ማርክ ላውረንሰን ዛሬ የሚጀመረውን የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ውጤቶች ግምቱን አስቀምጧል

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተመልሷል። የትኞቹ ቡድኖች የዓመቱ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በድል ይጀምራሉ? የትኞቹስ ሽንፈትን ይቀምሳሉ? እነዚህ ጥያቄዎች ዛሬ ምሽትና ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ ምላሽ ያገኛሉ።

ቀጣዩ የፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ማን ይሆን?

የአፍሪካ እግር ኳስ ቅሌት

ቢጫና ቀይ ካርዶች እንዴት ወደ እግር ኳስ ሜዳ መጡ?

የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን ዛሬ የሚጀምረውን የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት 10 ጨዋታዎች ውጤት ግምቱን አስቀምቷል።

ላውሮ ዓመቱን ሙሉ በፕሪምር ሊጉ የሚደረጉትን የ380 ጨዋታዎች ውጤት የሚገምት ሲሆን፤ ዛሬ ምሽት ማንቸስተር ዩናይትድ ከሌስተር ሲቲ በሚያደርጉት ጨዋታ ግምቱን ይጀምራል።

አርብ

Image copyright BBC Sport

ማንቸስተር ዩናይትድ ከሌስተር (ምሽት 2 ሰአት)

በኦልድ ትራፎልድ የሚገኙ የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ይህን የዓመቱ የመጀመሪያ ጨዋታ ለመመልከት በጉጉት እንደሚገቡ ምንም ጥርጥር የለውም። በቅድመ ውድድር ጨዋታቸው ብዙም የሚያስደስት ውጤት ያላስመዘገቡት ዩናይትዶች ደጋፊዎቻቸውን ለመካስ የማይቆፍሩት ድንጋይ አይኖርም ይላል ላውሮ።

አሰልጣኙ ሞሪንዮ ለማስፈረም ሲፈልገው ነበረው የመሃል ተከላካዩ ሃሪ መጓየር አሁንም በሌስተር ማልያ የሚጫወት ይሆናል።

ማንቸስተሮች ያለ ምንም ጥርጥር ከባለፈው የውድድር ዓመት የተሻለ ቡድን ይዘው ይቀርባሉ የሚለው ላውሮ፤ በዚህ ዓመት ፈተና ሊሆንባቸው የሚችለው የፖል ፖግባ ጉዳይ ብቻ ነው ። በወኪሉ ሚኖ ራዮላ አማካይነት ወደ ባርሴሎና ለማምራት ተዘጋጅቷል ከተባለ በኋላ ፖግባ የተረጋጋ አይመስልም። ምናልባትም የአለም ዋንጫ አሸናፊው ፖግባ በማንቸስተር ደስተኛ ካልሆነ፤ ለሞሪንዮ የመሃል ክፍል ከባድ ፈተና ሊሆንባቸው እንደሚችል ጠቅሷል።

ሌስተሮች በበኩላቸው በክረምቱ የዝውውር መስኮት ተጫዋች ለማስፈረም ሲሯሯጡ ነበር። ምንም እንኳን የአጥቂ መስመራቸው በጄሚ ቫርዲ ላይ ብቻ የተንተለጠለ ቢሆንም የፊት መስመር ተጫዋች ግን ማስፈረም አልቻሉም።

ሌስተር ሲቲዎች ባለፈው ዓመት ካደረጓችው የመጀመሪያ 10 ጨዋታዎች በ7ቱ የተሸነፉ ሲሆን፤ ይህንን ጨዋታ በጥንቃቄ ያደርጋሉ ብሏል።

በላውሮ ግምት መሰረት ማንቸስተር ዩናይትዶች 1- 0 ያሸንፋሉ።

ቅዳሜ

Image copyright BBC Sport

ኒውካስል ከቶተንሃም

ምንም ተጫዋች ያላስፈረሙት ቶተንሃሞች፤ ይህ የውድድር ዓመት እጅግ ወሳኝ እንደሚሆላቸው አስባለው ብሏል ላውሮ። ምን ያህል ውጤታማ ይሆናሉ የሚለው ግን አሁንም አጠራጣሪ ነው።

