ምርጫ፡ የትግራይ ክልላዊ ምርጫ ተፎካካሪዎች ምን አሉ?

ምርጫ፡ የትግራይ ክልላዊ ምርጫ ተፎካካሪዎች ምን አሉ?

መቀለ የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ እንደገለፀው በትግራይ ትናንት መራጮች ድምጻቸውን ለመስጠት ከንጋት 10፡30 ጀምሮ በምርጫ ጣቢያዎች ፊት ለፊት ተሰልፈው ተመልክቷል። በክልሉ 38 የምርጫ ክልሎች እንዳሉ የትግራይ ክልል ምርጫ ኮሚሽን መግለጹ ይታወሳል። በክልላዊ ምርጫው ክልሉን የሚያስተዳድረውን ህወሓትን ጨምሮ 5 ፓርቲዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ። ፓርቲዎች ስለምርጫው ትናንት ምን አሉ?