አሜሪካ የሳን ሱ ቺ እስርን ተከትሎ ሚያናማር ላይ ማዕቀብ እጥላለሁ ስትል አስጠነቀቀች

Joe Biden

የፎቶው ባለመብት, Reuters

በሚያናማር የአገሪቱ ጦር መፈንቅለ መንግሥት ማድረጉን ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶ ባይደን በሚያናማር ላይማዕቀብ ሊጥሉ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ።

በቀድሞዋ በርማ በዛሬዋ ሚያናማር የነበረውን አምባገነናዊ ወታደራዊ መንግሥት ተከትሎ በአሜሪካ ለረዥም ጊዜ ማዕቀብ ተጥሎ ቆይቶ ነበር።

ትናንት በሚያንማር የአገሪቱ ጦር መፈንቅለ መንግሥት አከናውኗል። ወታደሮች ሥልጣን መቆጣጠራቸውን ይፋ ያደረጉት የሲቪል መንግሥት አባላትን በቁጥጥር ሥር ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው።

የኖቤል ሰላም ሽልማት ተሸላሚዋ ኦንግ ሳን ሱ ቺ እና ሌሎች የፖለቲካ መሪዎች ተይዘው ወዳልታወቀ ሥፍራ ተወስደዋል።

የተባበሩት መንግሥታት፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና የአውሮፓ ሕብረት በበርማ የተደረገውን መፈንቅለ መንግሥት አጥብቀው ኮንነዋል።

ከእአአ 1989-2010 በእስር ቆይተው የነበሩት ሳን ሱ ቺ በቁጥጥር ሥር ከመዋላቸው በፊት ለደጋፊዎቻቸው በጻፉት ደብዳቤ “መፈንቅለ መንግሥቱን ተቃወሙ” ብለዋል።

ሳን ሱ ቺ መፈንቅለ መንግሥቱ በአገሪቱ ወታደራዊ አምባገነናዊ ስርዓትን ያመጣል ሲሉ ጽፈዋል ተብሏል።

በሚያንማር በወታደሩ እና በሲቪል አስተዳደሩ መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ውጥረት ተከስቶ ነበር።

ባለፈው ሕዳር በተደረገ ምርጫ የሳን ሱ ቺ ፓርቲ 'ናሽናል ሊግ ፎር ዲሞክራሲ' መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችለውን የመቀመጫ ቁጥር ማግኘት ችሎ ነበር። ሆኖም የአገሪቱ ጦር ምርጫው ተጭበርብሯል ሲሉ ቆይቷል።

ጦሩ መፈንቅለ መንግሥቱን ካደረገ በኋላ የ11 ሚንስትሮችን እና ሚንስትር ዲኤታዎችን ሹም ሽር አድርጓል። በሌሎች እንዲተኩ ከተደረጉ ሚንሰትሮች መካከል የፋይናንስ፣ የጤና እና የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ይገኙበታል።

ፕሬዝደንት ባይደን ባወጡት መግለጫ የአገሪቱ ጦር የሕዝቡን ፍላጎት ቀልብሶ ስልጣን መቆጣጠሩ አግባብ አይደለም ብለዋል።

አሜሪካ ከ10 ዓመታት በላይ በበርማ ላይ ጥላ የነበረውን ማዕቀብ ያነሳችው አገሪቱ ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መሸጋገሯን ተከትሎ ነው። ባይደን፤ “በየትኛውም ስፍራ በዲሞክራሲ ላይ ጥቃት ሲደርስ አሜሪካ ወደጎን አትልም” ብለዋል።

ይሁን እንጂ የፖለቲካ ተንታኞች የአገሪቱ ጦር መፈንቅለ መንግሥቱን ለማደረግ ሲነሳ አሜሪካ ማዕቀብ እንደምትጥል ቀድሞ ያውቃል። ከአሜሪካ ማዕቀብ ይልቅ መፈንቅለ መንግሥቱን ተከትሎ ቻይና፣ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ የሚሰጡት ምላሽ ለጦሩ አሳሳቢ ጉዳይ ነው ተብሏል።

ከዚህ ቀደም ቻይና የሚያንማር ጉዳይ ውስጣዊ ጉዳይ ነው በማለት ዓለም አቀፍ ጣልቃ ገብነትን ተቃውማ ነበር። በቀጠናው ከሚገኙት አገራት መካከል ካምቦዲያ፣ ታይናላንድ እና ፊሊፒንስ በበኩላቸው የበርማ ጉዳይ የአገሪቱ ውስጣዊ ጉዳይ ነው በማለት ጣልቃ መግባት እንደማይሹ ገልጸዋል።

በሚያናማር ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል?

