ከሚሉ አማላይ የፍቅር አጋር ፈላጊዎች መካከል የእርስዎን እንቁ (የሚኮሩበትን) ለማግኘት ይትጉ።

5. በቅድሚያ ጓደኝነት

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ከሁሉም በላይ ጓደኝነት ይቀድማል

በትዳር ረዥም ዓመት በስኬትና በደስታ የቆዩ ሰዎች፣ የትዳር አጋር ብቻ ሳይሆን ጓደኛቸውን እንዳገኙም ሲናገሩ ይደመጣል። እርስዎም የልብዎን ፍላጎት፣ በክፉ ቀን ምርኩዝ የሚሆን፣ በደስታ በሐዘን የማይለይዎትን የትዳር አጋር ለማግኘት ሲጀምሩ ከጓደኝነት ቢሆን መልካም ነው።

ግንኙነት ለትዳር ተብሎ እንደማይጀመር በፍለጋዎ የመጀመሪያው ምዕራፍ የመጀመሪያ ገጽ ላይ ማወቅ ጠቃሚ ይሆናል። ደግሞ የወደፊት ውሃ አጣጭዎን በጥሩ ጓደኛዎ በኩልም ሊተዋወቁ እንደሚችሉ ማስታወስ ተገቢ ነው።

6. ምርጫዎትን አይገድቡ

ከሰው የሚወዱትን ነገር በቀላሉ እንደሚለዩና ምን እንደሚፈልጉ የሚያውቁ ሊመስልዎት ይችላል። ነገር ግን ይህ ሰው ምኑም እኔ የምፈልገውን አይመስልም ካሉት ጋር ተጣምረው የሕይወት ዘመንዎን በደስታና በተድላ ሊኖሩ ይችላሉ።

ስለዚህ የሚፈልጉትን ለማግኘት መስፈርትዎን አያጥብቡት። ምርጫን ሳይገድቡ ግራ ቀኝ ማየት ጥሩ ነው።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ በማህበራዊ ሚዲያ ሕይወቴ ሕይወት የሚሉትን ሰው ሊያገኙ ይችላሉ፤ ያ ማለት ግን መጠናናት፣ የመምረጫ መስፈርትዎን ሁሉ አሽቀንጥረው ይጥላሉ ማለት አይደለም

7. ጥንቁቅ ይ

በኢንተርኔትና በማህበራዊ ሚዲያ የፍቅር አጋርን መተዋወቅ ግንባር ቀደም ድክመቱ የጋራ የሚሉት ሰው፣ ወዳጅ አለማወቅዎ ነው። ስለሚያገኙት ሰው ተሟላ መረጃ የሚሰጥ ማንም የለም።

የኢትዮጵያዊያንን ትዳር አከርካሪ እየሰበረ ያለው ምን ይሆን?

ከሚያገኙት ሰው አጠራጠጣሪ ነገር በገጠመዎ ወቅት ቸል አይበሉ። በተዋወቁ ሰሞን ገንዘብ የሚጠይቁ፣ በተደጋጋሚ ሚይዙትን ቀጠሮ የሚሰርዙ፣ ስለራሳቸው በሚገባ ማይገልጽ እና ሌሎች አጠራጣሪ ነገሮች ሲፈጠሩ ይጠንቀቁ።

በስሜት አበላ አይዘፈቁ። ጥንቃቄ...ጥንቃቄ...ጥንቃቄ...

ተያያዥ ርዕሶች