ኒውካስሎች አስቸጋሪ ክረምት ነበር ያሳለፉት። ደጋፊዎቻቸውም ቢሆኑ ለተጫዋቾች ብዙ ገንዘብ ፈስስ እየተደረገ አይደለም እያሉ ነው።

ኒውካስሎች የመጀመሪያ ነጥባቸውን ለማግኘት ትግል ስለሚያደርጉ ጨዋታው 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ይጠናቀቃል፤ የላውሮ ግምት ነው።

ቦርንማውዝ ከካርዲፍ

ፕሪምየር ሊጉን ዘንድሮ የተቀላቀሉት ካርዲፎች ጥሩ ጥሩ የሚባሉ ተጫዋቾችን አስፈርመዋል። አብዛኛዎቹ ግን ከቻምፒየንሺፑ የመጡ ናቸው።

ቦርንማውዞች በፕሪምየር ሊጉ ሲሳተፉ ይህ የውድድር ዓመት አራተኛቸው ሲሆን፤ የአማካይ ስፍራቸውን ለማጠናከር በ25 ሚሊዮን ፓውንድ ኮሎምቢያዊውን ጄፈርሰን ሌርማን አስፈርመዋል።

የላውሮ ግምት፤ 1-1

ጅማ አባጅፋር የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ሆነ

ያለእድሜ ጋብቻን በእግር ኳስ የምትታገለው ታዳጊ

ፉልሃም ከክሪስታል ፓላስ

ምንም እንኳን ክሪስታል ፓላሶች ለክንፍ ስፍራ ተጫዋቻቸው ዊልፍሬድ ዛሃ ከፍተኛ የሚባል ገንዘብ ቢቀርብላቸውም በዚህ ዓመት አብሯቸው የሚቆይ ይሆናል። አዲስ ፈራሚያቸው ማክስ ሜየር ደግሞ ለቡድኑ ትልቅ ጥንካሬ ይሆናል ተብሎ ይታሰባል።

ፉልሃሞች በዚህ ክረምት ነው ወደ ፕሪምር ሊጉ ያደጉት። ብዙ ተጫዋቾችንም አስፈርመዋል። በዚህ ጨዋታም ስብስባቸውን ተጠቅመው ክሪስታል ፓላስን 2-1 እንደሚያሸንፉ ገምቷል።

Image copyright BBC Sport

ሃደርስፊልድ ከቼልሲ

ሃደርስፊልዶች ባለፈው ዓመት ላለመውረድ ሲታገሉ የነበረ ሲሆን፤ በዚህ የውድድር ዓመትም የተሻለ ነገር ይዘው የቀረቡ አይመስልም። ነገር ግን የመጀመሪያ ጨዋታቸው ችግር ውስጥ ከገባው ቼልሲ ጋር መሆኑ ምናልባት ነጥብ ይዘው እንዲወጡ ሊረዳቸው እንደሚችል ላውሮ ገምቷል።

ቼልሲዎች የሚተማመኑበት ግብ ጠባቂያቸው ቲቦት ኮርቱዋ ወደ ማድሪድ መሄዱን ተከትሎ ተተኪ በማፈላለግ ተተምደው የቆዩ ሲሆን፤ አሁን ግን አዲስ በረኛ አግኝተዋል።

አዲሱ የቼልሲ አሰልጣኝ ማውሪዚዮ ሳሪ ገና ያልተረጋጉ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ምርጥ አራት ውስጥ እንኳን መግባት ይከብዳቸዋል ብሏል። በጨዋታው ግን ቼልሲዎች ሁለት ለባዶ እንደሚያሸንፉ ገምቷል።

ዋትፎርድ ከብራይተን

ዋትፎርዶች ከዓመት ዓመት ከባድ የውድድር ዘመነ እንደሚሆንባቸው ብገምትም ሁሌም ጥሩ ዓመት ያሳልፋሉ ያለው ላውሮ፤ በዚህ ዓመት ግን ጠንካራ እንደሚሆኑ አስባለው ብሏል።

ብራይተኖች በበኩላቸው ባለፈው ዓመት ከወራጅ ቀጠናው ለመውጣት ባለቀ ሰአት ያደረጉት ተጋድሎ የሚያስገርም ነበር። በዚህ ዓመትም ያንኑ ብቃታቸውን ደግመው ያሳዩናል ብሏል። ጥሩ የሚባሉ ተጫዋቾችንም አስፈርመዋል።

