አንድ ዓመት ባስቆጠረው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምን መቼ ተከሰተ?

የትግራይ ጦርነት

[ወደታች ያንሽራቱ]

የኢትዮጵያ ሠራዊት እና አጋሮቹ በአማራ ክልል በሚገኙ የትግራይ ኃይሎች ላይ የተጠናከረ የአየር እና የምድር ጥቃቶችን አካሄዱ።

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ማዕቀብ መጣል የሚያስችል የትዕዛዝ ውሳኔ ላይ ፊርማቸውን አኖሩ። ይህም የአሜሪካ መንግሥት በጦርነቱ ተባባሪ የሆኑ፣ ጦርነቱ እንዲራዘም፣ የሰብዓዊ አቅርቦት እንዳይደርስ እና የተኩስ አቁም እንዳይደረግ እንቅፋት የሆኑ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የኤርትራ መንግሥት፣ ህወሓት እና የአማራ ክልል ባለሥልጣንትን ተጠያቂ ማድረግ ያስችለዋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ በአገሪቱ ሠራዊት እና በትግራይ አማጺያን መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሳይገደሉ እንደማይቀር ተዘግቧል።

በተጨማሪም ለአንድ ዓመት የዘለቀው ጦርነት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ረሃብ አጋልጧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
የምስል መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የምስል ባለቤት Getty Images

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቅሙ ያለው ማንኛውም ዜጋ የትግራይ አማጺያንን ለመውጋት የአገሪቱን ሠራዊት እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቀረቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅም ያላቸው ኢትዮጵያውያን በሙሉ ጦርነቱን በመቀላቀል “አገር ወዳድነታቸውን” እንዲያስመሰክሩ ጠይቀዋል።

የፌደራሉ መንግሥት ከተቀሩት የአገሪቱ ክልሎች ኃይሎችን በማንቀሳቀስ በአሁኑ ወቅት ሁሉም ክልሎች በጦርነቱ ተሳታፊ ሆነዋል። የህወሓት አማጺያን ወደ በርካታ የአማራ አካባቢዎች ለመያዝ ዘመቻ በሚያካሂዱበት ጊዜ የአማራ ክልል “የህልውና ዘመቻ” በሚል ኃይሎቹን እያሰማራ ነው።

የአገር መከላከያ ሠራዊት ሴት የጦር ምርኮኞች በመቀለ ትግራይ
የምስል መግለጫ የአገር መከላከያ ሠራዊት ሴት የጦር ምርኮኞች በመቀለ ትግራይ የምስል ባለቤት Getty Images

ግጭቱ በፍጥነት ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ተዛምቷል። የህወሓት አማጺያን ቁልፍ የሆነውን ጂቡቲን ከአዲስ አበባ የሚያገናኘውን አውራ ጎዳና ለመያዝ ባደረጉት ሙከራ ከባድ ጦርነት መካሄዱ ተገልጿል።

የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ በደቡብ ትግራይ የምትገኘውን ትልቋን ከተማ አላማጣን መያዛቸውን አስታወቁ።

ዓለም አቀፍ የህክምና በጎ አድራጎት ድርጅት የሆነው የድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን (ኤምኤስኤፍ) ሦስት ሠራተኞች ትግራይ ክልል ውስጥ ተገደሉ።

ከመቀለ 25 ኪ.ሜ ርቆ በሚገኘው ቶጎጋ ተብሎ በሚጠራው ገበያ ላይ የአየር ጥቃት ተሰንዝሮ ቢያንስ 60 ሰዎች ተገደሉ። የፌደራሉ መንግሥት የጥቃቱ ዒላማ የነበሩት አማጺያኑ ናቸው በማለት የቀረበበትን ክስ አልተቀበለም።

የምስል ባለቤት BBC

የፌደራሉ መንግሥት “የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲቀርብ” ለማስቻል ሲል የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ አውጆ ከትግራይ አካባቢዎች በወጣ በተመሳሳይ ቀን የትግራይ ኃይሎች የትግራይ መዲናን መቀለን መቆጣጠራቸውን ይፋ አደረጉ።

መቀለ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ቅሳነት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህር ቤት ውስጥ የተጠለለች ተፈናቃይ ያጠበችውን ልብስ ስታሰጣ ሰኔ 11/ 2013።
የምስል መግለጫ መቀለ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ቅሳነት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህር ቤት ውስጥ የተጠለለች ተፈናቃይ ያጠበችውን ልብስ ስታሰጣ ሰኔ 11/ 2013። የምስል ባለቤት Getty Images

