በትግራዩ ግጭት እግሮቿን ያጣችው ታዳጊ አባት ጭንቀት

በትግራዩ ግጭት እግሮቿን ያጣችው ታዳጊ አባት ጭንቀት

የሽረ ከተማ በየዕለቱ ቁጥራቸው በርከት ያሉ ተፈናቃዮችን ታስተናግዳለች።

ከእነዚህም መካከል ከሽረ 50 ኪሎ ሜትር ርቃ ከምትገኘው አክሱም የመጣችው የስድስት ዓመቷ ቤተልሔም ተስፋዬ አንዷ ናት። ቤተልሔም በግጭቱ እናቷንና ሁለት እግሮቿን አጥታለች።

አባቷ የቋጠረውን ጥሪትም ለእሷ ማሳከሚያ አውጥቶ ጨርሷል። አሁን ለቤተልሔም ሰው ሰራሽ እግር እንዲደረግላት የሚያስችለውን ገንዘብ ከየት እንደሚያገኝ ጨንቆታል።