የሌሴቶው ጠቅላይ ሚኒስትር ሚስታቸውን በቅጥር ነፍሰ ገዳዮች አስገድለዋል ተባለ

የሌሴቶ ፖሊስ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንሰትር ቶማስ ታባኔ ከአሁኗ ባለቤታቸው ጋር

የፎቶው ባለመብት, AFP

የምስሉ መግለጫ,

የሌሴቶ ፖሊስ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንሰትር ቶማስ ታባኔ ከአሁኗ ባለቤታቸው ጋር

የሌሴቶ ፖሊስ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንሰትር ቶማስ ታባኔ ከአሁኗ ባለቤታቸው ጋር በመሆነ የቀድሞ ሚስታቸውን ለመግደል ማሴራቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።

ፖሊስ እንደሚለው ከሆነ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንሰትር ከአሁኗ ሚስታቸው ጋር በመሆን የቀድሞ ባለቤታቸውን እአአ 2017 ላይ ገዳይ በመቅጠር አስገድለዋል።

ሊፖሌሎ ታባኔ በጥይት ተመተው የተገደሉት ባለቤታቸው ጠቅላይ ሚንሰትር ለመሆን ቃለ መሃላ በሚፈጽሙበት ዋዜማ ላይ ነበር።

በግድያ ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው የአሁኗ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ባለቤት ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛሉ።

ፖሊስ የአሁኗ የጠቅላይ ሚንስትሩ ባለቤት በዋስ ከእስር እንዳይወጡ አዲስ ያገኘውን መረጃ ለፍርድ ቤት እንደሚያቀርብ ተነግሯል።

ጠበቆች ግን የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ጤና አሳሳቢ ስለሆነ "በዋስ ከእስር ተለቃ ባለቤቷን መንከባከብ ይኖርባታል ብለን መከራከሪያ እናቀርባለን" እያሉ ነው።

የቀድሞ ጠቅላይ ሚንሰትር ቶማስ ታባኔ ይህን ወንጀል አልፈጸምኩም ሲሉ ይከራከራሉ። ቶማስ ታባኔ የተከፈተባቸውን ክስ ተከትሎ ባሳለፍነው ወር ስልጣን ለመልቀቅ መገደዳቸው ይታወሳል።

ቶማስ ታባኔ እስካሁን ክስ አልተመሰረተባቸውም። ፖሊስ ግን አገኘሁት ያለው መረጃ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንሰትር ለገዳዮቹ የቀድሞ ባለቤታቸውን መኖሪያ ቤት ጠቁመዋል።

ፖሊስ ጨምሮ እንዳለው የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር እና የአሁኗ ባለቤታቸው ሊፖሌሎ ታምባኔን ለማስገደል 180ሺህ ዶላር ለመክፈል ተስማምተዋል።

እንደ ፖሊስ መረጃ ከሆነ ገዳይ እና አስገዳይ ክፍያው በተለያየ ጊዜ እንዲፈጸም ተስማምተው ነበር። 24ሺህ ቀደብ ለግድያው ተከፍሎ እንደነበረም በፖሊስ መዝገብ ላይ ተመልክቷል።

ከገዳዮቹ መካከል አንዱ ፍርድ ቤት ቀርቦ ምስክርነቱን እንደሚሰጥ ተነግሯል።

እንደተባለው የቀድሞዋ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለቤት እንድትገል የተፈለገው፤ አዲሷ ሚስት "ቀዳማዊ እመቤት" እንድትሆነ በመፈለጋቸው እንደሆነ ፖሊስ አመልክቷል።