ትግራይ፡ የአገሩን ናፍቆት በሙዚቃ የሚያስታምመው ስደተኛ

ትግራይ፡ የአገሩን ናፍቆት በሙዚቃ የሚያስታምመው ስደተኛ

ትግራይ ውስጥ በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት ከ70 ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ሱዳን እንደተሰደዱ ይነገራል።

ከእነዚህ መካከል አንዱ የሆነው ክብሮም በስደት ላይ ሆኖም ደስታና ሐዘኑን ከክራሩ ጋር በማውጋት ያሳልፋል። ጦርነቱ ቆሞ፣ ነገ የተሻለ ቀን እንደሚመጣ እና እርሱም የሙዚቃ ሕልሙን እንደሚያሳካ ያምናል።