'ስደተኛ ሆኜ ተወልጄ በድጋሚም ከልጆቼ ጋር ወደ ስደት ተመለስኩ'

'ስደተኛ ሆኜ ተወልጄ በድጋሚም ከልጆቼ ጋር ወደ ስደት ተመለስኩ'

አቶ ገብረእግዚአብሔር ኃይለሥላሴ ከ27 ዓመታት በፊት ሱዳን ከሚገኘው ኡም-ራቁባ የስደተኞች መጠለያ ወደ ኢትዮጵያ ሲሄዱ እንደ ስደተኛ ወደ መጠለያው እመለሳለሁ ብለው በጭራሽ አላሰቡም ነበር።

በ1977 ደርግ አገሪቱን በሚመራበት ወቅት እና ዕድሜያቸው 30ዎቹ አጋማሽ እያለ በኢትዮጵያ የተከሰተውን ጦርነት እና ረሃብ ሸሽተው በተሰደዱበት ወቅት የህይወታቸው አስከፊ ጊዜ በዚያ የሚያበቃ መስሏቸው ነበር።

ከ27 ዓመታት በኋላ በ70 ዓመታቸው ድንበሩን አቋርጠው ዳግመኛ እንደማያዩት ተስፋ ወዳደረጉበት የስደተኞች መጠለያ ለመመለስ ተገደዱ።