ሴቶች ስታዲየም እንዲገቡ በቅርቡ የፈቀደችው ሳዑዲ የሴቶች ሊግን ልታስጀምር ነው

Saudi families cheer at the King Abdullah Sports City known as "a radiant jewel" to attend the Saudi Football League soccer match Al Ahly and Al-Batin in Jeddah, Saudi Arabia, 12 January 2018.

የፎቶው ባለመብት, EPA

ሴቶች ስታዲየም ገብትው ኳስ እንዳይመለከቱ ትከለክል የነበረችው ሳዑዲ አራቢያ የሴቶች የእግር ኳስ ሊግን ልታስጀምር ነው።

በሊጉ የሚሳተፉ ቡድኖች በመዲናዋ ሪያድ እና በሌሎች ሁለት ከተሞች ውድድሮችን ያካሂዳሉ።

አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማን በሳዑዲ እያካሄዱ ካለው የለውጥ እርምጃ መካከል ይህ ውሳኔ ተጠቃሽ ነው።

የሰብዓ መብት ተሟጋቾች ግን አሁንም በሳዑዲ የሴቶች መብት ላይ ገደብ ተጥሏል ይላሉ።

ባለስልጣናት የሴቶች የእግር ኳስ ሊግን ማቋቋም ያስፈለገው ሴቶች በስፖርት ያላቸው ተሳትፎ ለማሳዳግ ነው ብለዋል።

ሴቶች ስታዲየም ገብትው እግር ኳስ እንዲመለከቱ የተፈቀደላቸው የዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ነበር። በተመሳሳይ ዓመት ሳዑዲ ሴቶች መኪና ማሽከርከር አይችሉም የሚለውን ክልከላዋን አስቁማለች።

ባሳለፍነው ዓመት ደግሞ ሴቶች ያለ ወንድ ጥበቃ ከአገር ውጪ ጉዞ ማድረግ እንዲችሉ እንደተፈቀደላቸው ይታወሳል።

ይህ ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን በርካታ የሴቶች መብት ተከራካሪዎች በሳዑዲ እስር ቤቶች ውስጥ እየማቀቁ ይገኛሉ።