ከልጇ ጋር ተምራ ከኮሌጅ ተመረቀችው የአራት ልጆች እናት

ከልጇ ጋር ተምራ ከኮሌጅ ተመረቀችው የአራት ልጆች እናት

ወ/ሮ አይሻ ሹንጊ በልጅነቷ ገንዘብ ለማግኘት ሲባል ከሰው ቤት ተቀጥራ ትሰራ ነበር። ያንን ያደረገችው የልጅነት ሕልሟን ለማሳካት ነበር፤ ትምህርት ለመማር። በእቅዷ መሰረትም ወደ ቤተሰቦቿ ተመልሳ ትምህርቷን ቀጠለች።

ስምንተኛ ክፍል ስትደርስ ግን ቤተሰቦቿ ያልጠበቀችውን ውሳኔ ወሰኑባት። ሊድርሯት ተስማሙ። የወላጆቿን ትዕዛዝ ማክበር ስለነበረባት ትዳሩን ተቀብላ ልጆች እየወለዱ ከባሏ ጋር መኖር ጀመረች።

የጎዳና ላይ ምግብ በምትሸጥበት ወቅት ለኦሮምኛ ተናጋሪ ስደተኞች በማስተርጎም ለአንድ ዓመት በበጎ ፈቃድ ሰራች። ይህ የበጎ አድራጎት ሥራዋም ወደቋሚ ቅጥር እንዲያድግላት ዕድል ተሰጣት። ነገር ግን ቋሚ ሆና እንድትቀጠር የሚያስችል የትምህርት ዝግጅት አልነበራትም።

በዚህ ወቅት አይሻ አራት ልጆችን ወልዳ ነበር። እናም በዚህ ሁኔታ ቁጭት ውስጥ የገባችው አይሻ ትምህርቷን ካቆመችበት ቀጠለች። አሁን ኮሌጅ ገብታ ዲፕሎማዋን ካጠናቀቀች በኋላ ዲግሪዋን ደግሞ ከልጇ ጋር በመመማር ላይ ትገኛለች።