በዩኬ የቻይና አምባሳደር ትዊተር ገፅ ወሲባዊ ቪዲዮን 'ላይክ' ማድረጉ ውዝግብ አስነሳ

የአምባሳደር ሊዪ ክሲያዎሚንግ

የፎቶው ባለመብት, Reuters/Twitter

በዩኬ የሚገኘው የቻይና አምባሳደር ይፋዊ የትዊተር ገፅ አንድ ወሲባዊ ቪዲዮን'ላይክ' አድርጓል በሚል ምርመራ እንዲከፈት ቻይና ትዊተርን ጠይቃለች።

የአምባሳደር ሊዪ ክሲያዎሚንግ ይፋዊ የትዊተር ገፅ ከዚህ ቀደምም የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲን የተቹ ፅሁፎችን በመውደድ እንዲሁም አይናቸው በጨርቅ ታፍኖ የታሰሩ ሰዎችንም ፎቶ ለጥፏል።

ባለስልጣናቱ "የአምባሳደሩ አካውንት ፀረ-ቻይና ጥቃት ደርሶበታል። ይህም ህዝቡን ለማሳሳት ሆን ብሎ የተወጠነ ሴራ ነው፤ ወንጀልም ነው" ብለውታል።

ትዊተር በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም አስተያየት አልሰጠም

ይህ ሁኔታ ቀልብ የሳበው የአምባሳደሩ ይፋዊ አካውንት ወሲባዊ ይዘት ያለውና በቻይና አንደኛው ቋንቋ መረጃን የያዘ ቪዲዮ ላይክ ማድረጉን ተከትሎ ነው።

በለንደን ተቀማጭነቱን ያደረገ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን ለሌሎች የትዊተር ተጠቃሚዎች ትዊቱን ፎቶ በማንሳት አጋርቷል።

ሆኖም ወዲያው ይህ ይፋዊ አካውንት ቪዲዮውን 'አንላይክ አድርጎታል"

ሆኖም አሁንም አወዛጋቢ የሆኑ ትዊቶችን ላይክ እንዳደረገ የነበረ ሲሆን በኋላ ግን አንላይክ አድርጎታል።

አንደኛው የቻይና ሙስሊሞችን የግዞት ጣቢያ ውስጥ ውስጥ ስታስገባ የተቀረፀ የድሮን ተንቀሳቃሽ ምስል የሚያሳይ ነው።

የቻይና መንግሥት ከዚህ ቀደም በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን የኡይጉር ሙስሊሞችን ወደ ግዞት ጣቢያ ወስዳለች መባሏን ውንጀላ ነው በማለት አጣጥላዋለች።

ከዚህ በተጨማሪም የኡይጉር ሙስሊሞችን የማምከን ስራ እየተሰራ ነው የሚለውንም የድሮን ተንቀሳቃሽ ምስል ቢቢሲ በማሳየት አምባሳደሩን ቢጠይቅም በጭራሽ ብለው ክደዋል።

የፎቶው ባለመብት, Twitter

በቻይና ትዊተር ቢታገድም በባለፈው አመት የቻይና ባለስልጣናት ትዊተርን በሰፊው መጠቀም ጀምረዋል፤ የአምባሳደሩም ይፋዊ ገፅ የተከፈተው በጥቅምት ወር ነው።

በመተግበሪያው ያለው ላይክ የማድረጊያ ቁልፍ አሳሳች ስለሆነ ድጋፋቸውን ለማሳየት ሳይሆን በስህተት የተፈፀመ ይሆናል ቢሉም የቻይና ባለስልጣናት በበኩላቸው ይህ አስተያየት ተቀባይነት የለውም ብለዋል፥

"ኤምባሲው ለትዊተር ሪፖርት አድርጓል ይህንንም ጠለቅ ያለ ምርምር በማድረግ ሁኔታውን በደንብ ሊያዩት ይገባል" ብለዋል ባወጡት መግለጫ

በአሁኑ ሰዓት የአምባሳደሩ ትዊተር ገፅ ሁለት ላይኮች ብቻ ሲሆን ያሉት ይህም ከአመት በፊት ትዊት የተደረጉ ናቸው።