በትዊተር የተዋወቃቸውን ዘጠኝ ሰዎች የገደለው ጃፓናዊ ጥፋተኛ መሆኑን አመነ

ታካሂሮ ሺራሺ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

በትዊተር የተዋወቃቸውን ዘጠኝ ግለሰቦች የገደለው ጃፓናዊ ጥፋተኛ ነኝ ብሏል።

በቅፅል ስሙ "የትዊተሩ ገዳይ የሚል ስያሜ የተሰጠው ታካሂሮ ሺራይሺ በቁጥጥር ስር የዋለው ከሶስት አመታት በፊት ነበር፥

በቤቱም ውስጥ የገደላቸው ሰዎች የሰውነትም አካላትም መገኘትም ጃፓንያውያንን አስደንግጧል።

ከነዚሀም መካከል የተቆረጠ ጭንቅላት፣ አጥንት በማቀዝዣና በሳጥንም ውስጥ ተገኝቷል።

በዚህ ሳምንት ረቡዕም በመዲናዋ ቶክዮ የቀረቡበት ክሶች በሙሉ ትክክል መሆናቸውንም ተናግሯል።

ጠበቆቹ በበኩላቸው ደንበኛቸው ግድያዎቹን ፈፅሜያለሁ ቢልም ከተገዳዮቹ ፍቃድ አግኝቷል ብለውም እየተከራከሩ ነው።

ስለዚህም በግድያ ወንጀል ሳይሆን ግድያ በፍቃድ በሚልም እንዲቀየርም የጠየቁ ሲሆን ይህም ሁኔታ ተቀባይነት ካገኘም ከስድስት- ሰባት ወራት በሚቆይ እስር ይቀልለታል ተብሏል።

ታካሂሮ 'የትዊተሩ ገዳይ' ከጠበቆቹ ጋር አይስማማም ለአገሬው ጋዜጣ እንደተናገረው ግለሰቦቹን ለመግደል ፈቃድ እንዳላገኘ ነው።

"ጭንቅላታቸው ጀርባ ቁስል ይታያል። ይህም ማለት እንዳያስቸግሩኝ የመታኋቸው ነው፤ እንድገድላቸው ፈቃድ አላገኘሁም" በማለት መናገሩንም ጋዜጣው በትናንት ዕትሙ አስነብቧል።

ታካሂሮ በግድያዎቹ ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆኖም ከተገኘ በጃፓን ህግ መሰረት የስቅላት ቅጣት ይጠብቀዋል።

የፍርድ ሂደቱ የመላ ጃፓናውያንን ቀልብ ሰቅዞ የያዘ ሲሆን በትናንትናው እለትም 600 የሚሆኑ ሰዎች ፍርድ ቤት ለመግባትና ለመከታተል ተሰልፈው መታየታቸውም ተዘግቧል።

አቃቤ ህግ ባቀረበው ክስ መሰረት ታካሂሮ የትዊተር ገፁንም የከፈተው ራሳቸውን ማጥፋት የሚፈልጉ ሴቶችን በቀላሉ ለማግኘትም ነበር። ሴቶቹም ቀላል ኢላማ ሆነውለታል።

ከሟቾቹ መካከል ስምንቱ ሴቶች ሲሆኑ ሶስቱ ደግሞ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ናቸው። የአስራ አምስት አመት ታዳጊና አራቱ ደግሞ በሃያዎቹ የእድሜ ክልል የሚገኙ ናቸው።

ታካሂሮ የገደለው ብቸኛው ወንድም 20 አመቱ ሲሆን የጠፋችበት የሴት ጓደኛው የት አደረስካት በሚል እሰጣገባ በተፈጠረ ግጭት ነው ተብሏል።

የ27 አመቱ ታካሂሮ እነዚህን ሴቶች በቀላሉ ራሳቸውን የሚያጠፉበት መንገድ እንዳለውና ራሱንም አብሯቸው እንደሚያጠፋ ገልጾላቸዋል።

በትዊተር ገፁም ላይ "በከፍተኛ ህመም ላይ ያሉ ሰዎችን መርዳት እፈልጋለሁ። በማንኛውም ሰዓት በመልእክት ሳጥኔ በቀጥታ መልእክታችሁን አድርሱኝ" ይላል።