በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ውስጥ ስብርባሪ ተገኘ

ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን Image copyright Getty Images

የቦይንግ 737 ማክስ ጀትላይነር አውሮፕላኖች የነዳጅ ቱቦ ውስጥ አላስፈላጊ ስብርባሪ መገኘቱ ተገለጸ። ግኝቱ የአውሮፕላኖቹ አስተማማኝነት ላይ ጥያቄ አስነስቷል።

የቦይንግ 737 ዋና ኃላፊ "ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ነው" ሲሉ ለሠራተኞቻቸው የተናገሩ ሲሆን፤ የቦይንግ ቃል አቀባይ በበኩላቸው የተረፈ ምርቱ መገኘት አውሮፕላኑን ከበረራ አያዘገየውም ብለዋል። 737 ማክስ በያዝነው ዓመት አጋማሽ ላይ ወደ ሥራ ይመለሳል መባሉ ይታወሳል።

የተረፈ ምርቱ መገኘት ይፋ ከመደረጉ በፊት የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች በረራ እንዲያቋርጡ መወሰኑ ይታወሳል። ይህም በኢትዮጵያና በኢንዶኔዥያ አውሮፕላኖቹ ተከስክሰው የብዙዎች ሕይወት መጥፋቱን ተከትሎ የተላለፈ ውሳኔ ነበር።

ቦይንግ "ከእንግዲህ የሚታመን ድርጅት አይደለም"

ተሰንጥቋል የተባለው ቦይንግ 737 አውሮፕላን ከበረራ ታገደ

ለአየር መንገዶች ያልተላለፉ ብዙ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ክንፍ ላይ በሚገኙ የነዳጅ ቱቦዎች ውስጥ አላስፈላጊ ተረፈ ምርቶች ተትተው መገኘታቸውን ድርጅቱ አሳውቋል።

የቦይንግ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ተረፈ ምርቶች (በእንግሊዘኛ Foreign Object Debris (FOD) የሚባሉት) የተገኙት መጋዘን ውስጥ የሚገኙ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ የጥገና ፍተሻ ሲደረግ ነበር።

"ተረፈ ምርቱ መገኘቱን ተከትሎ ምርመራ አድርገናል፤ ማስተካከያም አድርገናል" ብለዋል ቃል አቀባዩ።

ፌደራል አቪየሽን አድሚንስትሬሽን (ኤፍኤኤ)፤ ቦይንግ ስለ ተረፈ ምርቶቹ ጥልቅ ምርመራ እያደረገ መሆኑን እንደሚያውቅ ለቢቢሲ ተናግሯል።

ተረፈ ምርቶች ስንል አውሮፕላኑ በሚገጣጠምበት ወቅት ሠራተኞች የረሷቸው የብረት ቁርጥራጮች ወይም ሌላ አላስፈላጊ ቁሶችን የሚያካትት ሲሆን፤ በአንድ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ ይሸጥ የነበረው 737 ማክስ ባለፉት ጊዜያት የገጠሙት እክሎች ላይ የሚደመር መሰናክል ነው።

ቦይንግ ትርፋማነቴ ቀንሷል አለ

የቦይንግ 737 ማክስ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን?

737 ማክስ ባለፉት ሁለት ዓመታት

  • ጥቅምት 292018: የኢንዶኔዥያው ላየን ኤር 737 ማክስ 8 ተከስክሶ 189 ሰዎች ሞቱ።
  • ጥር 312019: ቦይንግ 79 ደንበኞቹ 5,011 የሚሆኑ ማክስ አውሮፕላኖችን እንዳዘዙት አሳወቀ።
  • መጋቢት 102019: የኢትዯጵያ አየር መንገዱ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ተከስክሶ 157 ሰዎች ሞቱ።
  • መጋቢት 142019: ቦይንግ ሁሉንም 737 ማክስ አውሮፕላኖች ከበረራ አገደ።