በኮሮናቫይረስ ምክንያት 1600 በላይ የአእምሮ ህሙማን በስህተት ከሆስፒታል ተለቀዋል ተባለ

በኮሮናቫይረስ ምክንያት 1600 በላይ የአእምሮ ህሙማን በስህተት ከሆስፒታል ተለቀዋል ተባለ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

በሰሜናዊ ዌልስ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ለ1700 የተጠጉ የአእምሮ ጤና እክል ያለባቸው ታማሚዎች በስህተት ከማዕከላት እንዲወጡ መደረጉ ተገልጿል።

ባሳለፍነው ሳምንት ‘ቤትሲ ካድዋላድር’ የጤና ቦርድ ወረርሽኙ ቀለል ሲል ሰዎች እንደ አዲስ ህክምናቸውን እንዲጀምሩ አሳስቧል።

ቦርዱ በግምቴ መሰረት ከ 200 እስከ 300 የሚደርሱ ታማሚዎች ተለቀዋል ቢልም ትክክለኛው ቁጥር ግን 1694 አካባቢ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም ምክንያት የጤና ቦርዱ ይቅርታ በመጠየቅ ታማሚዎችን ማፈላለግ ጀምሯል።

የቦርዱ ጊዜያዊ ስራ አስፈጻሚ ሲሞን ዲን በበኩላቸው የአእምሮ ታማሚዎቹን ከማዕከላቱ እንዱወጡ ማድረጉ ተገቢ አልነበረም፤ ሊፈጠር የማይገባው ስህተትም ነው ብለዋል።

‘’ይህን ያክል ቁጥር ያላቸው ታማሚዎች የመውጫ ጊዜያቸው ሳይደርስና ህክምናቸውን ሙሉ በሙሉ ሳይጨርሱ እንዲወጡ መደረጋቸው በጣም ያሳዝናል።‘’

አክለውም ‘’ሁሉም ታማሚዎች በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ከያሉበት ተፈልገው ወደ ቀድሞ ህክምናቸው እንዲመለሱ ይደረጋል መባሉ አስደስቶኛል። ነገር ግን እንዲህ አይነት ትልቅ ስህተት ያለበት ውሳኔ በቦርዱ እንዴት ሊፈጸም እንደቻለ አልገባኝም’’ ብለዋል።

ጌዜያዊ ስራ አስፈጻሚው ክስተቱን ተቀባይነት የሌለው ነው ካሉ በኋላ የጤና ስርዓቱን ለመደገፍ ፈጣን የሆነ መልሶ የመቋቋም ስራ መሰራት አለበት ብለዋል።

የዌልስ መንግስት በበኩሉ ከመጀመሪያ ደረጃ የአእምሮ ጤና ማዕከለት ታማሚዎች ያለጊዜያቸው መለቀቃቸውን ሰምተናል፤ በዚህ ከባድ ወረረርሽኝ ወቅት መከሰቱ ደግሞ አሳሳቢ ያደርገዋል ብሏል።

አንድ የመሥግስት ቃል አቀባይ እንዳሉት ሁሉም ታማሚዎች ወዳሉበት አካባቢ ድረስ በመሄድ ተፈልገው ወደ ጤና ማዕከላቱ እንዲመሱ ይደረጋል።