ኮሮናቫይረስ፡ ጣልያን ቫይረሱ የተገኘባቸው አካባቢዎች ዘጋች

ሆስፒታል የሚጠብቁ ፖሊሶች Image copyright EPA

ጣልያን ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ 'እጅግ ጥንቃቄ የተሞላበት' የተባለው እርምጃ መውሰድ መጀመሯ ተዘግቧል። በአውሮፓ ትልቁ በተባለው ወረርሽኝ ስጋት የገባት ጣልያን ኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው አካባቢዎችን ሙሉ በሙሉ መዝጋት ጀምራለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ጉሴፔ ኮንቴ ድንገተኛ ጊዜ እቅዳቸውን ቅዳሜ ዕለት ይፋ ባደረጉበት ወቅት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 79 ከፍ ብሎ ነበር ተብሏል።

ጣልያን ይህንን ውሳኔ ለማስተላለፍ የተገደደችው ሁለት ዜጎቿ በቫይረሱ ተይዘው ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ ነው።

በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በአንድ ቀን ውስጥ በእጥፍ ጨመረ

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝና የአየር መንገዶች የገቢ ማሽቆለቆል ስጋት

በሽታውን ለመደበቅ ባለስልጣናት ዶክተሮችን ያስፈራሩ ነበር

ከአስር በላይ የሚሆኑ በሰሜናዊ ሎምባርዲ እና ቬኔቶ ግዛቶች የሚገኙ ከተሞች በፍጥነት እንዲዘጉና ሰዎች በቀላሉ መውጣትና መግባት እንዲቆምም ተደርጓል።

በሁለቱ ሰሜናዊ ግዛቶች የሚገኙ እስከ 50 ሺ ሚደርሱ ዜጎች ከማንኛውም አይነት እንቅስቃሴ እንዲቆጠቡና ከቤታቸው እንዳይወጡ ተጠይቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳስታወቁት የተለየ ፈቃድ ካላቸው ሰዎች ውጪ ከከተሞቹ መውጣትም ሆነ መግባት የከተለከለ ነው።

በከተሞቹ የሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶችና የስፖርት ማዘውተሪያዎችም እንዲቋረጡ የተወሰነ ሲሆን ዛሬ ሊደረጉ የነበሩ የጣልያን ሴሪ አ ጨዋታዎችም በዚሁ ምክንያት እንደማይካሄዱ ታውቋል።

ፖሊስ አስፈላጊ ከሆነ ደግሞ መከላከያ ኃይሉ የወጡትን ደንቦች የማስከበር ግዴታ አለባቸውም ተብሏል።

ተያያዥ ርዕሶች