የህወሓት ኃይሎች በመንግሥት ጦር ላይ ጥቃት መክፈታቸውን ተከትሎ ከባድ ውጊያ መደረጉ ተሰማ። እራሳቸውን የትግራይ መከላከያ ኃይል እያሉ የሚጠሩት የህወሓት አማጺያን በርካታ ከተሞች መቆጣጠራቸውን እና ጦር መሳሪያዎችን መማረካቸውን ተናገሩ። ይህ ከባድ ጦርነት የተደረገው አገራዊው ምርጫ በተካሄደበት የሰኔ ወር ላይ ነበረ።

የተባበሩት መንግሥታት በትግራይ ክልል የሚገኙ 350 ሺህ ሰዎች በረሃብ አፋፍ ላይ ናቸው፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደግሞ ለረሃብ አደጋ ተጋልጠዋል አለ።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን
የምስል መግለጫ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን የምስል ባለቤት Getty Images

የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን በትግራይ የተከሰተው ቀውስ መፍትሄ እንዳያገኝ አድርገዋል በሚባሉ የአሁን እና የቀድሞ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ጦር አመራሮች፣ በአማራ ሚሊሻዎች እና በህወሓት አባላት ላይ የቪዛ እገዳ ጣሉ።

የአሜሪካ ሴኔት የኤርትራ ጦር ከኢትዮጵያ መውጣትን በተመለከተ የቀረበን የውሳኔ ሐሳብ በሙሉ ድምጽ አሳለፈ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወሓትን “አሸባሪ” ድርጅት ሲል ፈረጀ።

በተባበሩት መንግሥታት የኤርትራ አምባሳደር የኤርትራ ጦሯ ወደ ኢትዮጵያ ዘልቆ ትግራይ ክልል ውስጥ እንደተሰማራ ለጸጥታው ምክር ቤት አስታወቁ። ለወራት የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግሥታት በጦርነቱ ኤርትራ ተሳትፎ የላትም ሲሉ ነበር።

የምስል ባለቤት Getty Images

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለመጀመሪያ ጊዜ ኤርትራ ጦሯን ከትግራይ ለማስወጣት ተስማምታለች አሉ።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን በምዕራብ ትግራይ የተካሄዷል ያሉትን “የዘር ማጽዳት” አወገዙ።

ከመቀለ ከተማ በስተሰሜን በምትገኘው ደንጎላት መንደር ውስጥ በኤርትራ ወታደሮች ተገድለዋል ለተባሉ ሰዎች የመንደሯ ነዋሪዎች ሐዘናቸውን ሲገልጹ።
የምስል መግለጫ ከመቀለ ከተማ በስተሰሜን በምትገኘው ደንጎላት መንደር ውስጥ በኤርትራ ወታደሮች ተገድለዋል ለተባሉ ሰዎች የመንደሯ ነዋሪዎች ሐዘናቸውን ሲገልጹ። የምስል ባለቤት Getty Images

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ምርመራ የኤርትራ ወታደሮች በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃንን በአክሱም ከተማ ስለመግደላቸው ሪፖርት አውጥቷል። አምነስቲ ይህ ጭፍጨፋ በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል ሊሆን ይችላል ብሏል። ኤርትራ የአምነስቲ ሪፖርትን አልተቀበለችውም።

በማይ አይኒ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የኢትዮጵያ ወታደሮች ጥር 22/2013 ዓ.ም
የምስል መግለጫ በማይ አይኒ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የኢትዮጵያ ወታደሮች ጥር 22/2013 ዓ.ም የምስል ባለቤት Getty Images

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ዘመቻ በርካታ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መገደላቸውን እና በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ይፋ አደረገ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ የትግራይ ኃይሎች እጅ እንዲሰጡ 72 ሰዓታት ሰጡ። ከ6 ቀናት በኋላ የኢትዮጵያ ፌደራል ኃይሎች እና አጋሮች የትግራይ መዲና የሆነችውን መቀለን ተቆጣጠሩ።

በፌደራሉ መንግሥት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል የትግራይ ጦርነት በትግራይ ተጀመረ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ ሰጡ።

በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተው ቀውስ

የሰሜን ኢትዮጵያ ቀውስ

የሰሜን ኢትዮጵያ ቀውስ