የጋሬት ክሩክስ የሳምንቱ ምርጥ ቡድን

ሊቨርፑልና ቼልሲ ያለመሸነፍ ጉዟቸውን እንደቀጠሉበት ነው። በፕሪምየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥም አንዱ ከአንዱ የበላይ ለመሆን የሳምንት መጨረሻ ፍልሚያ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል።

በሌላ በኩል ካርዲፍ፣ ኒውካስል እና ሃደርስፊልድ እስካሁን ምንም ጨዋታ ያላሸነፉ ሲሆን ዌስትሃሞች ደግሞ ማንቸስተር ዩናይትድና ሆዜ ሞሪንሆን ግራ ያጋባ ድል ማስመዝገብ ችለዋል።

በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት

ስለጉግል የማያውቋቸው 10 እውነታዎች

በሳምንቱ መጨረሻ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች እነማን አስገራሚ ብቃታቸውን አሳዩን? የጋሬት ክሩክስ የሳምንቱ ምርጥ ቡድን እነሆ።

ግብ ጠባቂ- አሊሰን ከሊቨርፑል

Image copyright Getty Images

ብራዚላዊው ግብ ጠባቂ ሊቨርፑል ከቼልሲ ባደረጉት ጨዋታ እጅግ ወሳኝ የሆኑና ያለቀላቸው ሁለት የዊሊያን ሙከራዎችን ግብ ከመሆን አድኗል። ምንም እንኳን የቼልሲው ሃዛርድ ግብ ቢያስቆጥርበትም በሌላ አጋጣሚ አንድ ያለቀለት ሙከራም አድኖበታል።

በያዝነው የውድድር ዘመን አሊሰን ከተሞከሩበት ኳሶች 84.21 በመቶ የሚሆኑትን ግብ ከመሆን አድኗቸዋል።

ተከላካዮች- አንቶኒዮ ሩዲገር ሃሪ ማጓየር እና ዳኒ ሮዝ

አንቶኒዮ ሩዲገር: ይህ ተጫዋች በብዙ ኳስ አፍቃሪዎችና በቼልሲ ደጋፊዎች ዘንድ ተወዳጅነትና አድናቆትን እያተረፈ ነው። ባልታሰበ መልክ የሚያደርጋቸው የመከላከል እንቅስቃሴዎች ደግሞ የብቃቱ ማሳያዎች ናቸው።

ቼልሲዎች ቅዳሜ እለት ከሊቨርፑል ጋር ባደረጉት ፍልሚያ የሞሃመድ ሳላህ፣ ሳዲዮ ማኔ እና ሮቤርቶ ፈርሚንዮን እንቅስቃሴ እግር በእግር እየተከታተል ፋታ ነስቷቸው ነበር።

ሃሪ ማጓየር: ሌስተር ሲቲዎች ኒውካስልን ባሻነፉበት የሳምንቱ መጨረሻ ጨዋታ ምንም ግብ ሳያስተናግዱ እንዲወጡ ያደረጋቸው ማጓየር ነው ማለት ይቻላል። አጥቂው አዮዝ ፔሬዝ ከግብ ጠባቂው ጋር ተገናኝቶ ሊያስቆጥራት የነበረችውን ኳስ ያስጣለበት መንገድ አስገራሚ ነበር።

በኒውካስል የግብ ክልል ውስጥ ተከላካዮቹን በማስጨነቅ ለቡድኑ የፍጹም ቅጣት ማግኘት ምክንያትም ሆኗል። ከዚህ በተጨማሪም በጭንቅላቱ የገጫት ኳስ ለሌስተር ሲቲ ሌላ ግብ ሆና ተመዝግባለች።

ኢትዮጵያ 8.5 በመቶ ዕድገት ታሥመዘግባለች፡ አይ.ኤም.ኤፍ.

«የምታገለው ለማንም ብሔር የበላይነት አይደለም» አቶ በቀለ ገርባ

ዳኒ ሮዝ: ለሁለተኛ ተከታታይ ሳምንት ዳኒ ሮዝ የጋሬት ክሩክስ ምርጥ ቡድን ውስጥ መግባት ችሏል። ቶተንሃሞች ከሃደርስፊልድ በነበራቸው ጨዋታ ወደ ተቃራኒ ቡድን የሜዳ ክልል ውስጥ ቶሎ ቶሎ ለመግባት የሚያደርገው ጥረት ድንቅ ነበር።

