ለስደት የተዳረጉት በአፍሪካ ቀንድ የሚገኙ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን

ለስደት የተዳረጉት በአፍሪካ ቀንድ የሚገኙ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን

በአፍሪካ የተለያዩ አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ሆኖ መገኘት በወንጀል ያስቀጣል። ግለሰቦቹም ከማሕበረሰቡ፣ ከቤተሰቦቻቸውና ከጸጥታ አካላት የተለያዩ ጥቃቶችን እንደሚያስተናግዱ ይናገራሉ። በዚህም የተነሳ የትውልድ አገራቸውም ጥለው ከተሰደዱ ሁለት ግለሰቦች መካከል ፋሪስ ኩቺ ገዛኸኝን ከኢትዮጵያ እና ዋሂራ ላቤሌን ከሶማሊያ አነጋግረናል። ፋሪስ በሁለቱም ጾታ መጠራት የማይፈልጉ በመሆናቸው "አነርሱ" በሚል የሚጠሩ ሲሆን፣ ዋሂራ ደግሞ ጾታዋን በመቀየሯ የተነሳ ራሷን "አንቺ" በማለት ትገልጻለች።