የቱሉ ፈራ ቅን ልቦች የአውሮፕላኑን አደጋ አንደኛ ዓመት አሰቡ

የቱሉ ፈራ ቅን ልቦች የአውሮፕላኑን አደጋ አንደኛ ዓመት አሰቡ

ባለፈው ዓመት ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ኬንያ ናይሮቢ ሲበር የነበረና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን የስድስት ደቂቃ በረራ ካደረገ በኋላ ቢሾፍቱ አካባቢ ተከስክሶ የ157 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎም የአካባቢው ነዋሪዎች በደረሰው አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ሐዘናቸውን ከመግለጽ ባለፈ የመታሰቢያ ዝግጅት ድርገውላቸው ነበር።

በተለይ አንዲት እናት ወደ ስፍራው የሚሄዱ የሟች ቤተሰቦችን በማስተናገድና በኋላም ለሟቾች የ40 ቀን መታሰቢያ አድርገው ነበረ። ዘንድሮም እኒሁን እናት ጨምሮ የአካባቢው ነዋሪዎች የአደጋውን አንደኛ ዓመት አስበውታል።