ሂጃብ የምትለብሰው ታዋቂዋ ሞዴል ሀሊማ አደን ለምን ሥራዋን ተወች?

ሀሊማ አደን

የፎቶው ባለመብት, Giliane Mansfeldt Photography, LLC

ሀሊማ አደን ሂጃብ ለብሳ የዓለም ምርጧ ሞዴል መባሏ ከእስልምና ሐይማኖቷ ጋር የማይስማማ በመሆኑ ከፋሽን ኢንዱስትሪውን ራሷን አግልላለች፡፡ ከቢቢሲ ግሎባል የሃይማኖት ጉዳዮች ዘጋቢ ጋር በነበራት ቆይታ - እንዴት ሞዴል ሆና መሥራት እንደጀመረች እና ለማቆም እንዴት እንደወሰነች ትናገራለች፡፡

የ23 ዓመቷ ሀሊማ በበርካታ ሶማሌዎች ተከብባ በሚኔሶታ በሴንት ክላውድ ነው ያደገችው፡፡ ተራ ልብሶችን ለብሳ እና ያለ ምንም መዋቢያ ከውሻዋ ኮኮን ጋር ነው በደስታ ያሳለፈችው፡፡

የተወለደችበትንና ኬንያ የሚገኘው የስደተኞች መጠለያን በመጠቆም "እኔ ከካኩማ የመጣሁ ሀሊማ ነኝ" ትላለች፡፡ ሌሎች ሂጃብ የምትለብሰው ሱፐር ሞዴል ወይንም በቮግ መጽሔት ሽፋን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣች፣ የመጀመሪያዋ የሂጃቢ ለባሽ ሞዴል እያሉ ቢገልጿትም እርሷ ግን የፋሽን ኢንዱስትሪው ከእምነቴ ጋር የሚጋጭ ነው በማለት ትታዋለች።

"እንደዚህ በቃለ-መጠይቅ ምቾት ተሰምቶኝ አያውቅም" ስትል ሳቀች፡፡ "ምክንያቱም የራሴ ባልሆነ ልብስ ለመዘጋጀት 10 ሰዓት ስላላጠፋሁ" ብላለች።

ሂጃማ እንደምትለብስ ሞዴል ሀሊማ ልብሷን ትመርጣለች። በሥራዋ የመጀመሪያ ዓመታት የራሷን ሂጃብ እና በረዣዥም ቀሚሶች የተሞሉ ሻንጣዎችን ወደ እያንዳንዱ ቀረፃ ትወስድ ነበር፡፡ ለሪሃና ፌንቲ ቢውቲ የራሷን ቀላል ጥቁር ሂጃብ ለብሳለች፡፡

ምንም ለብሳ ቢሆን ለእያንዳንዱ ቀረፃ ሂጃቧን ማድረጓ ለድርድር የማይቀርብ ነበር፡፡ በጎርጎሮሳውያኑ 2017 በዓለም ላይ ካሉ ትልልቅ የሞዴሊንግ ኤጄንሲዎች አንዱ ከሆነው ከአይ ጂ ኤም ጋር ስትፈራረም መቼም ቢሆን ሂጃብ እንደማታወልቅ የሚገልጽ አንቀጽ ውሏ ውስጥ ጨምራለች፡፡ ሂጃብዋ ለእሷ ዓለሟ ማለት ነው፡፡

"የሞዴሊንግ ውል ለማግኘት መሞት የሚፈልጉ ሴቶች ቢኖሩም ተቀባይነት ባላገኝ ላለመሥራት ተዘጋጅቼ ነበር" ትላለች፡፡

ምክንያቱም በዚያ ወቅት ማንም ስለ እርሷ ስለማያውቅ "ማንም ነበረች።"

በሞዴሊንግ ስራ ውስጥ እየቆየች ስትመጣ፣ በምትለብሳቸው ልብሶች ላይ ቁጥጥሯ አነስተኛ ነበር።

በሙያዋ የመጨረሻ ጊዜያት ሂጃቧ እያነሰ እና እየቀነሰ ሄደ። አንዳንድ ጊዜ አንገቷን እና ደረቷን ያሳይ ነበር። አንዳንድ ጊዜም በሂጃብ ምትክ ጂንስ ወይም ሌሎች ልብሶችን እና ጨርቆችን ጭንቅላቷ ላይ ታደርግ ነበር፡፡

