ቢቢሲ የኮምላ ዱሞር 2020 ሽልማትን ይፋ አደረገ

Komla Dumor

ቢቢሲ ለስድስተኛ ዙር በቀድሞው ጋዜጠኛ ኮምላ ዱሞር ስም አፍሪካውያን ጋዜጠኞችን አወዳድሮ ሊሸልም ነው።

ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞችን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት በጋዜጠኝነት ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች በውድድሩ ላይ እንዲሳተፉ ግብዣ ቀርቧል።

አፍሪካውያን ጋዜጠኞች በውድድሩ እንዲሳተፉ የተጋበዙ ሲሆን፤ ይህ ሽልማት አዲስ ተሰጥኦ ያላቸውን ጋዜጠኞች ለማስተዋወቅ እና ክህሎትን ለማዳበር ያለመ ነው።

አሸናፊ የሚሆነው/የምትሆነው አፍሪካዊ ጋዜጠኛ ለንበደን በሚገኘው ቢቢሲ ስቱዲዮ ለሦስት ወራት በመስራት የጋዜጠኝነት ክህሎትና እና ልምድ እንዲያዳብሩ ይረዳል።

የኮምላ ዱሞር ሽልማት መጋቢት 11/2012 ይጠናቀቃል።

የውድድሩ መስፈርት ለመመልከት እና የውድድሩ ተሳታፊ ለመሆን ይህን ይጫኑ

የውድድሩ አሸናፊ በለንድን በቢቢሲ ዋና ቢሮ የመስራት እድል ከማግኘቱም በተጨማሪ፤ ወደ አፍሪካ በመጓዝ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የመዘገብ ዕድል ያገኛል።

ይህ ዓመታዊ ውድድር ይፋ የተደረገው የቢቢሲ ጋዜጠኛ የነበረውን ጋናዊውን ኮምላ ዱሞርን ለመዘከር ነው።

ኮምላ ዱሞር እአአ 2014 ላይ በድንገት ነበር በ41 ዓመቱ ህይወቱ ያለፈችው።

ከዚህ ቀደም የኮምላ ሞር ሽልማት አሸናፊዎች፡

  • 2015: ናንሲ ካቹንጊራ ከኡጋንዳ
  • 2016: ዲዲ አኪንዩሉሬ ከናይጄሪያ
  • 2017: አሚና ዩጉዳ ከናይጄሪያ
  • 2018: ዋኢሂጋ ሙዓኡራ ከኬንያ
  • 2019: ሶሎሞን ሴርዋንጃ ከኡጋንዳ