ኮሮናቫይረስ ፡ በየደቂቃው በዓለም ዙሪያ ኮቪድ-19 የሚይዛቸውና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርን የሚያሳይ ካርታ

ኮሮናቫይረስ ምስል

ከቻይናዋ ሁቤይ ግዛት ተነስቶ ሰው ከማይኖርበት አንታርክቲክ ውጪ ሁሉንም የዓለማችንን አህጉራትን ያዳረሰው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአሁኑ ወቅት የምድራችን ዋነኛ የጤና ስጋት ሆኗል።

ኮቪድ-19 በመባል የሚታወቀው ይህ ወረርሽኝ የመተንፈሻ አካልን የሚያጠቃ ሲሆን፤ መጀመሪያ ትኩሳት ቀጥሎም ደረቅ ሳል ከሳምንት በኋላ ደግሞ የትንፋሽ ማጠርን ያስከትላል።

እስካሁን በቫይረሱ ከ141 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የተያዙ ሲሆን ከ3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።

በበሽታው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ከተያዙና ከሞቱ ከአንድ ዓመት በኋላ የተለያዩ አይነት ክትባቶች ተገኝተው ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ለሰዎች እየተሰጡ ይገኛሉ።

ነገር ግን አሁንም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም፣ የእጅን ንጽህና በተደጋጋሚ መጠበቅና በየትኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ በሽታውን ለመከላከል ዋነኞቹ መንገዶች መሆናቸውን ባለሙያዎች አጥብቀው ይመክራሉ።

በየደቂቃው በዓለም ዙሪያ ባሉ አገራት ውስጥ በኮቪድ-19 የሚያዙ፣ ከበሽታው የሚያገግሙና በቫይረሱ ምክንያት ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎችን አሃዝ ቀጥሎ ከተቀመጠው ዝርዝር ላይ ይመልከቱ።

በአገራት

በዓለም ዙሪያ በበሽታው የተያዙ ሰዎች

Group 4

ሙሉውን ለመመልከት እባክዎን ብሮውዘርዎን ያሻሽሉ

ምንጭ፡ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ፣ ብሔራዊ የኅብረተሰብ ጤና ተቋማት

አሃዞቹ በመጨረሻ የተሻሻሉት 16 ኤፕሪል 2021 12:25 ከሰዓት ጂ ኤም ቲ+4

የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ምንድናቸው?

የኮሮናቫይረስ ሁለት ዋነኛ ምልክቶች ከፍተኛ ትኩሳትና ደረቅ ሳል ናቸው። በአንዳንድ ታማሚዎች ላይ እነዚህ ምልክቶች ወደ ትንፋሽ ማጠር ይወስዳሉ። ደረቅ ሳል ሲባል በጣም ጠንካራ የሆነ አንዳንድ ጊዜ ለአንድ ሰዓት የሚቆይ ነው። ከዚህ በፊት ደረቅ ሳል ካለብዎ የኮሮናቫይረስ ሳል በጣም ለየት ያለና ከባድ መሆኑን ማስተዋል ይችላሉ።

ከፍተኛ ትኩሳት የሚባለው ደግሞ የሰውነት ሙቀት መጠን ከ37.8 ዲግሪ ሴልሲየስ ሲልቅ ነው። ይህ ትኩሳት ሰውነት እንዲግል ወይም ደግሞ ከፍተኛ ብርድና መንቀጥቀጥ እንዲሰማን ያደርጋል።

ከእነዚህ ሁለቱ ዋነኛ ስሜቶች ባለፈ ራስ ምታትና ተቅማጥ አንዳንድ የበሽታው ታማሚዎች ያሳይዋቸው ምልክቶች ናቸው። የማሽተትና የመቅመስ አቅም ማጣትም ምልክቶች ሆነው ተመዝግበዋል።

ምልክቶቹ ቫይረስ ሰውነት ውስጥ በገባ በአምስት ቀናት ሊታዩ ይችላሉ። የዓለም ጤና ድርጅት ዘገባ ምልክቶቹ እስከ 14 ቀናት ድረስ ሳይታዩ ሊቆዩ እንደሚችሉ ያስረዳል።

