"ሲድኒ ላይ ያሸነፈው የእግዚአብሔር እግር ነው"- ኃይሌ ገብረ ሥላሴ

"ሲድኒ ላይ ያሸነፈው የእግዚአብሔር እግር ነው"- ኃይሌ ገብረ ሥላሴ

አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የምንጊዜም ታላቅ ሯጭ ነው። ከትራክ እስከ ጎዳና ላይ ውድድሮች ኢትዮጵያዊው ጀግና ክብረ ወሰኖችን እየሰባበረ በሁሉም ድልን ተቀዳጅቶባቸዋል። ኃይሌ ባደረጋቸው ውድድሮች፣ 2 የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ፣ 4 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናነትን እና 4 የቤት ውስጥ ውድድሮችን አሸንፏል̀። 27 ክብረ ወሰኖችን ሰባብሯል። ነገር ግን ለኃይሌ የትኛው ይበልጥበታል? የታላቁ ሯጭ አምስቱ ምርጫዎች እነዚህ ናቸው!