ማርች 8፡ የዓለም የሴቶች ቀንን ማንና የት ጀመረው?

An International Women's Day demonstration in Diyarbakir, Turkey in 2016

የፎቶው ባለመብት, AFP

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በተመለከተ ከመገናኛ ብዙኃን አለያም ከወዳጅ ሰምተው ይሆናል። ፅንሰ ሐሳቡ ምን ይሆን? መቼ ይከበራል? በዓል ወይስ የተቃውሞ ቀን?

በተመሳሳይስ ዓለማቀፍ የወንዶች ቀንስ ይኖር ይሆን ? ዓለም አቀፋ የሴቶች ቀን በየዓመቱ መጋቢት ስምንት መከበር ከጀመረ ዘመናትን አስቆጥሯል፤ ለተጨማሪ መረጃዎች አብረውን ይዝለቁ፦

ታሪካዊ ዳራ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን የአመፅ እንቅስቃሴን መነሻ በማድረግ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዘንድ እውቅናን ለማግኘት የበቃ በዓል ነው::

ወቅቱ እንደ አውሮፓውያኑ 1908 ነበር በኒውዮርክ ከተማ ነዋሪ የሆኑ 15,000 ሴቶች የተሻሻለ የሥራ ሰዓትና የደመወዝ ክፍያን እንዲሁም የመምረጥ መብታቸው እንዲከበር አደባባይ የወጡት።

ከአንድ ዓመት በኋላም የአሜሪካ ማኅበራዊ ፓርቲ ዕለቱን የሴቶች ብሔራዊ ቀን በማለት አውጆታል።

ክላራ ዚክተን በተባለች ሴት አማካኝነት ደግሞ በዓሉ ዓለማቀፋዊ ቅርፅን እንዲይዝ በ1910 ላይ በዴንማርክ ዋና ከተማ ኮፐንሀገን በተካሔደው ዓለማቀፋዊ የሠራተኛ ሴቶች ኮንፍረስ ላይ ሐሳቡ ቀረበ።

ከአስራ ሰባት ሀገራት የተውጣጡ መቶ ተሳታፊ ሴቶች ሀሳቡን በጄ አሉት። ይህንንም ተከትሎ ኦስትርያ ዴንማርክ ጀርመንና ስዊዘርላንድ በዓሉን በ1911 በማክበር ፈር ቀዳጅ ሆኑ።

ባለፈው የፈረንጆች 2011 ይሄው በዓል ለመቶኛ ጊዜ የተከበረ ሲሆን በዚህ ዓመት ሲታሰብ ደግሞ ለ109ኛ ጊዜ ነው ማለት ይሆናል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሴቶች ቀንን በ 1975 በይፋ ሲያከብር በዓሉ ዓለማቀፋዊ ይዘት ሊኖረው ችሏል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞም በ1996 ተ.መ.ድ "ያለፈውን በማሰብ የወደፊቱን እናቅድ " የሚል መሪ ቃል ይዞ ተከብሯል።

በዚህ ዓመት ደግሞ " እኩልነት የሰፈነባት ዓለም ሁሉን ማድረግ ትችላለች " በሚል የሚከበር ሲሆን ለፆታዊ እኩልነት ህዝቦች በጋራ ተሳስበው እንዲሰሩ የሚያሳስብ ነው።

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ሴቶች በማኅበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት የተጓዙትን ጉዞም ያስታውሳል።

መቼ ይከበራል? ዛሬ ላይ በዓሉ መጋቢት በባጀ በ8ኛው ቀን ይከበራል። ይሁን እንጂ ክላራ በተባለቺው ሴት አማካኝነት ሐሳቡ ሲጠነሰስ የተቀመጠለት ቋሚ ቀን አልነበረም።

