ኢትዮጵያ

 1. የድሬዳዋ ከተማ

  በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ፤ በምሥራቅ ባሌ ጊኒር ወረዳ እና በከተማ በሚገኙ ሁለት ማረሚያ ቤቶች ከስድሳ በላይ ታራሚዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘው ሆስፒታል መግባታቸውን ቢቢሲ አረጋግጧል። ቢቢሲ ከድሬዳዋ ከተማ ጤና ቢሮና ከምሥራቅ ባሌ ዞን ጤና ጽህፈት ቤት እንዳረጋገጠው በወረርሽኙ የተያዙት ሰዎች አስፈላጊውን የሕክምና ክትትልና ድጋፍ እንዲያገኙ እየተደረገ ነው።

  ተጨማሪ ያንብቡ
  next
 2. ፍርድ ቤት

  ጋዜጠኛ ያሲን ጁማን ጨምሮ 11 ተጠርጣሪዎች ሐምሌ 29 የዋስትና መብት ተፈቅዶላቸው የነበረ ቢሆንም ፖሊስ ይግባኝ በመጠየቅ ከእስር ሳይለቀቁ ቆይተው ነበር።

  ተጨማሪ ያንብቡ
  next
 3. አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ ሃምዛ ቦረና

  ቀዳሚ ምርመራ በኢትዮጵያ ሕግ ውስጥ ያለ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከዚህ ቀደም በነበሩት የመንግሥት አስተዳደር ውስጥ እንጂ በአሁኑ ወቅት ብዙ ጊዜ ሥራ ላይ ሲውል እንደማይታይ የሕግ ባለሙያው አቶ ታምራት ለቢቢሲ ገልፀዋል።

  ተጨማሪ ያንብቡ
  next
 4. ዶ/ር ፍሰሃየ አለምሰገድ

  በዩኒቨርስቲው የተለያዩ ግቢዎች በሚገኙ የተለያዩ ለይቶ ማቆያዎች የሚሰሩ 1 ሹፌር፣ 2 የፀረ ተህዋስ ኬሚካል ርጭት ባለሙያዎች፣ 23 የፅዳት ሰራተኞች እና 10 የጤና ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ገል በዩኒቨርሲቲው ኮርፖሬት ኮሚኒኬሽንና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተወካይ ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ዘ ሚካኤል ገልፀውልናል።

  ተጨማሪ ያንብቡ
  next
 5. አርማ

  በጋዜጠኞቹ ላይ የቀረበው ክስም ከሕዳር 12 እስከ ሰኔ 12 2012 ዓ.ም ባለው ጊዜ "የአማራ ሕዝብ በተለየ ተበድሏል፤ መንግስትም የአማራ ሕዝብ ሲበደል ሊከላከልለት አልቻለም ብሎ አስተላልፏል። ይህ ሲተላለፍ እናንተ ሰራተኞች ነበራችሁ በማለት እንደሆነና በዚህም በኦሮሚያ ክልል ደንቢዶሎና ኦዳ ቡልቱ አካባቢ አመፅ መነሳቱን፤ ንብረት መውደሙንና የሰው ሕይወት በመጥፋቱ መጠርጠራቸውን ፖሊስ ገልጿል ሲሉ ለቢቢሲ አስረድተዋል።

  ተጨማሪ ያንብቡ
  next
 6. አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

  በአፍሪካ ህብረት ታዛቢነት እየተደረገ ያለው የኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የሶስትዮሽ የበይነ መረብ ድርድር የተቋረጠ ሲሆን በሚቀጥለው ሳምንትም ይቀጥላል ብላ ኢትዮጵያ እንደምትጠብቅ በዛሬው ዕለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ አርብ ማለዳ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ በአሁኑ ወቅት ግብፅ እና ሱዳን ተቃውሞ ያነሱባቸው ኃሳቦች አዲስ እንዳልሆኑና ኢትዮጵያ የግድቡ ሙሌት ያለ ስምምነት አሁን ተፈፅሞ ተራዛሚ ጉዳዮች በሌላ ስምምነት መከናወናቸው እንዲቀጥል ትፈልጋለች ብለዋል።

  ተጨማሪ ያንብቡ
  next
 7. Tigray Regional Council

  የትግራይ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው በክልሉ ሕገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ በማድረግ የምርጫ ሥርዓት ለውጥና በምክር ቤቱ ውስጥ ባለው የመቀመጫ ብዛት ላይ ጭማሪ አድርጓል። በምክር ቤቱ ውሳኔ መሰረት በክልሉ ከዚህ በፊት የነበረውን የአብላጫ ድምጽ የምርጫ ሥርዓት በመቀየር በ"ቅይጥ ትይዩ የምርጫ ሥርዓት" እንዲተካ በማድረግ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።

  ተጨማሪ ያንብቡ
  next
 8. ጭስና እሳት ሲትጎለጎል

  በሊባኖስ መዲና ቤሩት ከትላንት ወዲያ በደረሰው ፍንዳታ አንድ ኢትዮጵያዊ ሕይወቱ ማለፉን በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄነራል የሆኑት አቶ ተመስገን ኡመር ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በቤይሩት ከትላንት ወዲያት አመሻሽ ላይ ባጋጠመው ከባድ ፍንዳታ ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት እንደደረሰባቸው ተነግሯል። በቤይሩት ኢትዮጵያ ቆንስላ ኃላፊ አቶ ተመስገን ኡመር እንዳሉት አምስት ያህል ኢትዮጵያዊያን መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል መግባታቸውን እንደሰሙና ይህንንም ለማጣራትና ያሉበትን ለማወቅ ጥረት እያደረጉ መሆኑን ለቢቢሲ ገልጸዋል።

  ተጨማሪ ያንብቡ
  next
 9. የትግራይ ምክር ቤት

  የትግራይ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው በክልሉን ሕገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ በማድረግ የምርጫ ሥርዓት ለውጥና በምክር ቤቱ ውስጥ ባለው የመቀመጫ ብዛት ላይ ጭማሪ አደረገ።

  ተጨማሪ ያንብቡ
  next
 10. ድምጻዊ ኢቲቃ ተፈሪ

  ድምጻዊው ሃጫሉ ሁንዴሳ፣ በተገደለበት እለት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርግ ከጓደኞቹ ጋር በሆስፒታል ውስጥ ከወዲያ ወዲህ ሲሯሯጡ እንደነበር ያስታውሳል። አምቦ በነበረው የቀብር ስነስርዓት ላይም አብዛኛው ሰው በሐዘን ስሜት ውስጥ ሆኖ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አልተጠቀመም ነበር።

  ተጨማሪ ያንብቡ
  next