ይህ መፈንቅለ መንግሥት በአገሪቷ ዜጎች ዘንድ ከፍተኛ ፍርሃትን ፈጥሯል። በርማ ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትእንደምትሸጋገር ተስፋን ሰንቀው ለነበሩት ዜጎች የሳን ሱ ቺ እና ሌሎች ሲቪል ፖለቲከኞች እስር እና መፈንቅለመግሥት የዲሞክራሲ ተስፋን ያጨለመ ሆኖባቸዋል።

አውራ ጊዳናዎች ጸጥ እረጭ ብለው ታይተዋል። በዋና ከተማ ጎዳናዎች ላይ ብዛት ያላቸው የአገሪቱ ጦር አባላትተሰማርተው ታይተዋል።

ሰኞ ዕለት ተቋርጦ የነበረው የስልክ እና ኢንተርኔት ግነኙነት ማክሰኞ ንጋት ላይ ተመልሷል።

የአገሪቱ ዋነኛ አየር ማረፊያ ግን አሁንም ዝግ እንደሆነ ነው።

ትናንት የሆነው ምን ነበር?

ትናንት [ሰኞ] ወታደሮች የአገሪቱን ሥልጣን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውና መሪያቸውም ኮማንደር ሚነ ኦንግ ሌይንግመሆናቸውን ተናግረዋል።

በርካታ ወታደሮች በአገሪቱ ዋና ከተማ ናይፒታው እና በሌላኛዋ ትልቋ ከተማ ያንጎን ጎዳናዎች በብዛት ታይተዋል።

የሞባይልና ኢንተርኔ አገልግሎት እንዲሁም ስልክ በስፋት የተቋረጠባቸው ዋና ዋና ከተሞች ላይ ሲሆን የአገሪቱብሔራዊ ቴሌቪዥን ሥርጭት ለማድረስ እክል ገጥሞኛል በማለት ተቋርጧል።

በርካታ ወታደሮችም በተለያዩ ቦታዎች እየሄዱ የሲቪል አስተዳደሩ ሚኒስትሮች የነበሩ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ሲያውሉነበር።

የቢቢሲዋ የደቡብ ምሥራቅ ኢሲያ ወኪል እንደምትለው ከሆነ ሳን ሱ ቺ በአገሪቱ ዜጎች ዘንድ ትልቅ ተቀባይነትአላቸው። ሰፊ የሕዝብ ድጋፍ ያላትን ሳን ሱ ቺን የመሰሉ ፖለቲከኞችን ማሰር ትልቅ ውሳኔ ነው።

ይህ ምርጫ የወታደራዊ መንግሥት አስተዳደር ካበቃበት ከ2011 ወዲህ ሲካሄድ ለ2ኛ ጊዜ ነው።

ነገር ግን ይህን ምርጫ ወታደሩ ሳይቀበለው ቀርቶ ነበር።

ይህን ተከትሎም ምናልባት ወታደሩ መፈንቅለ መንግሥት ያደርግ ይሆናል የሚል ፍርሃት ነግሶ ቆይቶ ነበር።

የፎቶው ባለመብት, Reuters

ኦንግ ሳን ሱ ቺ ማን ናቸው?

ሳን ሱ ቺ የበርማ የነጻነት አባት የሚባሉት የጄኔራል ኦንግ ሳን ሴት ልጅ ናቸው።

አባቷ የተገደሉት እሷ ገና የ2 ዓመት ልጅ ሳለች ነበር። የተገደሉትም በርማ ከእንግሊዝ ነጻነቷን ከመቀዳጀቷ ጥቂትቀደም ብሎ በፈረንጆቹ በ1948 ነበር።

ሳን ሱ ቺ በአንድ ወቅት ለዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብት ትልቅ ተምሳሌት ተደርገው ነበር የሚታዩት። ምክንያቱምምሕረት አያውቁም ከሚባሉት የምያንማር ወታደራዊ ኃይሎች በተጻጻራሪ በመቆም በአገሪቱ ዲሞክራሲ እንዲሰፍንበመታገል ረዥም ዓመታት ሳልፈዋል።

ይህን ተከትሎም በ1991 የኖቤል የሰላም ሽልማትን ማሸነፍ ችለው ነበር።

ሳን ሱ ቺ ሽልማቱን ያሸነፉት በቁም እስር ላይ ሳሉ ነበር።

ሳን ሱ ቺ ለ15 ዓመታት በእስር ከቆዩ በኋላ በ2010 ነጻ ወጥተዋል።

በ25 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በተደረገ ምርጫም ፓርቲያቸው ትልቅ ድል አግኝቶ ወደ ሥልጣን መምጣት ችሎነበር።

ሆኖም የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ሳን ሱ ቺ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ አልፈቀደም። ምክንያቱም የሳን ሱ ቺ ልጆችየውጭ ዜጎች ስለሆኑ ነበር። በዚህም የተነሳ መንግሥትን የሚመሩት ከጀርባ ሆነው ነው።

ሳን ሱ ቺ አሁን 75 ዓመትሆኗቸዋል።

የሰላም ኖቤል አሸናፊ የሆኑት ሳን ሱ ቺ በሚያናማር የሮሒንጋ ሙስሊሞች ላይ ለደረሰው ግፍና መከራ ቸልተኝነትበማሳየታቸው ከበርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ያገኟቸው ክብርና እውቅናዎችን ተነጥቀዋል።

ሆኖም በአገሯ ውስጥ ሳን ሱ ቺ በቡድሃ ብዙኃን ዘንድ ሰፊ ተቀባይነት አላት።