የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን ግምት ላውሮ እንዲህ አስቀምጧል፤ እርስዎም ይሞክሩት

ቶተንሃም ከቼልሲ Image copyright Robbie Jay Barratt - AMA
አጭር የምስል መግለጫ ቶተንሃም ከቼልሲ

ቼልሲዎች በማውሪሲዮ ሳሪ እየተመሩ በ18 ጨዋታዎች ሽንፈትን ያላስተናገዱ ሲሆን፤ ቅዳሜ ከቶተንሃም የሚያደርጉት ፍልሚያ በጉጉት ይጠበቃል።

ይህ ጨዋታ የመጀመሪያ ሸንፈታቸውን የሚያስተናግዱበት ሊሆን ይችላል ይላል የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን (ላውሮ)።

ቅዳሜ

ብራይተን ከሌስተር

ያለፉት ሁለት ሳምንታት ለሌስተር ሲቲዎች እጅግ ፈታኝ ነበሩ። የክለቡ ባለቤት ጨዋታ ተከታትለው ከሜዳ ሲወጡ ሄሊኮፕተር ተከስክሶ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

የዘንድሮ የቢቢሲ ምርጥ አፍሪካዊ ተጫዋች ዕጩዎች

ብራይተኖች ካደረጓቸው አምስት ጨዋታዎች በአንዱ ብቻ ነው የተሸነፉት። በሜዳቸውም ጥሩ ውጤት ይዞ የመውጣት ታሪክ አላቸው።

የላውሮ ግምት: 1-2

Image copyright BBC Sport

ኤቨርተን ከካርዲፍ

ካርዲፎች እስካሁን ካደረጓቸው አምስት ጨዋታዎች መሰብሰብ የቻሉት አንድ ነጥብና ሁለት ግቦችን ብቻ ነው።

ኤቨርተኖች ደግሞ በአሰልጣኙ ማርኮ ሲልቫ ስር የተሻለ ቡድን እየሆኑ ነው። ከተቀያሪ ወንበር ላይ በመነሳት ልዩነት መፍጠር የሚችሉ ጥሩ ጥሩ ተጫዋቾችም አሏቸው።

የላውሮ ግምት: 2-0

የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።
የአትሌቲኮ ማድሪዱ ጋናዊ አማካይ ቶማስ

ፉልሃም ከሳውዝሃምፕተን

አዲስ አሰልጣኝ ሲሾም ሁሌም ቢሆን ተጫዋቾች የቋሚነት ስፍራን ለማግኘት ምርጥ ብቃታቸውን ያሳያሉ። በፉልሃም ክላውዲዮ ራኔሪ ከተሾሙ በኋላም በቡድኑ ለውጥ እየታየ ነው።

የቅዱሳኑ አሰልጣኝ ማርክ ሁይስ ደግሞ ይህንን ጨዋታ ማሸነፍ ካልቻሉ የክለቡ ቆይታቸው ጥያቄ ውስጥ ሊገባ ይችላል።

የሳውዝሃምፕተን ቀጣይ ሁለት ጨዋታዎች ከማንቸስተር ዩናይትድና ከቶተንሃም መሆኑ ደግሞ ነገሮችን ይበልጥ ከባድ ያደርግባቸዋል።

የላውሮ ግምት: 2-1

Image copyright BBC Sport

ማንቸስተር ዩናይትድ ከክሪስታል ፓላስ

ክሪስታል ፓላሶች በሁሉም ውድድሮች ባደረጓቸው ሰባት ጨዋታዎች በአንዱም ማሸነፍ ያልቻሉ ሲሆን፤ ማስቆጠር የቻሉት የጎል ብዛትም አራት ነው።

ስለዚህ ይህ ጨዋታ ለማንቸስተሮች በቀላሉ የሚያሸንፉት ጨዋታ መሆን አለበት ይላል ላውሮ።

የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።
የሊቨርፑሉ የፊት መስመር አጥቂ ማኔ አምናም ከዕጩዎቹ መካከል ነበር

ማንቸስተር ዩናይትዶች ባለፈው ሳምንት በከተማ ተቀናቃኛቸው ሲቲዎች 3 ለ1 መሸነፋቸው ጫና ያሳድርባቸዋል ብዬ አላስብም፤ እንደውም ይህንን ጨዋታ በቀላሉ ያሸንፋሉ ብዬ አስባለሁ።

የላውሮ ግምት: 2-0

Image copyright BBC Sport

ዋትፎርድ ከሊቨርፑል

ዋትፎርዶች ባለፈው ሳምንት ሳውዝሃምፕተንን ያሸነፉበት መንገድ አከራካሪ ቢሆንም፤ ጥሩ የሚባል ጨዋታ ግን ማድረግ ችለው ነበር። ተጫዋቾቹ በጥሩ የመነቃቃት መንፈስ ላይ እንደሚገኙ ምንም ጥርጥር የለውም።

