ዳንኤል ቶሮኢቲች አራፕ ሞይ

በቀድሞ የኬንያ ፕሬዝደንት ዳንኤል ሞይ ህይወት ውስጥ ወሳኝ ኩነቶች
ዳንኤል አራፕ ሞይ ለ24 ዓመታት የኬንያን ፖለቲካ በበላይነት ይዘው ቆይተዋል።

የመጀመሪያው የኬንያ ፕሬዝድንት ጆሞ ኬንያታን ሞት ተከትሎ እአአ 1978 ላይ ወደ ስልጣን መጡ።

በመጀመሪያዎቹ የስልጣን ዘመናቸው ኬንያውያንን በአገር ፍቅር መዝሙሮች እና የልማት ስራዎች ቀልብ መያዝ ቻሉ። 1982 ላይ ግን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ሲደረግባቸው አምባገነን ሆኑ። ሞይ እአአ 1924 ላይ አርሶ አደር ከነበሩት ወላጆቻቸው በምዕራብ ኬንያ ተወለዱ።

ኬንያን ለረዝም ዓመታት የገዙት ሞይ፤ በስልጣን ዘመናቸው የነበሩት ወሳኝ አጋጣሚዎች የሚከተሉት ናቸው፡

 • 1960፣ 1962፣ 1963
  ዝርዝሮች የመጀመሪያው የኬንያ ሕግ መንግሥት የተረቀቀበተን የላንክስተር ኮንፍረንስ በለንደን ከተማ ተሳተፉ
 • 1967
  ዝርዝሮች በፕሬዝደንት ጆሞ ኬንያታ ሶስተኛው የአገሪቱ ምክትል ፕሬዝደንት ተደርገው ተሾሙ፤ በዚህም ደረጃ ለ11 ዓመታት አገልግለዋል።
 • 1978
  ዝርዝሮች የጆሞ ኬንያታ ሞትን ተከትሎ ሁለተኛ የኬንያ ፕሬዝደንት በመሆን ቃለ መሃለን ፈጸሙ። በተመሳሳይ ዓመት ታዋቂውን ጸሃፊ ጉጊ ዋ ኢንጎን ጨምሮ በርካታ የፖለቲካ እስረኞችን ለቀቁ።
 • 1982
  ዝርዝሮች በአየር ኃይል ውስጥ ያሉ ኦፊሰሮች የሞከሩትን መፈንቅለ መንግሥት የሞይ መንግሥት ቀለበሰ። ይህ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የተደረገው ኬንያ በአሃዳዊ የፖለቲካ ስርዓት እንምትተዳደር ይፋ ከሆነ በኋላ ነው። ቀጥሎ በመጡ ወራቶች በርካታ ፖለቲከኞች ለእስር ተዳርገዋል።
 • 1983
  ዝርዝሮች 8-4-4 የተሰኘውን የትምህርት ስርዓት ይፋ አደረጉ። ይህም የታሪካቸው አካል ሆነ።
 • 1989
  ዝርዝሮች ሕግ ወጥ የዝሆን ጥርስ ንግድ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር 12 ቶን የዝሆን ጥርስ አቃጠሉ።
 • 1991
  ዝርዝሮች የዓለም አገራት እና ዲሞክራሲያን አጥብቀው የሚጠይቁ ቡድኖች ባሳደሩባቸው ጫና የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ 2 ሀ እንዲሰረዝ በማድረግ ኬንያ መድብለ ፓርቲ ስርዓት እንድትከተል እና የፕሬዝደንቱ የመመረጥ ገደብ አበጁ።
 • 1992
  ዝርዝሮች ከ20 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በመድብለ ፓርቲ ስርዓት የተካሄደውን ምርጫ አሸነፉ።
 • 2002
  ዝርዝሮች በሙስና እና በዘገምተኛ ምጣኔ ሃብት የታጀበውን የ24 ዓመታት አገዛዝ አብቅቶ መንበረ ስልጣናቸውን ለሙያይ ኪባኪ አስረከቡ።
 • 2019
  ዝርዝሮች ከአንዲት ሴት 21 ሄክታር መሬት በሕገ-ወጥ መንገድ ወስደዋል ተብለው 1ቢሊየን የኬንያ ሽልንግ (300 ሚሊዮን ብር ገደማ) እንዲከፍሉ ፍርድ ቤት ወሰነባቸው።
 • 2020
  ዝርዝሮች ለረዥም ዓመታት በህመም ሲሰቃዩ ቆይተው በናይሮቢ ሆስፒታል ህይወታቸው አለፈ።

ጸሑፍ

ሙቶኒ ሚቹሪ፣ አንቶኒ ማኮሃ፣ ጁሊዬት ኢንጂሪ

የተዘጋጀው በኦላዋሌ ማሎሞ እና ፒዩሪቲ ቢሪር

ዲዛይን ኦላኒዬ አዴቢምፔ፣ ሚሊ ዋቺራ

ፎቶ፡ AFP/Getty Images

ያጋሩ!

  ትዊተር ላይ ያጋሩ
  ፌስቡክ ላይ ያጋሩ
  በዋትስአፕ ያጋሩ
 • whatsapp
 • በኢሜይል ያጋሩ