ስለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምን ያህል ልንሰጋ ይገባል?

በመስኮት ወደ ውጪ የምትመለከት ሴት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ኮሮናቫይረስ የማይታይ ገዳይ በሽታ እንደሆነ ተደጋግሞ ይገለጻል። ለመሆኑ በሽታው ከዚህ በላይ ምን ያህል አስከፊ ነው?

ቫይረሱ የማይታይ፣ ከያዘንም እስካሁን በሳይንስ የተረጋገጠ ክትባትም ሆነ መድኃኒት አልተገኘለትም።

በመሆኑም በርካታ ሰዎች ከቤት ለመውጣት፣ ወደ መደበኛ ሕይወታቸው ለመመለስ፣ ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት ለመላክ ቢሰጉ ምንም የሚደንቅ አይደለም።

ምክንያቱም ሁሉም ሰው ደህና መሆን ይፈልጋል፤ ነገር ግን ከዚህ ቀደም እንደነበረው ሕይወታችን ደኅንነታችን የተጠበቀ አይደለም።

ቫይረሱ ከሚያሳድረው የጤና አደጋ ባሻገርም፤ ተያያዥ የሆኑ ከፍተኛ ቀውሶችን አስከትሏል።

ለበሽታው ያለንን ተጋላጭነት እንዴት ልንቀንስ እንችላለን?

ይህ ጥያቄ የብዙዎች ጭንቀት ነው። ታዲያ ይህንን ለማድረግ ምን ማድረግ ይኖርብናል?

አንዳንድ ሰዎች እርግጠኛ እስኪኮን ድረስ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የተጣሉ ገደቦች ሊቀጥሉ ይገባል ይላሉ፤ ነገር ግን ገደቦቹ በራሳቸው አደጋ መሆናቸውን ከግምት ያስገቡ አይደሉም።

የዩናይትድ ኪንግደም የህክምና አማካሪ ፕሮፌሰር ክሪስ ዊቲይ ይህንን ተያያዥ ቀውስ "የወረርሽኙ ቀጥተኛ ያልሆነ አደጋ" ሲሉ ይገልጹታል።

ይህንን ለማስቀረት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የተጣሉ ገደቦች በላሉ መጠን፤ ግለሰቦች እንዲሁም ጠቅላላ ማኅበረሰቡ የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ሚዛናዊ ለማድረግ ውሳኔ ማሳለፍ አለባቸው።

ሙሉ በሙሉ ደንነት የማይሰማን ለምንድን ነው?

ይህንን ስሜት ብዙዎች ይጋሩታል።

በኤደንብራ ዩኒቨርሲቲ የዓለም ሕብረተሰብ ጤና ኃላፊ ፕሮፌሰር ዲቪ ስሪዲሃር፤ ይህን ጥያቄ ለመመለስ ልንጠይቅ የሚገባው ጥያቄ ምን ያህል ደኅንነታችን ተጠብቋል? የሚለው ነው ይላሉ።

"ወደፊትም ቢሆን አደጋ የማይኖርበት ምክንያት የለም" የሚሉት ፕሮፌሰሯ፤ ማሰብ ያለብን ልክ በዕለት ተዕለት እንደሚያጋጥሙን የመኪና ወይም የብስክሌት አደጋዎች ሁሉ ኮቪድ-19 በማኅበረሰቡ በሚቆይበት ዓለም ውስጥ አደጋውን እንዴት ልንቀንስ እንደምንችል መሆኑን ይገልጻሉ።

ይህም መንግሥት ወረርሽኑን ለመቆጣጠር አካላዊ ርቀትን መጠበቅ፣ የቫይረሱን መከላከያ መሳሪዎች አቅርቦት፣ በምርመራ መጠን እና ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የመከታተል እርምጃዎች ይወስናል ብለዋል።

አሁን አሁን በርካታ ገደቦች እየተነሱ ስለሆነ ለወደፊቱ ግለሰቦች የሚደርሱበት ውሳኔ ውሳኔና የሚወስዱት እርምጃ ሚናው ወሳኝ ነው።

ምን አልባት ውሳኔው ትክክለኛ አማራጭ የመፈለግ ጉዳይ ሳይሆን የመጨረሻውን አስከፊ አማራጭ የመፈለግ ጉዳይም ሊሆን ይችላል።

በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የአደጋ ስጋት ምሁር እና የመንግሥት አማካሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ዴቪድ ስፔንግልሃልተር በበኩላቸው፤ "አደጋውን በተገቢው መንገድ የመቆጣጠር ጉዳይ ጨዋታ ሆኗል" ይላሉ። በዚህም ምክንያት "እኛ እያጋጠመን ባለው የፈተና መጠንን መቆጣጠር እንፈልጋለን" ብለዋል።