ዝርዝር መረጃ

ተጨማሪ ለማየት ሰንጠረዡን ያንሸራቱ

*ከ100,000 ሰዎች መካከል የሞት

ዩኤስ አሜሪካ 564848 172.7 31536085
ብራዚል 373335 178.2 13943071
ሜክሲኮ 212339 168.3 2305602
ህንድ 178769 13.2 15061805
ዩናይትድ ኪንግደም 127270 189.6 4387820
ጣሊያን 116927 192.9 3870131
ሩሲያ 103834 71.2 4649044
ፈረንሳይ 100733 155.0 5289526
ጀርመን 80052 96.3 3155522
ስፔን 76981 164.9 3407283
ኮሎምቢያ 68328 137.6 2652947
ኢራን 66732 81.6 2237089
ፖላንድ 62032 163.6 2688025
አርጀንቲና 59228 133.5 2694014
ፔሩ 57230 178.9 1704757
ደቡብ አፍሪካ 53736 93.0 1566769
ኢዶኔዢያ 43424 16.2 1604348
ዩክሬን 41748 94.4 2006073
ቱርክ 35926 43.6 4268447
ቼክ ሪፐብሊክ 28532 267.5 1602711
ሮማኒያ 26232 134.5 1029304
ሃንጋሪ 25184 259.4 750508
ቺሊ 25177 134.4 1124718
ቤልጂየም 23747 206.8 949996
ካናዳ 23611 63.7 1129371
ኢኳዶር 17703 103.6 360546
ፖርቱጋል 16945 165.2 831001
ኔዘርላንድስ 16919 99.2 1404029
ፓኪስታን 16316 7.7 761437
ፊሊፒንስ 15960 15.0 936133
ቡልጋሪያ 15195 215.5 386381
ኢራቅ 14981 39.0 977175
ስዊዲን 13788 138.3 900138
ግብጽ 12738 12.9 216334
ቦሊቪያ 12648 111.4 289066
ስሎቫኪያ 11106 203.7 375974
ስዊትዘርላንድ 10510 123.3 632399
ባንግላዲሽ 10385 6.4 718950
ኦስትሪያ 9898 111.3 593423
ቱኒዚያ 9783 84.6 285490
ጃፓን 9612 7.6 535747
ግሪክ 9462 89.9 315273
ሞሮኮ 8945 24.8 505811
ዮርዳኖስ 8246 82.7 685973
ቦስኒያ እና ሄርዜጎቪና 7788 234.3 188994
ጓቲማላ 7221 41.9 212734
ሌባኖስ 6925 101.0 510403
ሳኡዲ አረቢያ 6823 20.2 404970
ክሮሺያ 6562 157.9 307790
እስራኤል 6338 75.6 837160
ፓናማ 6188 148.1 360841
ሰርቢያ 5991 85.8 662368
ሞልዶቫ 5571 137.5 245897
ፓራጓይ 5313 76.4 250165
ሆንዱራስ 4957 51.7 200935
ቻይና 4845 0.3 102242
አየርላንድ 4836 100.4 243508
ሰሜን መቂዶኒያ 4443 213.3 147094
ስሎቬኒያ 4159 200.2 232071
አዘርባጃን 4140 41.6 300666
ጆርጂያ 3939 98.4 295358
አርሜኒያ 3878 131.4 208520
ሊቱዋንያ 3770 134.6 234232
ዶሚኒካን ሪፐብሊክ 3418 32.2 261129
ኢትዮጵያ 3370 3.1 242028
ካዛክስታን 3291 18.0 341599
ምያንማር 3206 6.0 142628
አልጄሪያ 3155 7.5 119642
ኔፓል 3083 11.0 284673
ኮስታ ሪካ 3071 61.4 228577
የፍልስጥኤም ግዛቶች 3017 62.0 280741
ሊቢያ 2896 43.4 171880
አፍጋኒስታን 2539 6.8 57793
ኬንያ 2481 4.8 151653
ዴንማርክ 2455 42.7 242633
ቤላሩስ 2423 25.6 344223
አልባኒያ 2342 81.2 129594
ሱዳን 2208 5.3 33022
ኮሶቮ 2080 112.7 101191
ኤል ሳልቫዶር 2078 32.4 67557
ናይጄሪያ 2061 1.1 164233
ላትቪያ 2053 106.5 111334
ኡራጓይ 1908 55.3 164744
ቬንዙዌላ 1905 6.6 183190
ኦማን 1878 38.9 180031
ደቡብ ኮሪያ 1801 3.5 114646
ኪርጊዝስታን 1555 24.7 92095
የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች 1554 16.1 497154
ዚምባብዌ 1553 10.8 37751
ኩዌት 1448 35.0 256987
ሶሪያ 1446 8.5 21142
ሞንቴኔግሮ 1429 227.6 95551
ማሌዢያ 1378 4.4 375054
ዛምቢያ 1235 7.1 90918
ማላዊ 1138 6.3 33941
የመን 1126 4.0 5812
ኢስቶኒያ 1092 82.5 117554
ሴኔጋል 1091 6.9 39782
ካሜሩን 939 3.7 64809
አውስትራሊያ 910 3.7 29543
ፊንላንድ 887 16.1 84131
ሞዛምቢክ 798 2.7 69203
ሉክሰበርግ 785 129.9 64746
ጋና 771 2.6 91709
የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ 745 0.9 28956
ጃማይካ 723 24.6 43890
ኖርዌይ 708 13.3 107510
ቦትስዋና 671 29.8 44075
ኢስዋቲኒ 671 59.1 18417
ሶማሊያ 670 4.5 13079
ኡዝቤክስታን 638 2.0 86982
ስሪላንካ 618 2.9 96796
ናሚቢያ 604 24.7 46655
ባህሬን 594 37.8 164110
አንጎላ 561 1.8 24389
ማዳጋስካር 542 2.1 32205
ኩባ 525 4.6 93511
ሞሪታኒያ 453 10.3 18129
ማሊ 433 2.3 13070
ማልታ 409 93.1 29966
ኳታር 382 13.7 196580
ኡጋንዳ 338 0.8 41378
ሩዋንዳ 325 2.6 23888
ቤሊዜ 318 83.0 12538
ሌሶቶ 315 14.9 10709
ቆጵሮስ 291 24.5 56259
አይቮሪ ኮስት 274 1.1 45560
ጉያና 271 34.8 11863
ሄይቲ 251 2.3 12918
ጓድሉፕ 194 48.5 12927
ባሃማስ 194 50.3 9634
ኬፕ ቨርዲ 192 35.3 20466
ኒጀር 190 0.8 5131
ሱሪናም 187 32.5 9581
ኒካራጓ 180 2.8 6778
ጋምቢያ 170 7.5 5720
ቻድ 169 1.1 4706
ማያቴ 168 64.7 19789
ቡርኪና ፋሶ 154 0.8 13129
ትሪንዳድ እና ቶቤጎ 153 11.0 8940
ኮሞሮስ 146 17.5 3819
ፍሬንች ፖሊኔዢያ 141 50.8 18696