ልዑልነት ይቅርብኝ ያለው የእንግሊዙ ልዑል 'ሃሪ ብቻ ብላችሁ ጥሩኝ' እያለ ነው.

ልዑል ሄሪ Image copyright PA Media

የሰሴክስ ልዑሉ ሃሪ ለጋዜጠኞች "ሃሪ ብቻ ብላችሁ ጥሩኝ" ሲል ተናገረ።

ልዑሉ ይህን ያሉት በቱሪዝም ጉዳይ ላይ በስኮትላንድ መዲና ኤደንብራህ እየተሰጠ በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

ከሳምንታት በኋላ የንግስቷ የልጅ ልጅ እና ባለቤቱ ሜጋን ከንጉሳዊ ስርዓት ሙሉ በሙሉ ኃላፊነት ይገለላሉ።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ልዑል ሃሪ የቱሪዝም እና የጉብኚዎች ቁጥር በፍጥነት ማደግ ውብ ለሆኑ የዓለማችን መተኪያ የሌላቸው ቅርሶች አደጋን ደቅኗል ብሏል።

ልዑል ሃሪ በፍጥነት አስፈላጊው እርምጃ ካልተወሰደ መተኪያ የሌላቸው የዓለማችን መዳረሻዎች ይወድማሉ ወይም ይዘጋሉ ይላል።

ልዑል ሃሪ ከንጉሳዊ ስርዓት ኃላፊነቱ ከመገለሉ በፊት ከሚከውናቸው የመጨረሻ ኃላፊነቶች መካከል አንዱ ወደ ስኮትላንድ የወሰደው የቱሪዝም ጉዳይ አንዱ ነው።

ልዑል ሃሪ እና ባለቤቱ ሜጋን ህወታቸውን በሰሜን አሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም እንደሚያደርጉ እና የንጉሳዊው ስርዓት ከሚጠይቀው ኃላፊነት እራሳቸውን እንደሚያገሉ ማሳወቃቸው ይታወሳል።

ከሁለት ዓመት በፊት ልዑል ሃሪ በወቅቱ እጮኛው ከነበረችው ሜጋን ጋር አሁን ወዳቀናበት ኤደንብራ በሄደ ጊዜ በርካቶች አደባባይ ወጥተው ፍቅራቸውን በመግለጽ አቀባበል አድረገውላቸው ነበር።

ከሁለት ዓመት በኋላ ልዑሉ በተመሳሳይ ሥፍራ በተገኘበት ወቅት ግን የጠበቀው ድባብ የተለየ ነው። ሜጋን አብራው አልነበረችውም፤ እሱን ለመቀበል የወጣው ሰው ቁጥርም በጣም አነስተኛ ነበር።

ልዑል ሃሪ ከትናንት በስቲያ ኤደንብራህ ባቡር ጣቢያ ሲደርስ ባርኔጣውን አድርጎ፣ ጄንስ ሱሪ ታጥቆ እና ቦርሳውን በጀርባ አዝሎ ነበር።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