አውስትራሊያ፡ ለሰደድ እሳት መከላከያ ገቢ ለማሰባሰብ የተዘጋጀው የሙዚቃ ድግስ ሺዎችን አስተናግዷል

የሙዚቃ ድግሱ ታዳሚዎች Image copyright EPA

በአውስትራሊያውያው ሰደድ እሳት የተጎዱ አካባቢዎች መቋቋሚያና መልሶ ማልሚያ ገቢ ለማሰባሰብ በተዘጋጀው የሙዚቃ ድግስ ላይ በሺዎች ሚቆጠሩ ዜጎች እየታደሙ ሲሆን እስከ 10 ሚሊየን የአውስትራሊያ ዶላር እንደሚሰበሰብ ተገምቷል።

'ኩዊን ኤንድ አሊስ ኩፐር፣ 5 ሰከንድስ ሰመር፣ ቲና አሬና እንዲሁም ዴልታ ጉድረምን የመሳሰሉ እውቅ አውስትራሊያውያን በሙዚቃ ድግሱ ላይ ተሳታፊዎች መሆናቸው ታውቋል።

'' አውስትራሊያዊ እንደመሆናችን ሁሉንም ነገር አብረን እንቋቋመዋለን፤ እንደምንመለከተው ከላይ ያሉት ኃላፊዎች ግድ የሚሰጣቸው አይመስልም'' ብሏል የድግሱ አዘጋጅ ሴሌስት ባርበር።

አውስትራሊያ በሰደድ እሳት ሳቢያ የአስቸኳይ ጊዜ አወጀች

እውን አውስትራሊያ እንዲህ እየተቃጠለች ነው?

በአውስትራሊያ በቅርቡ የተከሰተው ሰደድ እሳት በትንሹ 33 ሰዎችን ህይወት ሲቀጥፍ በሺዎች የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶችን ደግሞ ከጥቅም ውጭ ማድረጉ የማይዘነጋ ነው።

አውስትራሊያ ከባለፈው መስከረም ወር ጀምሮ በተነሳ ሰደድ እሳት እየተቃጠለች ቆይታለች። ከካንቤራ ከተማ በስተደቡብ አቅጣጫ እየገሰገሰ የሚገኘው የሰደድ እሳት ደግሞ የአውስትራሊያ ባለስልጣናትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲደነግጉ እስከማስገደድ ደርሷል።

ባለስልጣናቱ እንደሚሉት አሁን በአካባቢው ያጋጠመው ሰደድ እሳት ምናልባትም ከሁለት አስርት ዓመታት ወዲህ አስከፊው ነው። እስካሁን ባለው ሁኔታም ይሄው አስከፊ ሰደድ እሳት 11 ሚሊየን ሄክታር ያክል አካባቢ መሬት አውድሟል።

ጠቅላይ ሚንስትር ሞሪሰን ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፤ የሰደድ እሳቱ ተባብሶ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ሰደድ እሳት ተዋጊ የሆኑ ተጨማሪ አውሮፕላኖችንም ወደ ሥራ ለማስገባት ተጨማሪ በጀት መጽደቁን ተናግረዋል። በአውስትራሊያ በተለይ ደግሞ ደቡብ ምስራቁ ክፍል ላይ እየተስተዋለ ያለው ከባድ ሙቀት ከኃይለኛ ንፋስ ጋር ተደማምሮ የሰደድ እሳቱን መቆጣጠር አዳጋች አድርጎታል።

በሲድኒ ኦሎምፒክ ስታዲየም እየተካሄደ ካለውና ለ10 ሰአታት ከሚፈጀው የሚዚቃ ድግስ የሚገኘው ገንዘብ ከተጎጂ ሰዎች በተጨማሪ የአካባቢ ጥበቃና እንስሳትን ለጥፋት ለመታደግ እንደሚውል ይጠበቃል።

Image copyright AFP

የደቡብ አሜሪካ ሃገራትና የአህጉረ-አውስትራሊያ አካል የሆነችው ኒው ዚላንድ በአውስትራሊያ ሰደድ እሣት ምክንያት ሰማያቸው ታፍኖ እንደነበር የሚያሳዩ ፎቶዎች እና ተንቀሳቃሽ ምስሎች የማሕበራዊ ድር-አምባ ተጠቃሚዎች አጋርተዋል።

ኒው ዚላንድን ጨምሮ ሲድኒ፣ ሜልቦርን፣ ካንቤራ እና አደላይድን የመሳሰሉ ትላልቅ የአውስትራሊያ ከተሞች በሰደድ እሣቱ ምክንያት ንፁህ አየር መተንፈስ ተስኗቸው ሰንብተዋል።

አቦርጂናሎች የአውስትራሊያ ጫካ እንዲቃጠል የሚፈልጉት ለምን ይሆን?

የሰደድ እሳቱን ለመቆጣጠር የአውስትራሊያ ጦር ጥሪ ቀረበለት

ለዚህ ሁሉ መከራ መነሻው የሕንድ ውቅያኖስ ዲፖሌ (IOD) ሚቲዮሮሎጂካዊ ክስተት ሲሆን ውቅያኖሱን በሚጎራበቱና በምድር ወገብ አቅራቢያ ባሉ ሀገራት የዝናብ ስልትን ይቀይራል። ይህም ከምስራቅ አፍሪካ እስከ ኢንዶኔዢያ ድረስ የተለጠጠ ሲሆን የአየር ጠባዩ እስከ አውስትራሊያ ድረስ ርቆ ይስተዋላል።

በኢትዮጵያ፣ ኬንያና ታንዛኒያ እና ሌሎች ጎረቤት አገራት ያለማቋረጥ የጣለ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የመሬት መንሸራተት ተከስቶ እስካሁን ድረስ በአጠቃላይ 250 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በሌላ በኩል አውስትራሊያ ደግሞ ድርቅ እና ሰደድ እሳት አስተናግዳለች።