ሊቨርፑሎች ፉልሃምን በሜዳቸው ሲያሸንፉ አሳማኝ አልነበሩም።

የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።
የናፖሊው ኩሊባሊ ከዘንድሮው ዕጩዎች አንዱ ነው

የሊቨርፑል አብዛኛዎቹ ተጫዋቾች ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በተደረጉ የብሄራዊ ቡድን ጨዋታዎች የተካፈሉ ሲሆን፤ በመጪው ረቡዕ ደግሞ በቻምፒዮንስ ሊጉ ከፒኤስጂ ከባድ ጨዋታ ይጠብቃቸዋል።

እነዚህን ሁሉ ነገሮች ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህ ጨዋታ ከባድ ሊሆንባቸው ይችላል ባይ ነው ላውሮ።

የላውሮ ግምት : 1-1

Image copyright BBC Sport

ዌስትሃም ከማንቸስተር ሲቲ

ብዙ ጊዜ ከብሄራዊ ቡድን ጨዋታዎች መልስ ተጫዋቾች አቋማቸው ይዋዥቃል፤ በማንቸስተር ሲቲ ቤት ግን እንደዚህ አይነት ነገር ብዙም አይታይም።

አሰልጣኙ ፔፕ ጋርዲዮላ ተጨዋቾቹ ሙሉ ትኩረታቸው በፕሪምየር ሊጉ ላይ እንዲሆን የተቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ምንም ጥርጥር የለውም።

ቡድኑ በሰባት ተከታታይ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለ ሲሆን፤ ይሄኛውም ከባድ ይሆንባቸዋል ብዬ አላስብም ብሏል ላውሮ።

የላውሮ ግምት: 0-2

Image copyright BBC Sport

ቶተንሃም ከቼልሲ

ምንም እንኳን ቼልሲዎች አስደናቂ ጉዞ እያደረጉ ቢሆንም፤ ቶተንሃም ደግሞ በደረጃ ሰንጠረዡ በአንድ ነጥብ ዝቅ ብሎ አራተኛ ላይ ነው የሚገኘው።

ላውሮ እንደሚለው ቶተንሃም ካሸነፈ በሰላሳ ነጥብ ከቼልሲ በላይ ይሆናሉ፤ ይህንን አጋጣሚ በቀላሉ አሳልፈው ይሰጣሉ ብዬ አላስብም ብሏል።

የላቀውሮ ግምት : 2-0

የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።
ሞሮኳዊው ቤናቲያ ለአራተኛ ተከታታይ ጊዜ የሊግ ዋንጫ ማግኘት ችሏል

እሁድ

Image copyright BBC Sport

ቦርንማውዝ ከአርሰናል

አርሰናሎች ከዎልቭስ ሲጫወቱ አቻ መውጣት እራሱ ከብዷቸው የነበረ ቢሆንም፤ በዚህ ሳምንት ግን ሽንፈትን የሚያስተናግዱ ይመስለኛል ብሏል ላውሮ።

ቦርንማውዞች ለአርሰናል የመልሶ ማጥቃት አጨዋወት እጅ የሚሰጡ አይመስለኝም፤ እንደውም በጥሩ ጨዋታ የሚያሸንፉ ይመስለኛል።

የላውሮ ግምት: 2-1

ዎልቭስ ከሃደርስፊልድ

ዎልቭሶች ከአርሰናል አቻ ሲለያዩ በጣም አስገርመውኛል የሚለው ላውሮ፤ ማሸነፍ ይገባቸው ነበር ብሏል።

ሃደርስፊልዶች አሁን ባላቸው ብቃት ዎልቭሶችን መቋቋም ይችላሉ ብዬ አላስብም ሲል አስታውቋል።

የላውሮ ግምት: 2-0

ሰኞ

በርንሌይ ከኒውካስል

ኒውካስሎች ወደ ማሸነፈ እየተመለሱ ይመስላል። ይህንን ጨዋታም የማያሸንፉበት ምንም ምክንያት የለም ብሎ ያስባል ላውሮ።

በርንሌዮች ደግሞ የተከላካይ መስመራቸው እየተጠናከር የመጣ ይመስላል። ከሌስተር በነበራቸው ጨዋታም በተለየ መልኩ ሲንቀሳቀስ የነበረው የተከላካይ መስመሩ ነው።

የላውሮ ግምት: 1-1

በሳላህ ቅርጽ የተሰራው ሃውልት መሳቂያ ሆኗል