የመጀመሪያው አሜሪካዊ ጠፈርተኛ ልጅ በቤዞስ ኩባንያ ጠፈር ደርሳ ተመለሰች

የ74 ዓመቷ ሎራ ሼፐርድ ከሌሎች ጠፈርተኞች ጋር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የመጀመሪያው አሜሪካዊ ጠፈርተኛ (አስትሮናት) አላን ሼፐርድ ልጅ አባቷ ወደ ጠፈር ከመጠቀ ከ60 ዓመታት በኋላ እሷም ወደ ጠፈር ተጉዛለች።

የ74 ዓመቷ ሎራ ሼፐርድ ቸርክሊ በጄፍ ቤዞስ የጠፈር ታክሲ ብሉ ኦሪጂን ውስጥ ተሳፍረው ወደ ጠፈር ተጉዘው ከተመለሱ ስድስት ሰዎች መካከል ናት።

ተጓዦቹ ሰብ ኦርቢታል በተሰኘው የጠፈር በረራ ተጎዙው ግራቪቲን ከቃኙ በኋላ ወደ ምድር ተመልሷል።

ብሉ ኦሪጂን የተሰኘው የልጥጡ ጄፍ ቤዞስ የጠፈር ምርምር ኩባንያ በ2021 ያስተኮሳቸው መንኩራኩሮች ሶስት ደርሰዋል።

የቀድሞው ጠፈርተኛ በ1998 ቢሆንም ከዚህች ዓለም በሞት የተለየው በ1962 ሜርኩሪ በተሰኘው መንኩራኩር ወደ ጠፈር የተጓዘ የመጀመሪያው አሜሪካዊ በሚል ስሙ በታሪክ መዛግብት ተፅፏል።

ከተጓዦቹ መካከል የቀድሞው የአሜሪካ ብሔራዊ እግር ኳስ ሊግ ኮከብና ጉድ ሞርኒንግ አሜሪካ የተሰኘው የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ የሆነው ማይክል ስትራኣሃን ይገኝበታል።

ሌሎቹ አራት ሰዎች ቅዳሜ አመሻሹን ወደ ጠፈር የመጠቀችውን መንኩራኩር የተሳፈሩት ከኪሳቸው ብዙ ሺህ ዶላሮች ከፍለው ነው።

ብሉ ኦሪጂን፤ ኒው ሼፐርድ ሲል የሰየማት መንኩራኩር የስሟ መታሰቢያነት ለመጀሪያው አሜሪካዊ ጠፈርተኛ እንዲውል በማሰብ ነው።

በነበረው ከባድ ነፋስ ምክንያት ከታሰበላት ሁለት ቀናት ዘግይታ ነው ኒው ሼፐርድ ወደጠፈር የመጠቀች።

በረራው ከዚህ በፊት ብሉ ኦሪጂን ያደረጋቸውን መስመር የተከተለ ሲሆን ተጓዦቹ ተመልሰው ቴክሳስ የሚገኝ አንድ በረሃ ላይ ጄፍ ቤዞስ ተቀብሏቸዋል።

100 ኪሎ ሜትር አልቲቲዩድ ላይ ደርሳ የተመለሰችው መንኩራኩር በዜሮ ግራቪቲ 10 ደቂቃዎች ቆይታለች። ይህም ሼፐርድ ከዓመታት በፊት ካደረገው ቆይታ አምስት ደቂቃዎች ያነሰ ነው።

ልጁ ሎራ አባቷ ወደ ጠፈር በመጠቀ ወቅት ማስታወሻ ይሆኑኛል ብሎ ቤት ውስጥ ያስቀመጣቸው ቁሳቁሶች ይዛ ነው ጠፈር ደርሳ የተመለሰችው።