አስራ አንደኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምር ሊግ ጨዋታዎች ግምት በላውሮ

ቅዳሜ እጅግ በጉጉት የሚጠበቀው ጨዋታ በአርሰናልና በሊቨርፑል መካከል በኤምሬትስ ስታዲየም ይካሄዳል ይካሄዳል። በዚህ ጨዋታ የበላይነቱን ማን ይወስድ ይሆን?

አርሰናሎች እጅግ አስደሳች የሚባል ጉዞ እያደረጉ ቢሆንም፤ ሊቨርፑል ግን የተሻለ ቡድን ይዞ ነው የሚቀርበው ይላል የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ላውሮ።

የአርሰናሎች የፊት መስመር አስፈሪ ነው፤ የተከላካይ መስመሩ ግን አስተማማኝ አይደለም።

ቅዳሜ

የፎቶው ባለመብት, BBC Sport

ቦርንማውዝ ከማንቸስተር ዩናይትድ

ቦርንማውዞች ባለፈው ሳምንት ፉልሃምን በአሳማኝ መልኩ ሲያሸንፉ የአጥቂው መስመር በትክክል ሃላፊነቱን ሲወጣ ነበር። ቼሪዎቹ የግብ እድል በመፍጠር የተዋጣላቸው ሲሆኑ፤ በዚህ ጨዋታ ደግሞ የራስ መተማመናቸው ከፍ ማለት አለበት።

ማንቸስተር ዩናይትድም ባለፈው ሳምንት ኤቨርተንን 2 ለ1 ሲያሸንፍ በአሳማኝ ብቃት አልነበረም። የማንቸስትር ተጫዋቾች ከፍተኛ አቅምና ጥራት ያላቸው ናቸው።

ነገር ግን ይህንን ጨዋታ ለማሸነፍ ዩናይትዶች ይከብዳቸዋል ብዬ አላስብም፤ የላውሮ አስተያየት ነው።

የላውሮ ግምት: 0-2

ካርዲፍ ከሌስተር

የሌስተር ሲቲ ተጫዋቾች ባለፈው ሳምንት ያጋጠማቸው አሳዛኝ ነገር የስነልቦና ጫና ሊያሳርፍባቸው ይችላል። የቀበሮዎቹ ባለቤት ቪቻይ ስሪቫዳናፐፕራባ ከአራት ባልደረባዎቹ ጋር ሄሊኮፕተር ተከስክሶ ህይወታቸው ማለፉ አስደንጋጭ ነበር።

የሌስተር ተጫዋቾች ከዚህ ሃዘን ተላቀው ውጤት ይዘው ለመውጣት እንደሚጥሩ አልጠራጠርም።

ካርዲፎች በቀላሉ እጅ ባይሰጡም ሌስተር ግን ይህን ጨዋታ ያሸንፋል ብዬ አስባለው።

የላውሮ ግምት: 0-2

የፎቶው ባለመብት, BBC Sport

ኤቨርተን ከብራይተን

ብራይተኖች ባለፈው ሳምንት ከዎልቭስ በነበራቸው ጨዋታ ምንም ግብ ሳያስተናግዱ ከመውጣታቸው በተጨማሪ፤ ሶስተኛ ተከታታይ ድላቸውን ማስመዝገብ ችለዋል።

ከጉዲሰን ፓርክ ስታዲየም ነጥብ ይዞ መውጣት ግን እንደሚታሰበው ቀላል አይደለም።

ኤቨርተን ባለፉት ሳምንታት ነጥብ እየጣለ ቢሆንም፤ እንደ ቡድን ግን ከጨዋታ ጨዋታ እየተሻሻሉ ነው። ይህንንም ጨዋታም ያለ ምንም ጥርጥር እንደሚያሸንፉ አስባለሁ።

የላውሮ ግምት: 2-0

ኒውካስል ከዋትፎርድ

ዋትፎርዶች ዘንድሮ አስገራሚ አጀማመር ሲሆን ያሳዩት፤ ኒውካስሎች ግን እስካሁን የውድድር ዓመቱ ከተጀመረ አንድም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻሉም።

ኒውካስሎች በብራይተን በተሸነፉበት ጨዋታ 27 የግብ ሙከራዎችን ሲያደርጉ፤ አንዱንም ወደ ግብነት መቀየር ግን አልቻሉም።

የላውሮ ግምት: 2-0

ዌስትሃም ከበርንሌይ

ዌስትሃሞች እጅግ መጥፎ የሚባል አጀማመር ነው ዘንድሮ ያጋጠማቸው። በደረጃ ሰንጠረዡ 13ኛ ላይ ሲሆን የሚገኙት ከ10 ጨዋታም መሰብሰብ የቻሉት 8 ነጥብ ብቻ ነው።

በርንሌዮች ባለፈው ሳምንት በቼልሲ በቀላሉ መሸነፋቸው አስገርሞኛል ያለው ላውሮ፤ ላለመሸነፍ የሞት የሽረት ትግል እንደሚያደርጉ ተስፋ አድርጌ ነበር ብሏል።

