«ሳሸንፍ ጀርመናዊ ስሸነፍ ስደተኛ» ሜሱት ኦዚል

ከግራ ወደ ቀኝ ጎንዶጋን፣ ኦዚል፣ ፕሬዝደንት ኤርዶዋን እና ሴንክ ቶሱን Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ከግራ ወደ ቀኝ ጎንዶጋን፣ ኦዚል፣ ፕሬዝደንት ኤርዶዋን እና ሴንክ ቶሱን

ጀርመናዊው የአርሴናል እግር ኳስ ተጫዋች ሜሱት ኦዚል ከቱርኩ ፕሬዝደንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶዋን ጋር በአካል መገናኘቱን ተከትሎ ከደረሰበት ወቀሳ በኋላ ራሱን ከበሔራዊ ቡድን ማግለሉን አስታውቋል።

ውሳኔውን አስመልክቶ በሰጠው ረዘም ባለ መግለጫ ላይ የ29 ዓመቱ ኦዚል «ከጀርመን እግር ኳስ ማሕበር የደረሰኝ ምላሽ የብሔራዊ ቡድኑን ማልያ ድጋሚ መልበስ እንዳልሻ አድርጎኛል» ሲል አስታውቋል።

በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ደካማ አቋም አሳይቷል ተብሎ የተወቀሰው ኦዚል «ጀርመን በሩስያው የዓለም ዋንጫ ላይ ላሳየችው የወረደ አቋም ሁሉ እኔ ተጠያቂ እየሆንኩ ነው» በማለት ምሬቱን አሰምቷል።

«ሳሸንፍ ጀርመናዊ ስሸነፍ ስደተኛ» ሲልም የተሰማውን ስሜት በፅሑፍ ገልጿል።

አብረሃም መብራቱ፡ «ቡድኑን ስኬታማ የማድረግ ሕልም አለኝ»

አብረሃም መብራቱ፡ የየመንን ብሔራዊ ቡድን ለትልቅ ውድድር ያበቃ ኢትዮጵያዊ

ወርሃ ግንቦት ላይ ከቱርኩ ፕሬዝደንት ሬሴብ ጣይብ ኤርዶዋን ጋር ፎቶ ተነስተዋል በሚል ኦዚል እና የቡድን አጋሩ ኢካይ ጉንዶጋን ወቀሳ ሲዘንብባቸው እንደነበረ አይዘነጋም።

ኦዚል «እኔና ጉንዶጋን ከፕሬዚዳንቱ ጋር የመከርነው ስለ እግር ኳስ እንጂ ስለፖለቲካ አይደለም» ይላል።

ኋላ ላይ የቱርክ ገዥው ፓርቲ ሁለቱ እግር ኳስ ተጫዋቾች ከፕሬዚዳንቱ ጋር የተነሱትን ፎቶ ለምርጫ ቅስቀሳ ተጠቅሞበታል።

ከክስተቱ በኋላ በርካታ የጀርመን ፖለቲከኞች «ተጫዋቾቹ ለጀርመን ያላቸው አተያይ ጥያቄ የሚያጭር ነው» ሲሉ ተደምጠዋል።

ኤርትራ የሃይማኖት እሥረኞችን ፈታች

ኢትዮጵያ በዱቤ ተጨማሪ ነዳጅ ከሳኡዲ አረቢያ ጠየቀች

''የኤርትራ ኢኮኖሚያዊ ዕቅድ የተነደፈው በኢትዮጵያ ሃብት ላይ ነበር'' አምባሳደር አውዓሎም ወልዱ

ኢትዮጵያ በዱቤ ተጨማሪ ነዳጅ ከሳኡዲ አረቢያ ጠየቀች

የጀርመን መንግሥት የጣይብ ኤርዶዋን አገዛዝ ላይ የተፈፀመውን መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ ቱርክ የወሰደችውን እርምጃ በፅኑ እንደሚቃወም አሳውቆ ነበር።

ከቱርካዊያን ቤተሰቦች የተወለደው ሜሱት ኦዚል «ከቱርክ ፕሬዝደንት ጋር ፎቶ አልነሳም ብል የአያቶቼን አምላክ እንደናቅኩ ነበር የምቆጥረው ሲል» አቋሙን ግልፅ አድርጓል።

ኦዚል ክስተቱን ተክትሎ ከእርሱ አልፎ ቤተሰቦቹ ማስፈራራት እና ዛቻ እየደረሰባቸው እንደሆነም አልሸሸገም።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