በአሜሪካና ካናዳ ድንበር ላይ የሰው አንጎል ተገኘ

በአሜሪካ ድንበር ላይ የተገኘው የሰው አንጎል Image copyright Courtesy US Customs and Border Protection
አጭር የምስል መግለጫ በአሜሪካ ድንበር ላይ የተገኘው የሰው አንጎል

የአሜሪካ ጉምሩክ ኃላፊዎች በካናዳ ፖስታ አመላላዥ መኪና ውስጥ የሰው አንጎል ማግኘታቸውን ገለጹ።

ሰፋ ባለ ጠርሙስ ውስጥ የተቀመጠው አንጎል የተገኘው በአሜሪካዋ ሚችጋን እና በካናዳዋን ቶሮንቶ መካከል በሚገኘው ብሉ ዋተር በተባለ ድልድይ ነው።

ጠርሙሱ የተገኘው "Antique Teaching Specimen" (የጥንታዊ አስተምሮ ናሙና) የሚል መግለጫ ተጽፎበት ሲሆን፤ መነሻውን ቶሮንቶ አድርጎ ወደ ዊስኮንሰን እንዲደረስ የተላከ ነበር።

የጉምሩኩ ኃላፊዎች እንደተናገሩት፤ ስለ ጠርሙሱ ባለቤት እንዲሁም አንጎሉ ወደ አሜሪካ እንዲገባ የተፈቀደበትን ሰነድ አላገኙም።

የ 'ኮፒ ፔስት' ፈጣሪ ሞተ

ፓስፖርት፡ የሰዎችን እንቅስቃሴ የወሰነ ሰነድ

ኬንያዊውን ገርፈዋል የተባሉት ቻይናውያን አሰሪዎች ከሃገር እንዳይባረሩ ፍርድ ቤቱ አዘዘ

የጉምሩኩ ዳይሬክተር ማይክል ፎክስ "የአሜሪካ የማኅበረሰብ ጤና ተቋም እና የበሽታ ቁጥጥር ድርጅትም እንዲህ አይነት ነገሮች እንዳይዘዋወሩ የሚከለክል ጥብቅ ሕግ አላቸው" ብለዋል።

የአሜሪካ ጉምሩክ ኃላፊዎች ድንበር ላይ እንግዳ ነገር ሲይዙ ይህ የሰው አንጎል የመጀመሪያቸው አይደለም።

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2014 የሎስ አንጀለስ አውሮፕላን ማረፊያ ሠራተኞች ከናይጄሪያ ወደ ካሊፎርንያ የተላኩ 67 ቀንድ አውጣዎች አግኝተው ነበር። 2006 ላይ ደግሞ የዳይኖሰር እንቁላልን ጨምሮ ስምንት ቶን ጥንታዊ ቅሪተ አካል ተይዞ ነበር።

ቅሪተ አካሉ ከአርጀንቲና ወደ አሪዞና የተላከ መሆኑ ይታማናል።

ተያያዥ ርዕሶች