በጋሬት ክሩክስ የሳምንቱ ምርጥ ቡድን ውስጥ እነማን ገብተው ይሆን?

ሊቨርፑል አሁንም በአሸናፊነቱ እንደቀጠለ ሲሆን፤ ቼልሲ ደግሞ ከዌስትሃም ባደረገው ጨዋታ በአዲሱ የውድድር ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ ነጥብ ጥሏል።

ከዚህ በተጨማሪ በሳምንቱ መጨረሻ ጨዋታዎች የባለፈው የውድድር ዓመት አሸናፊ ማንቸስተር ሲቲዎች በድጋሚ ያሸነፉበት፤ ጎረቤቶቻቸው ማንቸስተር ዩናይትዶች ከዎልቭስ አቻ የተለያዩበትና አርሰናል ኤቨርተንን በማሸነፍ ወደ ጥሩ አቋም የተመለሰበትን ውጤት አሳይቶናል።

ነገር ግን በእነዚህ ሁሉ ጨዋታዎች የትኞቹ ተጫዋቾች ጎልተው መታየት ቻሉ? የጋሬት ክሩክስ የሳምንቱ ምርጥ ቡድን እነሆ።

የላውሮ የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ግምቶች

አይሸወዱ፡ እውነቱን ከሐሰት ይለዩ

Image copyright BBC Sport

ግብ ጠባቂ - ዴቪድ ዴሂያ

Image copyright Getty Images

አሁንም ለተከታታይ ሦስተኛ ሳምንት ዩናይትዶችን ታድጓቸዋል። ከበርንሌይ፣ ዋትፎርድ እንዲሁም በዚህ ሳምንት ደግሞ ከዎልቭስ በነበራቸው ጨዋታ ድንቅ ብቃቱን ማሳየት ችሏል። ራዉል ሄሜኔዝ ወደ ግብ የሰደዳትን ኳስ ያዳነበት መንገድ እጅግ አስገራሚ ነበር።

ከዚህ በተጨማሪም ዊሊ ቦሊ የሞከራት ኳስ ያለቀላት ብትመስልም ዴሂያ እንደምንም ብሎ ግብ ከመሆን አድኗታል።

ስደተኞችን የምትታደገው መርከብ ፈቃዷ ተነጠቀ

ይህን ያውቃሉ? የ2017-2018 የውድድር ዓመት ከተጀመረ ብዙ ግብ ሊሆኑ የሚችሉ ኳሶችን በማዳን የሚስተካከለው ግብ ጠባቂ የለም። እስካሁንም 78 በመቶ የሚሆኑት ኳሶች አድኗል።

ተከላካዮች - ዳኒ ሮዝ ጆዌል ማቲፕ ኢሳ ዲዮፕ

Image copyright Getty Images

ዳኒ ሮዝ: ይህ ተጫዋች ወደ ሌላ ቡድን ሊቀላቀል ነው የሚለው ወሬ መናፈስ ከጀመረ ወዲህ አቋሙ እየወረደ የመጣ ቢመስልም፤ ከብራይተን በነበረባቸው ጨዋታ ግን ድንቅ ነበር።

የቶተንሃምንም የማሸነፊያ ሁለተኛ ግብ ኤሪክ ላሜላ ሲያስቆጥር ለግብ እንዲሆን አመቻችቶ የሰጠው ሮዝ ነበር።

ጆዌል ማቲፕ: ካሜሩናዊው ተከላካይ ከቡድኑ ሊቨረፑል ጋር በመሆኑ በጣም ደስተኛ ይመስላል። ግብ ካስቆጠረ በኋላም ደስታውን የገለጸበት መንገድ ይህንኑ ያሳያል። ከ2016 ጀምሮ እስካሁን ማቲፕ በቡድኑ ቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ከገባባቸው ጨዋታዎች 64 በመቶውን አሸንፈዋል።

