ፎቶግራፍ፡ እናትነት በማረሚያ ቤት

አንጀላ ከልጇ አንቲካ ጋር

የፎቶው ባለመብት, JADWIGA BRONTE

ፎቶ አንሺዋ ጃድዊጋ ብሮንቴ አምና ለአሥር ወራት እናቷን በሞልዶቫ ማረሚያ ቤት እየተመላለሰች ጠይቃለች። ስድስት ማረሚያ ቤት ያሉ እናቶችን ከልጆቻቸው ጋር የሚያሳይ የፎቶግራፍ ፕሮጀክትም ሠርታለች።

‘ጉድ ሜሞሪስ’ ወይም ጥሩ ትውስታ የተባለው የፎቶ ስብስቧ ማረሚያ ቤት ያሉ እናቶችና ልጆችን ሕይወት ያስቃኛል።

“ፎቶዎቹ እንደ ወንጀለኛ ሳይሆን እንደ እናት እንዲታዩ፣ በራስ መተማናቸው እንዲጨምር፣ ራሳቸውን እንዲያገኙ ይረዳሉ” ትላለች ፎቶ አንሺዋ ጃድዊጋ።

የስድስቱ ሴቶች ታሪክ እነሆ፦

ከእስር ወጥቼ ሕይወቴን ዳግመኛ መጀመር አልማለሁ” አሊና- የኒኮል እናት

የፎቶው ባለመብት, Jadwiga Bronte

ለቤተሰቦቼ ብቸኛ ልጅ ነኝ። ሀብታም ባንሆንም የሚያስፈልገኝን ሀሉ አሟልተውልኛል።

ታማኝና ደስተኛ ነኝ። አንዳንዴ ስሜታዊ እሆናለሁ።

ጓደኞቼ፣ የሥራ ባልደረቦቼ ትዝ ይሉኛል። ጫማ ፋብሪካ ውስጥ ነበር የምሠራው። የመጀመሪያ ፍቅረኛዬን የተዋወቅኩትም እዚያ ነው።

በከዋክብት በደመቀ ምሽት ስንንሸራሸር ትዝ ይለኛል። ውብ ጊዜ ነበር።

ከዛ ከባለቤቴ ጋር ተዋወቅን። ወንድ ልጅ ወለድን። በጣም ደስ ብሎኝ ነበር። ያኔ ባለቤቴ ሌላ ቤተሰብ፣ ሌላ ሕይወት ነበረው።

አሁን ልጄ አንድ ዓመት ተኩል ነው። እኮራበታለሁ።

አሁን ሌላ የምወደው ሰው አለኝ። እሱም ይወደኛል። ልጄን እንደራሱ ልጅ ነው የሚወደው።

ቶሎ ከልጄ ጋር ከእስር ወጥቼ ሕይወቴን ዳግመኛ እንደ አዲስ መጀመር አልማለሁ።

ከቤተሰቦቼጋርያሳለፍኩትንጊዜማሰብያስደስተኛልአና- የሶንያ እናት

የፎቶው ባለመብት, Jadwiga Bronte

ሴት ነኝ። የአራት ልጆች እናት ነኝ። ብርቱ ሰው ነኝ። ተስፋ አልቆርጥም።

መሥራት፣ ሙዚቃ ማዳመጥ፣ የፍቅር ፊልም ማየት እወዳለሁ። ሁለት ወንድሞችና አንድ እህት አሉኝ።

ቤተሰቦቼ ሞተዋል። ከወንድሞቼና ከእህቴ ጋር ጥሩ ግንኙነት የለንም። አናወራም። የምትደግፈኝ አንድ አክስቴ ብቻ ናት።

ከቤተሰቦቼ ጋር ያሳለፍኩትን ጊዜ ማሰብ ያስደስተኛል። ትውስታውን እስከወዲያኛው በውስጤ ይዤው እኖራለሁ። ከምንም ጋር ላነጻጽረው አልችልም።

