በኤፍ ኤ ካፕ አራተኛ ዙር አርሰናልና ማንቸስተር ተፋጠዋል

አርሰናልና ዩናይትድ Image copyright Michael Regan

አርሰናል ቀላል የማይባሉ ሳምንታት ቢያሳልፍም በፕሪምር ሊጉ የመጨረሻ ጨዋታው ቼልሲን ማሸነፉ የተጫዋቾቹንም ሆነ የአሰልጣኙን የአሸናፊነት መንፈስ ከፍ እንደሚያደርገው ይታሰባል።

አርሰናሎች የቼልሲውን ጨዋታ ተሸንፈው ቢሆን ኖሮ ለአራተኝነት የሚያደርጉት ጉዞ ከባድ ይሆን ነበር።

ዛሬ ማታ በኤፍ ኤ ካፕ ከማንቸስተር ዩናይትድ የሚያደርጉት ፍልሚያ ደግሞ በዚህ በተነቃቁበት ሰዓት መሆኑ የአሸናፊነቱን ግምት ለአርሰናል ብዙዎች እንዲሰጡ አድርጓል። በሌላ በኩል በሶልሻየር የሚመሩት ዩናይትዶች ሆዜ ሞሪንዮ ከተሰናበቱ በኋላ ተከታታይ ስድስተኛ የፕሪምር ሊግ ጨዋታቸውን አሸንፈዋል።

የህንድ ፊልም አፍቃሪዎች ወተት እየሰረቁ ነው

የሂትለር ሥዕሎች ለምን አልተሸጡም?

እስካሁን ዩናይትዶች በሁሉም ውድድሮች ሰባት ተከታታይ ጨዋታ ያሸነፉ ሲሆን ይሄኛውን የሚያሸንፉ ከሆነ ስምንተኛ ድላቸው ይሆናል ማለት ነው።

በአዲስ ጉልበትና የአጨዋወት ዘዴ ብቅ ያሉት ዩናይትዶች በታዳጊው ማርከስ ራሽፎርድ ፊታውራሪነት እየተመሩ አርሰናልን እንደሚያሸንፉ ተስፋ ሰንቀዋል።

የአርሰናል ብቸኛው ዋንጫ የማግኘት ዕድል የተንጠለጠለው በኤፍ ኤ ካፑ ላይ መሆኑ ጨዋታው የሞት የሽረት እንዲሆን ያደርገዋልም ተብሎ ይጠበቃል።

የአርሰናሉ አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሪ እየመሠረቱት ያለው ቡድን ከየትኛውም የፕሪምየር ሊጉ ቡድን በተሻለ ብዙ የሜዳውን ክፍል ሸፍኗል። ይህ ደግሞ ተጫዋቾቹ ፈጣን እንቅስቃሴ ያደርጋሉ ማለት ነው።

በአሁኑ ሰዓት የአርሰናል ብቸኛው ችግር የተከላካይ መስመሩ ይመስላል። የክንፍ ተከላካዩ ሄክቶር ቤለሪን በጉዳት ምክንያት ከዚህ በኋላ በውድድር ዓመቱ አለመጫወቱ ደግሞ ለአሰልጣኙ ትልቅ ፈተና ነው።

የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ማርክ ላውረንሰን በድንቅ አቋም ላይ የሚገኙት ዩናይትዶች ትክክለኛ ፈተና የሚገጥማቸው በዛሬው የአርሰናል ጨዋታ ነው ይላል።

የማሸነፉን ግምትም ለአርሰናል የሰጠ ሲሆን ጨዋታው በአርሰናል 2 ለ1 አሸናፊነት እንደሚጠናቀቅ ገምቷል።

በሌሎች ጨዋታዎች ደግሞ ቅዳሜ ማንቸስተር ሲቲ ከበርንሌይ፣ ኒውካስል ከዋትፎርድ፣ ኤቨርተን ከሚልዎል እንዲሁም ዌስትሃም ከዊምበልደን ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

መስታወት መፃዒውን ለማየት እንደሚያስችል ያውቁ ኖሯል?

አዲሱ የካርዲፍ ሲቲ ፈራሚ የገባበት አልታወቀም

ውጤቶቹን የገመተው ላውሮ ሲቲዎችና ኒውካስሎች ሁለት ለባዶ በሆነ ተመሳሳይ ውጤት ያሸንፋሉ ሲል ኤቨርተን ደግሞ አንድ አቻ ይጨርሳል ብሏል።

ዌስትሃሞች ደግሞ ተጋጣሚያቸውን ሁለት ለአንድ እንደሚያሸንፉም ገምቷል።

እሁድ በሚደረጉ ሌሎች ተጠባቂ የኤፍ ኤ ካፕ አራተኛ ዙር ጨዋታዎች ክሪስታል ፓላስ ከቶተንሃም እና ቼልሲ ከሼፊልድ ዌንስደይ ይገናኛሉ። ጨዋታዎቹም በክሪስታል ፓላስና በቼልሲ ተመሳሳይ 2 ለ1 አሸናፊነት እንደሚጠናቀቅ ላውሮ ግምቱን አስቀምጧል።