የባህር ላይ ወንበዴዎች መርከበኞችን አገቱ

ኢሳ ዲዮፕ: ባለፈው ሳምንት ዌስትሃም ከኤቨርተን ባደረጉት ጨዋታ ተከላካዩ ዲዮፕ የአጥቂ መስመር ተጫዋቾችን ፋታ ነስቷቸው ነበር። በዚህ ሳምንትም ድንቅ ብቃት ላይ ከሚገኙት ቼልሲዎች ጋር በነበራቸው አስቸጋሪ ጨዋታ፤ ምንም ግብ ሳይቆጠርባቸው አቻ እንዲወጡ ከፍተኛውን ሚና ተጫውቷል።

አማካዮች - ዲዬጎ ጆታ ኢኬይ ጉንዶዋንሮን ሌነን ጄምስ ማዲሰን

Image copyright Getty Images

ዲዬጎ ጆታ: ዎልቭሶች በፕሪምየር ሊጉ አይን ውስጥ እየገቡላቸው ካሉ ምርጥ ተጫዋቾቻቸው መካከል ዲዬጎ ጆታ የመጀመሪያውን ቦታ ይይዛል። አዲሱ የውድድር ዓመት ከተጀመረ ይህ ተጫዋች ከየትኛውም የቡድኑ አጋሮች በተሻለ ለግብ ሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።

ኢኬይ ጉንዶዋን: ሲቲዎች ከካርዲፍ ባደረጉት ጨዋታ ዴቪድ ሲልቫ ባይኖርም፤ ጉንዶዋን ግን ተተክቶ ገብቶ አላሳፈራቸውም። ጀርመናዊው የአማካይ ስፍራ ተጫዋች በጨዋታው አንድ ግብ ሲያስቆጥር ያደረገው እንቅስቃሴም አስገራሚ ነበር።

አሮን ሌነን: የበርንሌይ የውድድር ዓመት አሁን ገና ጀመረ ይመስላል። የዩሮፓ ሊግ አስቸጋሪ ጉዟቸውም አብቅቷል። አማካዩ ሌነን ደግሞ ወደ ቀድሞ አቋሙ የተመለሰ ይመስላል። የአማካይ መስመሩንም በተገቢ ሁኔታ ሲመራ የነበር ሲሆን፤ አንድ ግብም ማስቆጠር ችሏል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችና ወላጆቻቸው ስጋት

ጄምስ ማዲሰን: ሌስተር ሲቲዎች ወደ አሸናፊነት እየተመለሱ ይመስላል። በቡድኑ ወጥ አቋም እያሳዩ ካሉ ተጫዋቾች ደግሞ ማዲሰን አንዱ ነው። እስካሁንም ለቡድኑ ሦስት ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን፤ አንድ ለግብ የሚሆን ኳስ ደግሞ አመቻችቶ አቀብሏል።

አጥቂዎች- ሰርጂዮ አጉዌሮ አሌክሳንደር ላካዜት ራሂም ስተርሊንግ

Image copyright Getty Images

ሰርጂዮ አጉዌሮ: ዓለማችን ካየቻቸው ምርጥ ጨራሾች መካከል አጉዌሮ አንዱ ነው ይላል ክሩክስ። ሲቲዎች ከካርዲፍ ባደረጉት ጨዋታ 205ኛ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

አሌክሳንደር ላካዜት: የአርሰናልን ማሸነፊያ ሁለተኛ ግብ በአስደናቂ ሁኔታ ያስቆጠረው ላካዜት ከግቡ በተጨማሪ ደስታውን የገለጸበት መንገድም አስገራሚ ነበር። አርሰናልን ከተቀላቀለ በኋላ ይህ ተጫዋች ካስቆጠራቸው 16 ግቦች መካከል 12ቱን ያስቆጠረው በሜዳቸው ኤምሬትስ ነው።

ራሂም ስተርሊንግ: ሲቲዎች ካርዲፍ ሲቲን 5 ለምንም ባሸነፉበት ጨዋታ ስተርሊንግ የሚያቆመው ሰው አልተገኘም ነበር። ከጨዋታ ጨዋታም አጨዋወቱንና ግብ የማግባት ብቃቱን እያሳደገ መጥቷል።

ተያያዥ ርዕሶች