የሩሲያ ሴቶች በ1917 "ዳቦና ሰላም " በማለት ያነሱት የተቃውሞ እንቅስቃሴ የበለጠ ቅርፅ እንዲይዝ አድርጎታል።

ይሄው ለአራት ቀናት የዘለቀው አመፅ በጁላዊያኑ የዘመን አቆጣጠር ዕሑድ የካቲት 23 የሩሲያውን ቄሳር የሴቶችን የመምረጥ መብት እንዲፈቅድ ያስገደደ ሲሆን በመንግሥት አስተዳደር ደግሞ እውቅና እንዲሰጥ ሆኗል ይህ እንግዲህ በጎርጎሳውያኑ የዘመን አቆጣጠር መጋቢት 8 መሆኑ ነው።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ለማቀፍ የወንዶች ቀን በ 1990ዎቹ እውቅናን ካገኘበት ዕለት ጀምሮ በየዓመቱ ህዳር 19 ይከበራል፤ ምንም እንኳን እስካሁን ድረስ በተመድ እውቅናን ያላገኘ ቢሆንም ታላቋን ብሪታኒያ ጨምሮ ከ60 አገሮች በላይ የሚያከብሩት ሲሆን አላማውም "የጎልማሶችና የህፃናት ወንዶች ጤንነት" ላይ በማተኮር ፃታዊ ተግባቦትን ለማሻሻል ፆታዊ እኩልነትን ለማስፈንና አርአያ ለሚሆኑ ወንዶች እውቅና መስጠት" ላይ ያተኮረ ነው።

"ጎልማሶችና ህፃናት ወንዶች ላይ ተፅእኖ መፍጠር" የ2019 ዓለም አቀፍ የወንዶች ቀን መሪ ቃል ነበር።

የሴቶች ቀን ለም አቀፍዊ አከባበር እንግዲህ የሴቶች ቀን በብዙ አገሮች ማለት ይቻላል ብሔራዊ በዓል ሲሆን በተለይ በሩሲያ ከዕለቱ ሦስት አራት ቀን ቀደም ብሎ የአበባው ገበያ ይደራል።

በቻይና ደግሞ በመንግሥት አስተዳደር በመፈቀዱ አብዛኛው ሴቶች የግማሽ ቀን ዕረፍት የሚሰጣቸው ቢሆንም በአንፃሩ ደግሞ ይህንን የማያከብሩ ቀጣሪዎችም ቁጥራቸው ቀላል አይደለም።

ወደ ጣሊያን ስንመጣ ደግሞ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ ሴቶች ምሞሳ የተሰኘውን በቢጫና ሮዝ ቀለማት ያሸበረቀ አበባ በገፀ በረከትነት ያገኛሉ። ምክንያቱ በውል ባይታወቅም ይሔው ልማድ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በሮማ እንደተጀመረ ይታመናል።

በአሜሪካ ደግሞ መጋቢት ወር የሴቶች ታሪካዊ ወር ነው፤ የፕሬዝዳንቱ ቢሮም ለሴቶች ስኬትና ድል በየዓመቱ እውቅና ይሰጣል።

የዘንድሮው ለም አቀፍ የሴቶች ቀን "እያንዳንዳችን ለእኩልነት" የሚለውን መሪ ቃል ከፊት በማድረግ ይከበራል። የአብሮነት ህብርን እሳቤ በመመርኮዝ የተመረጠ ነው የበዓሉ ዘመቻም " ሁላችንም ባለ አሻራዎች ነን" ይላል። የእያንዳንዳችን የተናጥል እንቅስቃሴ ባህሪና ሥነ ልቦና በማኅበረሰቡ ዘንድ የሚኖረው ተፅእኖ ቀላል አይደለም።

በዚህ ህብረ ቀለምም ለውጥ ማምጣት እንችላለን፤ በአብሮነት ህብርም ፆታዊ እኩልነት እንዲሰፍን መረዳዳት እንችላለን " በማለት ያትታል።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ይሔው ዓለም አቀፋዊ በዓል ታላቅ የሚባል እምርታ ላይ ደርሷል። ለአብነት በጥቅምት ወር 2017 #እኔም [#metoo] በማለት የሴቶችን ፆታዊ ጥቃትና ትንኮሳ ለመቃወምና ለማውገዝ ሚሊዮኖች በማህበራዊ መገናኛ ገፆች ድምፃቸውን አሰምተዋል።

ይሔው #እኔም እንቅስቃሴ በ2018 አድጎ አለማቀፍዊ ቅርፅ በመያዝ እንደ ህንድ ፈረንሳይና ደቡብ ኮሪያ ያሉ ሀገራት ይህንንኑ ዘመቻ ለለውጥ ተቀላቅለዋል።

በአሜሪካ በሚደረገው የኘሬዝዳንቱ ሥልጣን ዘመን አጋማሽ ምርጫ ላይ የሴቶች ቁጥር ብልጫ የታየበት ነው። በሰሜን አየርላንድም የፅንስ ማቋረጥ ኢህጋዊነት ሲሻር የሱዳን ሴቶች እንዴት መልበስና መንቀሳቀስ እንዳለባቸው የሚደነግገው ህግ ምሊቀየር ችሏል።