ለአሥር ዓመት በትዳር ኖሬያለሁ። ይህን ሰው ስሙ እንኳን ሊጠራ አይገባውም። ከተለያየን ረዥም ጊዜ ሆኖናል።

ሁለት ሴት ልጆችና ሁለት ወንድ ልጆች አሉኝ። ትንሿ ልጄ ሶንያ ከኔ ጋር ናት። ሌሎቹን ግን ቶሎ ቶሎ አላገኛቸውም። አብሬያቸው ባለመሆኔ አዝናለሁ።

ስፈታእሠራለሁ።ልጄንምአስተምራለሁኤሌና- የቫኑሻ እናት

የፎቶው ባለመብት, Jadwiga Bronte

እናቴ የሞተችው በሦስት ዓመቴ ነው። ከእህትና ወንድሞቼ ጋር ተለያየን። ታላቅ እህቴና ወንድሜ ከአባቴ ስላልተወለዱ አባታቸው ወደ ካዛኪስታን ወሰዳቸው።

እኔና ታናሽ እህቴ ከእናቴ ወንድም ጋር መኖር ጀመርን። ከዛም እህቴን ለሌላ ቤተሰብ ሰጧትና እኔን ሕፃናት ማሳደጊያ አስገቡኝ።

ትምህርት ቤት ስገባ ደስ አለኝ። ጓደኞች አገኘሁ።

በጣም ደስ የሚለኝ የልጅነት ትዝታዬ የዘጠኝ ዓመት ልደቴ ነው። አስተማሪዬ ኬክና ስጦታ አመጥታልኝ ነበር። በጣም እወዳታለሁ። ልክ እንደ እናቴ ናት።

ከልጅነት ሕይወቴ የምጠላው አያቴ የሞተችበትን ቀን ነው። ዘመዶቼ ቀብር አልወሰዱኝም ነበር።

በአንድ መደብር ሽያጭ ክፍል እሠራ ነበር። አላገባሁም። የልጄ አባት በጣም እወደው የነበረ ሰው ነው።

ታስሮ እየተመላለስኩ እጠይቀው ነበር። ሲፈታ ግን እኔ ጋር ሳይመጣ፣ ልጁንም ሳያይ ቀረ።

የሁለት ዓመት ልጄ ቆንጆና ብልህ ነው።

ሙዚቃ፣ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ፣ ንባብ እወዳለሁ።

ስፈታ እሠራለሁ። ልጄንም አስተምራለሁ። የተሻለ ሕይወት ሊኖረው ይገባል። የኔን ስህተት መድገም የለበትም።

“በልጅነቴና ወጣት ሳለሁም ጥሩ ጓደኞች ነበሩኝ” ሉሚድሚላ- የሉሊያን እናት

የፎቶው ባለመብት, Jadwiga Bronte

እስከ 19 ዓመቴ ከቤተሰቦቼና ከእህቴ ጋር ነው የኖርኩት። ከዛ እናቴና አባቴ ተለያዩ። አባቴ ይጮህብኝ፣ ይደበድበኝ ነበር። እህቴን የበለጠ ይወዳታል።

