የሳምንቱ መጨረሻ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት

እንደተለመደው የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን በሳምነቱ መጨረሻ የሚደረጉ የእንግሊዝ ፕሪምር ሊግ ጨዋታዎች ውጤት ገምቷል።

ቅዳሜ

Image copyright BBC Sport

ዌስትሃም ከማንቸስተር ዩናይትድ

በዩናይትድ ቤት የፖል ፖግባ እና የአሰልጣኙ ሞሪንዮ እሰጣ ገባ ብዙዎችን ግራ እያጋባ ነው። እንደውም ይሄ የተጫዋች አሰልጣኝ ግጭት በአንዳቸው ከክለቡ መልቀቅ ሊፈታ እንደሚችል ብዙዎች እየገመቱ ነው።

ምነም እንኳን ቡድኑ የውጤት ቀውስ ውስጥ ቢሆንም ይሄኛው ጨዋታ ይከብደዋል ብዬ አላስብም ብሏል ላውሮ።

ዌስትሃሞች በሌላ በኩል ጥሩ የሚባል ጊዜ እያሳለፉ ሲሆን፤ ከጨዋታ ጨዋታም እየተሻሻሉ መጥተዋል። ነገር ግን ጨዋታው በማንቸስተር አሸናፊነት እንደሚጠናቀቅ ገምቷል።

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ኦዚልን ደገፉ

ሉካ ሞድሪች እና ማርታ የፊፋ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተባሉ

የላውሮ ግምት፡ ዌስትሃም 0 - 2 ማንቸስተር ዩናይትድ

Image copyright BBC Sport

አርሰናል ከዋትፎርድ

አርሰናል በተከታታይ ስድስት ጨዋታዎችን አሸንፈዋል። ምንም እንኳን ትልቅ ከሚባሉት ቡድኖች ጋር ባይገናኙም፤ ከሲቲው ሽንፈት በኋላ እየተሻሻሉ የመጡ ይመስላል።

በአዲሱ አሰልታን ኡናይ ኤምሪ ስር አርሰናል ጥሩ ቡድን የሆነ ይመስላል። ጥያቄው ግን ከእንግሊዝ ምርጥ ሶስት ቡድኖች ውስጥ መግባት ይችላል ወይ ነው። በዚህ ሳምንት ግን ዋትፎርድን በማሸነፍ ሰባተኛ ተከታታይ ድላቸውን ያስመዘግባሉ።

ላውሮ ግምት፡ አርሰናል 2- 0 ዋትፎርድ

ኤቨርተን ከፉልሃም

ባለፈው ከአርሰናል ጋር በነበራቸው ጨዋታ ኤቨርተኖች የአጨራረስ ችግር ታይቶባቸው ነበር። እስካሁን ካደረጉት ስድስት ጨዋታም ማሸነፍ የቻሉት አንዱን ብቻ ነው።

ፉልሃሞች አሁንም ቢሆን የተከላካይ መስመራቸው አስተማማኝ አይደለም።

የላውሮ ግምት፡ ኤቨርተን 2- 0 ፉልሃም

Image copyright BBC Sport

ሃደርስፊልድ ከቶተንሃም

ሃደርስፊልዶች በፕሪምየር ሊጉ እስካሁን ምንም ጨዋታ አላሸነፉም። በደረዣ ሰንጠረዡም የመጨረሻውን ደረጃ ይዘው ነው የሚገኙት። ቶተንሃሞች በሌላ በኩል ወደ አሸናፊነታቸው እየተመለሱ ነው።

ምንመ እንኳን ሃደርስፊልዶች የተደራጅ እግር ኳስ ቢሆንም የሚጫወቱት፤ ጨራሽ የሚባል የፊት መስመር ተጫዋች ግን የላቸውም።

የላውሮ ግምት፡ ሃደርስፊልድ 0 - 2 ቶተንሃም

የሃገራት ሊግ ምንድነው?

ጥቁር አሜሪካዊው ኮሊን ኬፐርኒክ የናይክ ኩባንያ መሪ አስተዋዋቂ ሆነ

Image copyright BBC Sport

ማንቸስተር ሲቲ ከብራይተን

ብራይተኖች ባለለፈው ሳምንት በቶተንሃም መሸነፋቸው የእድል ጉዳይ እንጂ በጨዋታው ተበልጠው አልነበረም። ማንቸስተር ሲቲዎች ደግሞ ምርጥ አቋም ላይ ከመገኘታቸው በላይ ስንት ግብ አስቆጥረው ይሆን የሚያሸንፉት የሚለው ጥያቄ ብዙ ትኩረት አግኝቷል።

የላውሮ ግምት፡ ማንቸስተር ሲቲ 2 - 0 ብራይተን

Image copyright BBC Sport

ቼልሲ ከሊቨርፑል

ቼልሲዎች ባለፈው ሳምንት በካራቦአ ካፕ ሊቨርፑል ላይ የተቀዳጁትን ድል ይደግሙታል ብዬ አላስብም ብሏል ላውሮ። ጨዋታው ከፍተኛ ፉክክር እንደሚታይበትና አዝናኝ እነደሚሆን ምንም ጥርጥር የለኝም በማለት የጨዋታውን ተጠባቂነት ይገልጻል።

ምንም እንኳን ቼልሲዎች በሜዳቸው ቢሆንም የሚጫወቱት፤ የየርገን ክሎፕን አጨዋወት ዘዴ ተቋቁመው የሚያሸንፉ አይመስለኝም።

የላውሮ ግምት፡ ቼልሲ 1- 1 ሊቨርፑል

እሁድ

ካርዲፍ ከበርንሌይ

ባለፈው ሳምንት በፕሪምር ሊጉ የመጀመሪያ ድላቸውን ያስመዘገቡት በርንሌዮች፤ ሁለተኛውን ለመድገም የማይቆፍሩት ድንጋይ አይኖርም። ካርዲፎች ደግሞ በማንቸስተር ሲቲ ከደረሰባቸው አስከፊ ሽንፈት ለማገገም የሚቸገሩ ይመስለኛል ይላል ላውሮ።

የላውሮ ግምት፡ ካርዲፍ 1- 1 በርንሌይ

ሰኞ

በርንማውዝ ከክሪስታል ፓላስ

ክሪስታል ፓላሶች በካራቦአ ካፕ ዌስት ብሮም ላይ የተቀዳጁት ድል ጉልበት የሚሆናቸው ይመስለኛል። ጨዋታውንም እንደሚያሸንፉ እገምታለው ብሏል ላውሮ።

በርንማውዞች በበኩላቸው በሜዳቸው ሲጫወቱ ብዙ ግብ እድሎችን ይፈጥራሉ። የዚህ ሳምንት ጨዋታ ግን የሚከብዳቸው ይመስለኛል።

የላውሮ ግምት፡ በርንማውዝ 2- 1 ክሪስታል ፓላስ

ተያያዥ ርዕሶች