ሌላኛው የሀሊማ የስራ ውል ውስጥ የተካተተው አንቀጽ በራሷ የግል ቦታ መልበስ እንድትችል አድርጓል፡፡

ሆኖም እሷን ተከትሎ ወደ ኢንዱስትሪው የገቡ ሌሎች ሂጃብ የሚለብሱ ሞዴሎች ተመሳሳይ አክብሮት እንደሌላቸው ወዲያው ተገነዘበች፡፡ ልብስ የሚለውጡበት መጸዳጃ ቤት ፈልጉ ሲባሉ ሰምታለች፡፡

"እነዚህ ሴቶች የእኔን ፈለግ እየተከተሉ ቢሆንም የተከፈተከላቸው በር የአንበሳው አፍ ነው" አልኩኝ፡፡

ተተኪዎቿ ከእርሷ እኩል እንዲሆኑ ትጠብቅ የነበረ ሲሆን ለእነሱ ያላት የመከላከያ ስሜትንም አጠናከረ፡፡

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

"ብዙዎቹ በጣም ወጣት ሲሆኑ ዘግናኝ ኢንዱስትሪ ሊሆንባቸው ይችላል። በተካፈልንባቸው መዝናኛ ቦታዎች እንኳን አንዷን ሂጃብ የምትለብስ ሞዴል ከሚወሯት ወንዶች ለመከላከል እንደምትጥር ትልቅ እህት ሆኜ ራሴን አገኛለሁ። 'ይህ ትክክል አይመስልም ፣ ልጅ ነች' የሚል ስሜት ውስጥ ነበርኩ፡፡ ወደ ውጭ አውጥቼ ከማን ጋር እንደሆነች እጠይቃታለሁ" ትላለች።

የሃሊማ የኃላፊነት ስሜት እና ማህበራዊ ህይወት በተወሰነ ደረጃ የመጣው የሶማሌ ተወላጅ ከመሆኗ ነው፡፡

በሰሜን ምዕራብ ኬንያ በሚገኘው ካኩማ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ልጅ ሆኖ ጠንክሮ መሥራት እና ሌሎችን መርዳትን ከእናቷ ተማረች፡፡ ይህም ተግባሯ ሀሊማ የሰባት ዓመት ልጅ ሳለች አሜሪካ ውስጥ ብዙ የሶማሊያ ማህበረሰብ በሚኖሩባት ሚኔሶታ ከተዛወሩ በኋላም ቀጠለ፡፡

ሃሊማ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆና የመጀመሪያዋ ሂጃብ የምትለብስ ንግስት ስትሆን ችግር ተፈጠረ፡፡ ጥሩ ውጤት ላይ ያተኮረችው እናቷ እንደማይወዱት ታውቅ ነበር፡፡

"በጣም አፍሬ ነበር ምክንያቱም ልጆቹ ወደ ቤትዋ ይመጡና እናቴ ያዘጋጀችውን 'ይህንን አታድርጊ' ይላሉ'' ብላለች።

ፍርሃቷ ትክክል ነበር፡፡ የሃሊማ እናት ዘውዱን ሰበረችው፡፡ "በጣም ስለጓደኞችሽ እና በውበት ውድድሮች ላይ እያተኮርሽ ነው" አሏት።

ሃሊማ በወይዘሪት ሚኒሶታ አሜሪካ የ2016 ውድድር ላይ ተሳተፈች። የመጀመሪያዋ ሂጃብ የለበሰች ተወዳዳሪ ስትሆን ግማሽ ፍፃሜ ለመድረስም በቃች፡፡

ከእናቷ በተጻራሪ ሃሊማ በሞዴልነት ሙያ ለመሰማራት መረጠች። እናቷ ሙያው ሃሊማ ጥቁር፣ ሙስሊም እና ስደተኛ ከመሆኗ ጋር አብሮ አይሄድም ብለው ያስባሉ፡፡

በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ስትሳተፍም ሆነ በወይዘሪት ዩ ኤስ ኤ ላይ ዳኛ ስትሆን እናቷ "ትክክለኛ ሥራ እንድታገኝ" ያበረታቷት ነበር፡፡

የሃሊማ የበጎ አድራጎት ሥራ ነው እናቷን ለማሳመን በተወሰነ መልኩ የረዳት፡፡ ለተሻለ ኑሮ ከሶማሊያ ወደ ኬንያ ለ12 ቀናት በእግር የተጓዘች ስደተኛ በመሆኗ የተቸገሩትን መርዳት ያለውን ፋይዳ ታውቃለች፡፡

"እርሷም 'ለሰው መልሶ መርዳት ባይኖረው ሞዴሊንግን የምትቀጥይበት ምንም መንገድ የለም' አለች፡፡ ከኤም ጂ አይ ጋር ባደረግሁት የመጀመሪያ ስብሰባ ወደ ዩኒሴፍ እንዲወስዱኝ ነግሬያቸዋለሁ ትላለች ሀሊማ።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

አይ ኤም ጂ ደገፋት እና በ2018 ሃሊማ የዩኒሴፍ አምባሳደር ሆነች፡፡ ልጅነቷን በስደተኞች ካምፕ በማሳለፍዋ ሥራዋ በህፃናት መብት ላይ ያተኮረ ነበር፡፡

"እናቴ እንደ ሞዴል በጭራሽ አላየችኝም፡፡ የወጣት ሴቶች የተስፋ ብርሃን እንደሆንኩ ትመለከተኛለች። ለእነሱም ጥሩ አርአያ እንደምሆን ሁልጊዜ ያስታውሰኛል" ብላለች።

ሃሊማ ለተፈናቀሉ ሕፃናት ግንዛቤን ከፍ ለማድረግ እንዲሁም እሷ ያለመችበት እንደደረሰች ሁሉ እነሱም አንድ ቀን እንደዚያው እንደሚያደርጉ ተስፋ እንዲያደርጉ ለማሳየት ፈለገች፡፡

ዩኒሴፍ ግን እንደጠበቀችው አልሆነላትም፡፡

በ 2018 የዩኒስፍ አምባሳደር ሆና ብዙም ሳይቆይ ቴድ ቶክ ላይ ለመቅረብ የካኩማ ካምፕን ጎብኝታለች፡፡

"ልጆቹን አግኝቼ 'አሁንም ነገሮች እንደነበሩ እየተከናወኑ ነው? አሁንም በአዳዲስ መጤዎች ፊት መደነስ እና መዘመር አለባችሁ?' ስላቸው 'አዎ ግን አሁን እኛ ወደ ካምፕ ለሚመጡ ሌሎች ታዋቂ ሰዎች አናደርግም። አሁን 'ላንቺ እናደርጋለን' ብለዋል፡፡"

ሀሊማ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማት ተናደደች፡፡ እሷ እና ሌሎች ልጆች ዝነኛ ሰዎች ለመጎብኘት ሲሄዱ ሲዘምሩ እና ሲጨፍሩ እንደነበር አሁንም ድረስ እንደምታስታውስ ትናገራለች፡፡

ድርጅቱ በልጆች ትምህርት ላይ ከማተኮር ይልቅ በስሙ ላይ ያተኮረ መስሎ ታያት፡፡

"የራሴን ስም መፃፍ በማልችልበት ጊዜ እንኳን 'ዩኒሴፍ' ብዬ መጻፍ እችል ነበር ትላለች፡፡ ሚኔሶታ የመጀመሪያውን መጽሐፌን፣ የመጀመሪያ እርሳሴን እና የመጀመሪያዬን ቦርሳዬን ሰጠኝ፡፡ ዩኒሴፍ ግን ይህን አላደረገልኝም፡፡"

ጥላ ከሄደች በኋላ ያ ሁሉ እንደተለወጠ ትገምታለች፡፡

ለዓለም የህፃናት ቀን በካኩማ የሚገኙትን ልጆች በቪዲዮ ስታነጋግራቸው መቀጠል እንደማትችል ወሰነች፡፡ በዚህ በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት እና በክረምቱ እነሱን ማየት ከባድ ነበር፡፡