ጥሩ ግንኙነት የነበረኝ ከእናቴና እህቴ ጋር ነው።

ትምህርት ደስ ይለኝ ነበር። በተለይ ሥዕል፣ ሙዚቃ፣ ስፓርትና የቋንቋ ትምህርት እወዳለሁ።

በልጅነቴና ወጣት ሳለሁም ጥሩ ጓደኞች ነበሩኝ። ከልጄ ሉሊያን አባት ጋር ፍቅር የያዘኝ በ20 ዓመቴ ነበር።

እድሉን ስላላገኘሁ ዩኒቨርስቲ መግባት አልቻልኩም።

አብሬያቸውአለመሆኔያሳዝነኛልአንጅላ- የአኒቱካ እናት

የፎቶው ባለመብት, Jadwiga Bronte

ከሁለት ዓመቴ ጀምሮ ያሳደገኝ አባቴ ነው። እናቴ ወንድሜን ይዛ የሄደችው አንድ ዓመት ሲሞላው ነበር።

ከዛ በኋላ ከእናቴና ከወንድሜ ጋር አላወራሁም። አባቴ ጓደኛዬ ነበር። ጥሩ ትምህርት እንዳገኝ አድርጓል።

ሦስት ዓመት ኬክ መጋገር ተምሬያለሁ።

የማልረሳው የልጅነት ትውስታ አባቴ ልደቴን ከክፍል ጓደኞቼ ጋር ሲያዘጋጅ ነው። በጣም የምጠላው ደግሞ እናቴ ጥላን የሄደችበትን ወቅት።

ከባለቤቴ ጋር ለስምንት ዓመት አብረን ነን። ስድስት ልጆች አሉኝ። ትንሿ አኒቱካ ከኔ ጋር ናት።

ሌሎቹ ልጆቼ ቤት ናቸው። ካገኘኋቸው ሰባት ወር አለፈኝ። አብሬያቸው አለመሆኔ ያሳዝነኛል።

ልጆቼሁሉነገሬናቸውራታ- የኒኮል እናት

የፎቶው ባለመብት, Jadwiga Bronte

ሁለት ልጆች አሉኝ። እንቁ ናቸው። ፈጣሪ እነሱን ስለሰጠኝ እኮራለሁ።

እህቴ እስከሞተችበት ቀን ድረስ አምስት ቤተሰብ ነበረኝ። ከሞተች በኋላ ቤተሰባችን አንደቀድሞው መሆን አልቻለም።

ወላጆቼ ተፋትተዋል። እናቴ ሌላ ሰው አግብታለች። ሁለት ብዙም የማላዋራቸው ወንድሞች አሉኝ።

ትምህርት ቤት መሄድ ደስ ይለኝ ነበር። የማልወዳቸውን ትምህርቶች ግን አልማርም ነበር።

ኳስ መጫወት ደስ ይለኝ ነበር።

የማልረሳው አስደሳች የልጅነት ትውስታ ከወንድ ጓደኛዬ ቫሲል ጋር ያሳለፍነው ጊዜ ነው።

ይንከባከበኝ፣ ስጦታ ይሰጠኝም ነበር። ሁሌም ከኔና ከምታሳድገኝ አክስቴ ጋር ስለሚሆን እወደው ነበር። የማምነው ብቸኛ ሰው እሱ ነበር።

የሚያሳዝነኝ ነገር አክስቴ እስከ 16 ዓመቴ ድረስ ሁሌ ትመታኝ ነበር። ከአቅሜ በላይ ሲሆን ከቤት ጠፍቼ ሌላ ቦታ ሥራ ተቀጠርኩ።

የራሴ ገንዘብ እያገኘሁ ስለነበር ደስ አለኝ። ከዛ ከአገር ወጥቼ ለአንድ ዓመት ተኩል ሠራሁ።

ነገሮች ተበላሽተው እስክታሰር ድረስ ሕይወት ጥሩ ነበር። ግን በፈጣሪ እርዳታ ነፃ እወጣለሁ።

ከልጆቼ አባት ጋር አልገናኝም። ልጆቼ ሁሉ ነገሬ ናቸው።

አንዱ ልጄ ከኔ ሌላኛው ከአክስቴ ጋር ይኖራል። ካየሁት ዓመት አልፏል።

በቅርቡ አግብቻለሁ። ጥሩ ባል አለኝ። ከዚህ ሊያወጣን እየሞከረ ነው።

ህልሜ ከዚህ ወጥቼ ሥራ ይዤ ልጆቼን ማሳደግ ነው። ሰፊ መናፈሻ ያለው ቤትም እፈልጋለሁ።