ቡድኑ የፍጹም ቅጥት ምት አግኝቶ ሃሪ ኬን ወደ ግብ የቀየራት ኳስ መነሻው ከዳኒ ሮዝ ነበር።

አማካዮች- ጆርጂንዮ ዋይናልደም ማርክ ኖብል ጊሊፊ ሲጉድሰን እና ሜሱት ኦዚል

ጆርጂንዮ ዋይናልደም: በኮከቦች በተሞላው የሊቨርፑል የአማካይና የፊት መስመር ይህ ተጫዋች ጎልቶ ለመውጣት ተቸግሮ ነበር። ነገር ግን ከቼልሲ ጋር በነበራቸው ጨዋታ ድንቅ አቋም ላይ ነበር።

በዚህ ጨዋታ ሦስቱ የሊቨርፑል የፊት መስመር ተጫዋቾች እንደቀድሟቸው አልበሩም። ጄምስ ሚልነርና ጆርዳን ሄንደርሰን ደግሞ ኤደን ሃዛርድን ሲከተሉ ነበር ያመሹት። ዋይናልደም ግን የአማካይ መስመሩን በተገቢ ሁኔታ ሲመራው ነበር።

ማርክ ኖብል: ዌስትሃሞች በፕሪምር ሊጉ በአራት ተከታታይ ጨዋታዎች ምንም ማሸነፍ ባይችሉም፤ ማንቸስተር ዩናይትድን ባሸነፉበት የምሳ ሰዓት ጨዋታ ግን ድንቅ ብቃት ላይ ነበሩ። የአማካይ ክፍሉ ሞተር ደግሞ ማርክ ኖብል ነበር።

በጨዋታው አንድ ለጎል የሚሆን ኳስ ከማቀበሉ በተጨማሪ ከማንኛውም የቡድኑ ተጨዋቾች በተሻለ ብዙ ኳሶችን አቀብሏል።

ጊልፊ ሲጉድሰን : ኤቨርተኖች ከፉልሃም ባደረጉት ጨዋታ ባልታሰበ መልኩ የፍጹም ቅጣት ምት ቢስትም፤ ከባድ ይመስሉ የነበሩ ሁለት ኳሶችን ግን ወደ ግብነት ቀይሯቸዋል።

ተጫዋቹ ካስቆጠራቸው ጎሎች በተጨማሪ አምስት ለግብ የቀረቡ ኳሶችን አመቻችቶ ለቡድን አጋሮቹ አቀብሏል።

ሜሱት ኦዚል: አዲሱ አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሪ ከተጫዋቾቻቸው ብዙ ነገር እየጠየቁ ነው። ብዙ ሃላፊነት መጣል የጀመሩት ደግሞ በሜሱት ኦዚል ላይ ነው። ለዚህም ማሳያው ከዋትፎርድ በነበራቸው ጨዋታ የቡድኑ አምበል ኦዚልን ማድረጋቸው ነው። እሱም በጣም ጥሩ በሚባል የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ሃላፊነቱን ተወጥቷል።

አጥቂዎች- ራሂም ስተርሊንግ ሃሪ ኬን እና ማርኮ አርናልቶቪች

ራሂም ስተርሊንግ:የአምና ሻምፒዮኖቹ ማንቸስተር ሲቲዎች ከብራይተን በነበራቸው ጨዋታ ስተርሊንግ አስገራሚ ነበር። ጨዋታውን ሲያሸንፉም አንድ ግብ ሲያስቆጥር ለሁለተኛው ግብ ደግሞ ኳሱን አመቻችቶ ያቀበለው ስተርሊንግ ነበር።

ሃሪ ኬን: ሃሪ ኬን አሁንም ከዓለም ዋንጫው ድካም የተላቀቀ አይመስልም። እንደ ድሮው አስገራሚ ብቃቱን ባያሳየንም ከሃደርስፊልድ በነበራቸው ጨዋታ ግን ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል።

በፕሪምየር ሊጉም የእሱን ያክል የተሳካለት የፍጹም ቅጣት ምት መቺ የለም።

ማርኮ አርናልቶቪች: ዌስትሃም ከማንቸስተር ዩናይትድ ባደረጉት ጨዋታ የማንቸስተርን ተከላካይ መስመር ሲያስቸግሩ ከነበሩት ተጫዋቾች መካከል አርናልቶቪች አንዱ ነው። ዌስትሃም ማንቸስተር ዩናይትድን ሶስት ለአንድ ሲያሸንፍ ሦስተኛዋን ግብ በአስገራሚ ሁኔታ ያስቆጠራት እሱ ነበር።

ተያያዥ ርዕሶች