ኢትዮጵያ፡ የአርሶ አደሩን ልፋት መና ያስቀረው የአንበጣ መንጋ ወረራ

ኢትዮጵያ፡ የአርሶ አደሩን ልፋት መና ያስቀረው የአንበጣ መንጋ ወረራ

ከመስከረም መጀመሪያ ጀምሮ በኢትዮጵያ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ አሁንም መቋጫ አላገኘም። ከሶማሌ እስከ ትግራይ ክልል ድረስ አምስት ክልሎችንና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን አዳርሷል። አርሶ አደሮች በባህላዊ መንገድ ለመከላከል እየሞከሩ ነው። በኦሮሚያ ክልል ሰው አልባ አውሮፕላንን በመጠቀም የኬሚካል ርጭት እየተካሄደ ነው። የአንበጣ መንጋው በየጊዜው የሚጨምር በመሆኑ ጉዳቱን መቀነስ አስጋሪ ሆኗል።