"ከልጆቹ ጋር ከተነጋገርኩ በኋላ ወሰንኩ" ትላለች ፡፡

ዩኒሴፍ ዩ ኤስ ኤ ለቢቢሲ እንደተናገረው "ለሃሊማ የሶስት ዓመት ተኩል አጋርነትና ድጋፍ እናመሰግናለን፡፡ አስደናቂ የመቋቋም እና የተስፋ ታሪኳ የእያንዳንዱን ልጅ መብት ወደሚያስከብር ራዕያዋ መርቷታል፡፡ ዩኒሴፍ ከሃሊማ ጋር አብሮ በመሥራቱ ዕድለኛ ሲሆን ለወደፊት ሥራዋ መልካሙ እንዲገጥማት እንመኛለን።"

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ሃሊማ ሞዴሊንግ ሞያዋ ያላት ጥርጣሬም እየባዛ ነበር፡፡

በፋሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ፍላጎቷ እየጨመረ በሄደ ቁጥር፣ ከቤተሰቦቿ ጋር የምታሳልፈው ጊዜ አነስተኛ ሆነ። በሙስሊም ሃይማኖታዊ በዓላትም ከቤት ውጭ ታሳልፍ ጀመር፡፡

"በሙያዬ የመጀመሪያ ዓመት ለዒድ እና ለረመዳን ቤት ማሳለፍ ችያለሁ። ባለፉት ሦስት ዓመታት ግን እየተጓዝኩ ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ በሳምንት ከስድስት እስከ ሰባት በረራዎች ይኖረኛል፡፡ በቃ ማቆሚያ የለውም' ትላለች፡፡

በመስከረም 2019 በ 'ኪንግ ኮንግ' መጽሔት የፊት ሽፋን ላይ ደማቅ ቀይ እና አረንጓዴ የአይን ማስዋቢያ እና በፊቷ ላይ ትልቅ ጌጥ አድርጋ ታየች፡፡ ጭምብል የሚመስል እና ከአፍንጫዋ እና ከአፍዋ በቀር ሁሉንም ነገር ይሸፍናል፡፡

"ዘይቤው እና ሜካፑ በጣም የሚያስፈራ ነበር። እኔን የሚመስል ነጭ ሰው ነበር የምመስለው" ትላለች።

አስደንጋጭ በሆነ መልኩ በተመሳሳይ ዕትም ውስጥ አንድ እርቃኑን የሆነ ወንድ ፎቶ አገኘች፡፡

"ሂጃብ የለበሰች ሴት ባለችበት መጽሔት ላይ እርቃኑን የሆነ ሰው በሚቀጥለው ገጽ ላይ መኖሩን መጽሔቱ እንዴት ተቀባይነት አለው ብሎ ያስባል? ብላ ትጠይቃለች፡፡ ካመነችበት ሁሉ ጋር ተቃራኒ ሆነ፡፡

ኪንግ ኮንግ ለቢቢሲ "አብረን የምንሠራቸው አርቲስቶች፣ ፎቶግራፍ አንሺዎች እና አስተዋፅዖ አድራጊዎች አንዳንዶቹን ሊማርኩ እና ሌሎችንም ቀስቃሽ ሊመስሉ በሚችሉ መንገዶች ራሳቸውን ይገልጻሉ። ነገር ግን የሚፈልጓቸው ታሪኮች ሁሌም ርዕሰ ጉዳዩን እና ሞዴሉን ያከብራሉ' ብሏል፡፡

"ሃሊማ ከእኛ ጋር በሠራችው ሥራ፤ በግሏ ያልወደደቻቸው እና የእሷ ባህሪ ጋር በምንም መልኩ የማይገናኙ ምስሎች በመኖራቸው እናዝናለን፡፡"

ሃሊማ በአውሮፕላን ማረፊያዎች ሆና በመጽሔቶች ሽፋን ላይ ያሉትን ፎቶግራፍዋን ስትመለከት ብዙውን ጊዜ ራሷን መለየት እንደሚያቅታት ትናገራለች፡፡