ይሁን እንጂ በአደጋው ላይ ጫና ያሳደሩብን ሁለት ምክንያቶች አሉ ይላሉ ፕሮፌሰሩ። አንደኛው በቫይረሱ እንዳንያዝ ሲሆን አንዴ ከተያዝን በኋላ ደግሞ የመሞት አሊያም በጠና መታመም ሌላኛው ነው።

በሆስፒታል አሊያም በእንክብካቤ ማዕከላት ካልሆንን በስተቀር ለበሽታው ያለን ተጋላጭነትን የሚያሳየው መመሪያ የሚመጣው በብሔራዊ ስታስቲክስ መሥሪያ ቤት ከሚካሄደው የመንግሥት ክትትል ፕሮግራም ነው።

ሰሞኑን የወጣው አንድ መረጃ እንደሚያሳየውም ከ400 ሰዎች አንዱ በቫይረሱ ይያዛል።

ይህም በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ያለን የመገናኘት እድልን ከወሰንን፣ አካላዊ ርቀትን ከጠበቅን፤ የመያዝ ዕድሉ በጣም ጠባብ እንደሆነ ያሳያል።

በመሆኑም መንግሥት ቫይረሱን ለመግታት ምርመራዎችን ካካሄደ፣ ቫይረሱን ለመቆጣጠር የሚካሄዱ ፕሮግራሞች ላይ ክትትል ካደረገ፣ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ሊቀንስ እንደሚችል ተስፋ ይሰጣል።

አብዛኞቹ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የሚያጋጥማቸውም ከቀላል እስከ መካከለኛ ህመም ነው። በሆስፒታል የህክምና ክትትል የሚያስፈልገው ምልክት የሚያሳየው ከ20 ሰዎች መካከል አንዱ ነው።

ለበሽታው ያለንን ተጋላጭነት እንዴት ልናውቅ እንችላለን?

ከዚህ ቀደም ሲል የቆየ የጤና እክል ያለባቸው ሰዎች ለበሽታው የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው። ከ65 ዓመት በታች እድሜ ላይ የሚገኙ ሰዎች ያለህመም መሞታቸው የተለመደ አለመሆኑን አንድ ጥናት አመልክቷል።

ምን አልባት ቀላሉ መንገድ የሚሆነው በሚቀጥሉት 12 ወራት መሞትን በተመለከተ ምን ያህል እንደምትጨነቁ ራሳችሁን መጠየቅ ነው።

ከ20 ዓመት በላይ ከሆን በበሽታው የመያዝ እድላችን ለመጪዎቹ ወራት ያለን የመሞት እድል ነጸብራቅ ነው።

ለምሳሌ 40 ዓመት የሆነው ሰው፤ በአማካይ በአንድ ዓመት ውስጥ ከአንድ ሺህ ሰዎች መካከል አንዱ የመሞት እድል አለው። በተመሳሳይ ከኮሮናቫይረስ የመዳን እድልም አይኖረውም።

ይህም በአማካይ ለበሽታው ያለንን ተጋላጭነት የሚያሳይ ነው፤ ነገር ግን የሞት አደጋው በማንኛውም የእድሜ ክልል የሚገኙና የጤና እክል ባለባቸው ሰዎች ስለተያዘ፤ አብዛኛው ሰው ለበሽታው የመጋለጥ እድሉ ዝቅተኛ ነው።

ህጻናት ከኮሮናቫይረስ ይልቅ እንደ ካንሰርና አደጋ ባሉ ሌሎች ምክንያቶች ለሞት የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ ነው።

በወረርሽኙ ወቅት በቫይረሱ የሞቱት ከ15 ዓመት በታች ያሉ ህጻናት ሦስት ናቸው፤ ይህም በየዓመቱ በመኪና አደጋ ከሚሞቱ 50 ህጻናት ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ ቁጥር ነው።

ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑትን መለየት

ሁላችንም ለበሽታው ካለን ተጋላጭነት አንጻር ራሳችንን ለመጠበቅ ልብ ልንለው የሚገባው ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑትን መለየትን ነው።

በአሁኑ ጊዜ ባለስልጣናትና የጤና ባለሙያዎች ብዙ ሰዎችን ራሳቸውን እንዲያገሉ እየጠየቁ ነው። እነዚህ ሰዎች ሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎች ያሉባቸውንም ያካትታል።

ከዚህም በተጨማሪ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ለበሽታው በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ ናቸው ተብለው ተለይተዋል። እነዚህም ከ70 ዓመት በላይ የሆኑትንና የስኳርና የልብ ሕመም ችግር ያለባቸውን የያዘ ነው።

በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በእድሜ መግፋት ዙሪያ ባለሙያ የሆኑት ፕሮፌሰር ሳራ ሃርበር "የተሸፋፈነና የዘፈቀደ የእድሜ አጠቃቀምን" በተመለከተ ያሳሰቡ ሲሆን፤ ለበሽታው የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን በጥንቃቄ መመልከት እንደሚያስፈልግ መክረዋል።