ኡጋንዳ፡ የኩዊን ኦፍ ካትዌ ተዋናይት በ15 አመቷ ህይወቷ አለፈ

ኒኪታ ፐርል ዋሊግዋ Image copyright Disney

ከኡጋንዳ ዝቅተኛ ከሚባለው መንደር ወጥታ ዓለምን ስላስደመመቸው ታዳጊ የቼዝ ተጫዋች ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነው ኩዊን ኦፍ ካትዌ ላይ ተዋናይት የነበረችው የ15 አመቷ ታዳጊ ህይወቷ ከሰሞኑ ማለፉን ሚዲያዎች ዘግበዋል።

ኒኪታ ፐርል ዋሊግዋ በጭንቅላት ዕጢ በሽታ ስትሰቃይ ነበር ተብሏል።

ከአራት አመታት በፊት ለዕይታ የበቃው ይህ ፊልም ፊዮና ሙቴሲ የተባለች ታዳጊ የነበራትን የቼዝ ችሎታ የሚያስቃኝ ነው።

ኢትዮጵያውያን 'የሌሉበት' ስለ ኢትዮጵያ የሚዘክረው ሬድ ሲ ዳይቪንግ ሪዞርት ፊልም

የ'ፍሬንድስ' ፊልም ተዋናዮች እንደገና ቢመለሱስ?

በዘጠኝ አመቷ ቼዝ ጨዋታን የጀመረችው ይህች ታዳጊ ትምህርት ቤት ያልገባች ብትሆንም ዓለም አቀፍ ውድድሮችን አድርጋለች።

ታዋቂዋ ኬንያዊት ተዋናይት ሉፒታ ኒዮንግ የታዳጊዋ እናት ገፀ ባሕርይ ተላብሳ የምትጫወት ሲሆን ሌላኛው ታዋቂ ተዋናይ ዴቪድ ኦየልዎ ደግሞ የቼዝ መምህሯ ሆኖ ተውኗል።

ኒኪታ የፊዮናን ጓደኛ ግሎሪያን ገፀባህርይ ወክላ የተወነች ሲሆን፤ የቼዝንም ህጎች ለመጀመሪያ ጊዜ ያስረዳቻት እሷ ነበረች።

የኢትዮጵያ ፊልም ወዲያና ወዲህ

የዶክተር ዐብይ አሕመድ ፊልም

ከአራት አመታት በፊት የጭንቅላት እጢ እንዳለባት ከታወቀ በኋላ የኩዊን ኦፍ ካትዌ ዳይሬክተር ሚራ ናይር ህንድ ሄዳ እንድትታከምም ገንዘብ የማሰባሰብ ስራ ስትሰራ ነበር።

የኡጋንዳ ዶክተሮች የህክምና ቁሳቁስ የለንም ማለታቸውን ተከትሎ ነበር የውጭ ህክምና ሲፈለግላት የነበረው።

በቀጣዪ ዓመት እጢው ጠፍቷል ብትባልም በባለፈው አመት እንደገና መገኘቱ ተነግሯት ነበር።

ተያያዥ ርዕሶች