ቼልሲ ከ ዩናይትድ ማን ያሸንፋል? የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ግምቶች

ዎልቭስ ከ ሌስተር
አጭር የምስል መግለጫ ዎልቭስ ከ ሌስተር

የ26ኛው ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ በሚደረግ ግጥሚያ ይጀምራሉ።

በሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ የተባለው ቼልሲን ከማንችስተር ዩናይትድ ያፋጥጣል። ማን ያሸንፋል? የቢቢሲው ስፖርት ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ግምቶቹን አስቀምጧል።

ዎልቭስ ከ ሌስተር

ዎልቭስ እና ሌስተር በዘንድሮ የውድድር ዓመት ድንቅ አቋም እያሳዩ ይገኛሉ። ሁለቱም በመጀሪያዎች አራት ውስጥ ሆነው የመጨረስ ዕድል አላቸው።

ዛሬ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ሲል ፕሪሚየር ሊጉ ዎልቭስን ከሌስተር ያገናኛል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ድንቅ ጨዋታ እንደሚታይበት ይጠበቃል።

ባለፈው የውድድር ዓመት ዲኦጎ ጆታ ሦስታ (ሃትሪክ) በሠራበት ግጥሚያ ዎልቭስ ሌስተርን አስተናግዶ 4-3 ማሸነፍ ችሎ ነበር።

ዛሬስ? ላውሮ የዎልቭስ ልጆች ሌስተርን 2ለ1 አሸንፈው በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ ከቶተንሃም አናት 6ኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣሉ ብሏል።

አጭር የምስል መግለጫ ኖርዊች ከ ሊቨርፑል

ኖርዊች ከ ሊቨርፑል

ነገ ቅዳሜ ሁለት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። 09፡30 ሲል ሳውዝሃምፕተን ከበርንሌይ ይገናኛሉ።

ላውሮ ይህ ጨዋታ በባለ ሜዳዎቹ ሳውዝሃምፕተኖች በድል ይጠናቀቃል ብሏል።

ቅዳሜ ምሽት 02፡30 ላይ የፕሪሚየር ሊጉ መሪ የሆኑት ሊቨርፑሎች ወደ ካሮ ሮድ አቅንተው በፕሪሚየር ሊጉ መጨረሻ ደረጃ ላይ ከሚገኙት ኖርዊች ጋር ይገናኛሉ።

ላውሮ አይበገሬዎቹ ሊቨርፑሎች ቢያንስ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ያሸንፋሉ ይላል።

አጭር የምስል መግለጫ አስቶን ቪላ ከ ቶተንሃም

አስቶን ቪላ ከ ቶተንሃም

ቶተንሃሞች ከማንችሰተር ሲቲ ወሳኝ የሆኑ 3 ነጥቦችን መሰብሰባቸው ይታወሳል።

አሁንም ቢሆን አስተማማኝ የሆነ ወጥ አቋም ላይ ባይገኙም ይህን ጨዋታ እንደሚያሸንፉ ጥርጥር ይለኝም ይላል ላውሮ።

አስቶን ቪላ 0 ቶተንሃም 2 ሲል ግምቱን ያስቀመጠው ላውሮ ነው።

አርሰናል ከኒውካስትል

ሌላው በጉጉት የሚጠበቀው ጨዋታ ኢምሬትስ ላይ የሚካሄደው የአርሴናል እና ኒውካስል ዩናይትድ ጨዋታ ነው።

አርሰናሎች የአቻ ባለሙያዎች የሚል ቅጽል ስም ተሰጥቷቸዋል። በዘንድሮ የፕሪሚየር ሊግ ውድድር ካደረጓቸው 25 ጨዋታዎች 13ቱ በአቻ ውጤት ነው የተጠናቀቁት።

ይህን ጨዋታ ግን በደጋፊዎቻቸው ፊት እንደሚያሸንፉ ተስፋ አደርጋለሁ ይላል ላውሮ።

ውጤት አርሰናል 2 ኒውካስል 0 ።

ቼልሲ ከ ማንችስተር ዩናይትድ

የሳምንቱ ሌላው ወሳኝ ጨዋታ ቼልሲን ከ ማንችስተር ዩናይትድ ያገናኛል። ሰኞ ምሽት በሚካሄደው ጨዋታ ላውሮ ቼልሲ የበላይነት ይዞ እንደሚያጠናቅቅ ግምቱን አስቀምጧል።

የላውሮ ግምት ቼልሲ 2 ማንችስተር ዩናይትድ 0 ።

ማንችስተር ሲቲ ከዌስት ሃም

ረቡዕ የካቲት 11 ከምሽቱ 4፡30 ላይ ሲቲዎች የለንደኑን ክለብ ዌስት ሃም ዩናይትድን ያስተናግዳል።

ሲቲ ይህን ጨዋታ በብዙ የጎል ልዩነት እንደሚያሸንፍ ተገምቷል።

ላውሮ ሲቲ ይህን ጨዋታ 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ያሸንፋል ብሏል።

ተያያዥ ርዕሶች