በላውሮ ግምት ዋትፎርድ 1-0 ያሸንፋል።

ዎልቭስ ከኤቨርተን

በክረምቱ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያደጉት ዎልቭሶች ብዙ የፖርቹጋል ታዳጊ ተጫዋቾችን አስፈርመዋል። በውድድር ዘመኑም ብዙ ግቦችን እንደሚያስቆጥሩ አስባለው ብሏል።

ኤቨርተኖች ባለፈው ዓመት ያጋጠማቸው አስቸጋሪ የውድድር ዘመን ዘንድሮ የሚደገም አይመስለኝም ያለው ላውሮ፤ በጨዋታው ግን ዎልቭስ 2-1 እንደሚያሸንፍ ገምቷል።

እሁድ

Image copyright BBC Sport

ሊቨርፑል ከዌስትሃም

ሁለቱም ቡድኖች በዝውውር መስኮቱ ቁልፍ ቁልፍ ተጫዋቾችን ያስፈረሙ ሲሆን፤ አዝናኝ ጫዋታ ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል። ዌስትሃሞች ከአንድ እስከ አስር ባለው ውስጥ ለመጨረስ ተስፋ እንዳላቸውም አስባለው ብሏል ላወሮ።

ሊቨርፑሎች ደግሞ ድሮም የነበራቸው ቡድን ላይ ዘንድሮ ያስፈረሟቸው ተጫዋቾች ሲደመሩ እጅግ አስፈሪ ይሆናሉ። እንደውም ለዋንጫው ማንቸስተር ሲቲን ሊገዳደሩ ይችላሉ። ይህንንም ጨዋታ በቀላሉ 2-0 እንደሚያሸንፉ አልጠራጠርም ብሏል።

የላውሮ ምርት አራት ግምት
1. ማንቸስተር ሲቲ 2. ሊቨርፑል 3. ማንቸስተር ዩናይትድ 4. አርሰናል

ሳውዝሃምፕተን ከበርንሌይ

ሳውዝሃምፕተኖች ባለፈው የውድድር ዘመን በ38 ጨዋታዎች 37 ግቦችን ያስቆጠሩ ሲሆን፤ በዚህ ዓመትም ይህን አቋም የሚደግሙ ከሆነ አሳሳቢ ሊሆንባቸው ይችላል።

በርንሌይ በበኩሉ ባለፈው ዓመት ለአውሮፓ ሊግ የመሳተፊያ እድል የሚሰጣቸው ውጤት ቢያስመዘግቡም፤ ሃሙስ ምሽት ጨዋታ አድርጎ እሁድ በፕሪምየር ሊጉ መጫወት ዓመቱን አስቸጋሪ ሊያደርግባቸው ይችላል።

የላውሮ ግምት ሳውዝሃምፕተን 2-1 በርንሌይ

Image copyright BBC Sport

አርሰናል ከማንቸስተር ሲቲ

እጅግ አጓጊ እና ለክብርም ለነጥብም የሚደረግ ወሳኝ ጨዋታ።

አዲሱ የአርሰናል አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሪ ኮከብ የሚባል ተጫዋች ማስፈረም ባይችሉም፤ የቀድሞው ቡድን ብቻውን ግን የሚናቅ አይደለም። በሌላ በኩል ግን የተከላካይ እና የአማካይ መስመሩ ብዙም ተስፋ የሚጣልበት እንዳልሆነ ብዙዎች አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው።

ማንቸስተር ሲሰቲዎች አሁንም ቢሆን አስፈሪ የሚባል አቋማቸው ላይ ነው የሚገኙት። ይህንንም ጨዋታ ያለምንም ጥርጥር ያሸንፋሉ ብሏል። አርሰናሎች ከ20 ዓመት በላይ የቆዩትን አሰልታን አርሰን ቬንገር ማሰናበታቸውን ተከትሎ ብዙ ለውጦች ሊኖሩ ይችላሉ። ይህ ደግሞ ውጤታቸው ላይ ከፍተኛ ተጽህኖ ይኖረዋል።

የላውሮ ግምት፤ አርሰናል 0-2 ማንቸስተር ሲቲ

ተያያዥ ርዕሶች