አርጀንቲናዊው አዲሱ የካርዲፍ ፈራሚ፡ ከእነአውሮፕላኑ የት እንደገባ አልታወቀም

ኤሚሊያኖ ሳላ Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ አዲሱ ፈራሚ ኤሚሊያኖ ሳላ ቅዳሜ ዕለት ነበር ፊርማውን ያኖረው

በ15 ሚሊየን ፓውንድ ካርዲፍ ሲቲን ለመቀላቀል ቅዳሜ ፊርማውን ያኖረው አርጀንቲናዊው አጥቂ ኤሚሊያኖ ሳላ በአነስተኛ አውሮፕላን ወደ እንግሊዝ ሲመጣ የገባበት አልታወቀም ተብሏል።

የ28 ዓመቱ እግር ኳሰኛ እሱን ጨምሮ ሁለት ሰዎችን በጫነችው አውሮፕላን መሳፈሩ ቢረጋገጥም 'ቻነል' የተባሉት ደሴቶች ጋር ከደረሱ በኋላ ግን አውሮፕላኗ ደብዛዋ ጠፍቷል።

ተጫዋቹን ከፈረንሳዩ 'ናንት' የክለብ ሪከርድ በሆነ ዋጋ ያስፈረመው የፕሪምየር ሊጉ ካርዲፍ ሲቲ በተፈጠረው ነገር እጅግ ማዘኑን አስታውቋል።

አሜሪካዊቷ በብስክሌት 'እንደወፍ' በመብረር ክብረ ወሰን ሰበረች

የአስር ደቂቃ እንቅስቃሴ የማስታወስ ችሎታን እንዴት ይጨምራል?

የግዛቲቱ ፖሊስ በበኩሉ አደጋ ደርሶ ሊሆን ይችላል በተባለው ቦታ ከፍተኛ ፍለጋ ቢያደርጉም ምንም ዓይነት ማስረጃ ማግኘት እንዳልቻለና የፍለጋ ሥራውን ለማቋረጥ መገደዱን አስታውቋል።

''አውሮፕላኑ ውሃ ላይ አርፎ ከሆነ የተሳፋሪዎቹ በሕይወት መገኘት ዕድል እጅግ የጠበበ ነው'' ብሏል ፖሊስ።

በመቶዎች የሚቆጠሩ የኤሚሊያኖ የቀድሞ ቡድን ደጋፊዎች ደግሞ እርግጠኛ መረጃ ማግኘት ባይችሉም ከአሁኑ ሃዘናቸውን እየገለጹ ነው።

የኤሚሊያኖ ሳላ ወላጅ አባት ሆራሲዮ ስለጉዳዩ ከጓደኛቸው እንደሰሙና ምንም ዓይነት መረጃ እንደሌላቸው ገልጸዋል።

''ምንም የማውቀው ነገር የለም። እስካሁን የተፈጠረውን ነገር አላመንኩም። ጥሩ ዜና እንደምሰማ ተስፋ አደርጋለው።'' በማለት የልጃቸውን መምጣት እየተጠባበቁ እንደሆነ ተናግረዋል።

ከወንበርና ከሲጋራ የቱ ይገድላል?

ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን?

የፍለጋ ሥራውን የሚመሩት ጆን ፊትዝጄራልድ በበኩላቸው የአካባቢውን የአየር ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የአውሮፕላኗን ተሳፋሪዎች በሕይወት ማግኘት የማይታሰብ ነው ብለዋል።

ምናልባት አውሮፕላኗ ውሃ ላይ አርፋ ቢሆን እንኳን የውሃው ቅዝቃዜ ከደቂቃዎች በላይ በሕይወት እንዲቆዩ አያደርጋቸውም ሲሉ አክለዋል።

ካርዲፍ ሳላን በክለቡ ታሪክ ውድ በሆነ ዋጋ ሲሆን ያስፈረመው፤ ትላንት ወደ ከሰዓት ከአዲሱ ቡድኑ ጋር ሥልጠና ይሠራል ተብሎ እየተጠበቀ ነበር። በተከሰተው አደጋም ተጫዋቾቹ ስለተደናገጡ ለማክሰኞ ታስቦ የነበረው ሥልጠና መሰረዙን የክለቡ ዋና ኃላፊ ኬን ቾ ገልጸዋል።