ድርቅ የጎዳቸው የምሥራቅ አፍሪካ የዱር እና የቤት እንስሳት

ድርቅ የጎዳቸው የምሥራቅ አፍሪካ የዱር እና የቤት እንስሳት

በአፍሪካ ቀንድ እና በምሥራቅ አፍሪካ አገራት ውስጥ በተከታታይ በነበሩ የዝናብ ወቅቶች የሚጠበቀውን ያህል ዝናብ ባለመጣሉ የተነሳ 26 ሚሊዮን ሰዎች ለምግብ እጥረት ተጋልጠዋል።

በሰሜን ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ኢትዮጵያ እስከ 2022 (እኤአ) አጋማሽ ድረስ የሚቀጥል ድርቅ እንደሚኖር ይህም የሰዎችን እና የእንስሳትን ሕይወት በከፍተኛ ሁኔታ አደጋ ላይ እንደሚጥል ተተንብይዋል።

በአካባቢው ያለው ሁኔታ እጅግ የከፋ መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች የቤት እና የዱር እንስሳት እየሞቱ ነው ብለዋል።

ማሳሰቢያ፤ ይህ ቪዲዮ ለአንዳንድ ሰዎች ሊረብሹ የሚችሉ ምስሎችን ይዟል።