"እራሴን ማየት ስለማልችል ደስታዬ ዜሮ ነው። ሌላ ሰው መሆን ምን ያህል የአዕምሮ ጉዳት ሊኖረው እንደሚችል ያውቃሉ? ደስተኛ እና አመስጋኝ መሆን ሲገባኝ እና መገናኘት ሲኖርብኝ፣ ያ እኔ ነኝ? የራሴን ስዕል ግን ከእኔ በጣም ሩቅ ነበር፡፡"

"የሙያ ሥራዬ ከፍተኛ መስሎ ቢታይም በአዕምሮዬ ደስተኛ አልነበርኩም፡፡ "

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ሌሎች ችግሮችም ነበሩ። ስለሂጃብ ያላት ሕግ እስኪበጠስ ድረስ እየከረረ መጣ፤ እንዲሁም ሌሎች ሂጃብ የሚለብሱ ሞዴሎችም የሚስተናገዱበት መንገድም እንደዛው።

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሁሉንም ነገር ቀያየረ፡፡ በኮቪድ -19 የፋሽን ሥራዎችን ሲቆሙ ከምትቀርባት እናቷ ጋር ጊዜ ለማሳለፍ ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡

"2021ን እያሰብኩ በጭንቀት ውስጥ ነበርኩ፤ ምክንያቱም ከቤተሰቦቼ ጋር ቤት መቆየት እና ጓደኞቼን እንደገና ማየት እፈልግ ነበር" ትላለች።

በዚህም ባለፈው ጥቅምት የሞዴሊንግን እና የዩኒሴፍ ሚናዋን ለመተው ወሰነች፡፡

"ኮቪድ ለሰጠኝ አዲስ ዕድል አመስጋኝ ነኝ። ሁላችንም ስለ ሙያ መንገዳችን እያሰላሰልን 'እውነተኛ ደስታን ያመጣልኛል ፣ ደስታ ያስገኛል?' ብለን እንጠይቃለን" ትላለች።

የእናቷ ጸሎቶች በመጨረሻ ደረሰ፡፡

"ሞዴል በነበርኩበት ጊዜ እናቴ እያንዳንዱን ፎቶ መነሳት አልተቀበለችም። የእናት እና የልጅ ፎቶ መነሳትን እንኳን አታከናውንም ነበር" ትላለች ፡፡

"እርሷ በእውነት የእኔ ቁጥር አንድ አርዐያዬ ነች። ፈጣሪ የእሷ ልጅ እንድሆን ስለመረጠኝ በጣም አመስጋኝ ነኝ። በእውነቱ አስደናቂ እና ጠንካራ ሴት ነች፡፡"

ሃሊማ የምትደሰተው በፎቶግራፉ ብቻ አይደለም፡፡ በአፍጋኒስታን ውስጥ ያለውን ጦርነትን እና ዓመፅን በመሸሽ ላይ በተመሠረተ የእውነተኛ ታሪክ ፊልም ዋና አጋጅ ሆና አጠናቃለች፡፡ 'አይ አም ዩ' በመጋቢት ወር በአፕል ቴሌቪዥን ሊለቀቅ ተዘጋጅቷል።

"ለኦስካር እጩ መሆናችንን ለማየት በጉጉት እንጠብቃለን" ትላለች።

ዩኒሴፍን መተው ማለት ሃሊማ የበጎ አድራጎት ሥራ መስራቷን ትታለች ማለት አይደለም፡፡

"ፈቃደኛነቴን አላቆምም" ትላለች፡፡ ዓለም እንደ ሞዴል ወይም እንደ ዝነኛ ሰው የምትፈልገኝ አይመስለኝም። የምትፈልገኝ የአንድ ሳንቲምን እና የማህበረሰብን ጥቅም እንደምታውቅ የካኩማዋ ሃሊማ ትፈልጋለች፡፡"

መጀመሪያ ግን እረፍት ልታደርግ አስባለች ፡፡

"ታውቃላችሁ ተገቢ እረፍት በጭራሽ አላውቅም፡፡ የአእምሮ ጤንነቴን እና ቤተሰቦቼን ቅድሚያ እሰጣለሁ። የአዕምሮ ጤንነቴ እየታየሁ እና ሕክምና በማግኘት ላይ ነኝ። "