'አላማዬ ወደ እንግሊዝ መግባት ነው፤ ካልሆነ ግን ባሕር ላይ ብሞት እመርጣለሁ'

'አላማዬ ወደ እንግሊዝ መግባት ነው፤ ካልሆነ ግን ባሕር ላይ ብሞት እመርጣለሁ'

በፈረንጆቹ 2021 ብቻ ከ17 ሺህ በላይ ስደተኞች ከፈረንሳይ ወደ እንግሊዝ ተሻግረዋል።

አንዳንዶቹ ይህንን ለማድረግ በሺዎች የሚቆጠር ፖውንድ ለደላሎችና ለሕገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ከፍለዋል።

ቁጥራቸው የሚበዛው ግን የሚከፍሉት ገንዘብም ሆነ የሚረዳቸው ሰው የሌላቸው ናቸው።

በዚህም ምክንያት በአደገኛ ሁኔታ ባሕር አቋርጠው ወደ እንግሊዝ ለመግባት ይሞክራሉ።

ባለፈው አንድ ዓመት ሱዳናዊያን ስደተኞች በተመሳሳይ ሁኔታ ወደ እንግሊዝ ለመግባት ያደረጉትን ጥረት ቢቢሲ ሲዘግብ ቆይቷል።