በርንሌዮች እንደ ባለፈው ዓመት ስድስተኛ ወይም ሰባተኛ ሆኖ ለመጨረስ የሚጫወቱ አይመስልም። ዘንድሮ ከደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላለመገኘት ነው ትግላቸው።

የላውሮ ግምት: 2-0

የፎቶው ባለመብት, BBC Sport

አርሰናል ከሊቨርፑል

እነዚህ ሁለት ቡድኖች ወደፊት አጥቅተው ሲጫወቱ እጅግ አስፈሪ ናቸው። ነገር ግን ሊቨርፑል የተከላካይ መስመሩ ከአርሰናል የተሻለ ነው። በተጨማሪም ሙሉ የቡድኑ አወቃቀር የሊቨርፑል ወጥነት ይታይበታል።

አርሰናሎች መሃል መስመሩ ላይና ተከላካዩ ላይ ብዙ መስራት አለባቸው። የተቃራኒ ተጫዋቾች በእነሱ የግብ ክልል ኳስ ይዘው እንዲጫወቱ ይፈቅዳሉ፤ ይህ ደግሞ ለሊቨርፑል ጥሩ ነው።

እኔ እንደሚመስለኝ ይላል ላውሮ፤ ሊቨርፑሎች በሁሉም ነገር የተሻሉ ናቸው። ለዚህም ነው ይህንን ጨዋታ እንደሚያሸንፉ የማስበው።

የላውሮ ግምት: 1-2

የፎቶው ባለመብት, BBC Sport

ዎልቭስ ከቶተንሃም

ዎልቭሶች ባለፈው ሳምንት ሙሉ የኳስ የበላይነት ኖሯቸው በብራይተን መሸነፋቸው አስገርሞኛል። በዚህ ጨዋታ ምን አይነት አጨዋወት ይዘው ይመጡ ይሆን?

ቶተንሃሞች ባለፈው ሰኞ በማንቸስተር ሲቲ መሸነፋቸው በቡድኑ ተጫዋቾች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል አስባለው ብሏል ላውሮ።

የላውሮ ግምት: 0-2

እሁድ

የፎቶው ባለመብት, BBC Sport

ማንቸስተር ሲቲ ከሳውዝሃምፕተን

ሳውዝሃምፕተኖች እስካሁን ካደረጓቸው 10 ጨዋታዎች ማስቆጠር የቻሉት 6 ግብ ብቻ ነው። በደረጃ ሰንጠረዡም አስራ ስድስተኛ ላይ ነው የሚገኙት።

በተቃራኒው ማንቸስተር ሲቲዎች እስካሁን በ26 ነጥብና 24 ንጹህ ጎል የደረጃው አናት ላይ ተቀምጠዋል። ስለዚህ ሳውዝሃምፕተን ነጥብ ይዞ ይወጣል ብሎ ማሰብ ይከብዳል።

የላውሮ ግምት: 3-0

የፎቶው ባለመብት, BBC Sport

ቼልሲ ከክሪስታል ፓላስ

ክሪስታል ፓላስ አሁንም የግብ ማስቆጠር ችግራቸውን በደንብ የፈቱት አይመስልም። ባለፈው ሳምንት ከአርሰናል ሲጫወቱ ሁለት የፍጹም ቅጣት ምት ቢያገኙም፤ እስካሁን ያስቆጠሯቸው ግቦች ሰባት ብቻ ናቸው።

የአጥቂ መስመራቸው ደግሞ የተንጠለጠለው በዊልፍሬድ ዛሃ ላይ ብቻ መሆኑ ደግሞ ነገሮችን ከባድ ያደርግባቸዋል።

ቼልሲዎች ደግሞ የሚያቆማቸው ያለ አይመስልም። ምርጡ ተጫዋቻቸው ኤደን ሃዛርድ በቡድኑ ውስጥ ሳይኖር እንኳን አጨዋወታው ለተቃራኒ ቡድን እጅግ አስቸጋሪነው።

የላውሮ ግምት: 2-0

ሰኞ

ሃደርስፊልድ ከፉልሃም

በዚህ አጨዋወታቸው ሁለቱም ቡድኖች በቀጣዩ ዓመት ከፕሪምየር ሊጉ ተሰናብተው በቻምፒዮንሺፑ እንደምንመለከታቸው አልጠራጠርም ብሏል ላውሮ። ሁለቱም ቡድኖች በድምር ካደረጓቸው 20 የፕሪምር ሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት አንዱን ብቻ ነው።

ሃደርስፊልዶች እስካሁን በሜዳቸው ባደረጓቸው 5 ጨዋታዎች ምንም ግብ ማስቆጠር አልቻሉም።

ፉልሃሞች ደግሞ ምንም እንኳን ጥሩ አቋም ላይ ባይገኙም፤ ከሃደርስፊልድ በተሻለ ከፕሪምየር ሊጉ ያለመውረድ እድል እንዳላቸው አስባለው ብሏል ላውሮ።

የላውሮ ግምት: 2-1